2016-07-25 16:33:00

የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ


በቨነዝዋላ ተከስቶ ያለው ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ውዝግብ እንዲረግብ ለማድረግ አገሪቱን በመምራት ላይ ያለው የፖለቲካ ሰልፍ ተቃዋሚ የፖለቲካ ሰልፍ የቫቲካን ገላጋይነት ሚና ያስፈልጋል በማለት ያቀረበው ጥያቄ የአገሪቱ መንግሥት እንደተስማማበት የደቡብ አመሪካ አገሮች ህብረት ጠቅላይ ዋና ጸሓፊ ኤንረስቶ ሳምፐር የሰጡት መግለጫ በማስመልከት የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል ተጠሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ገልጠው ቅድስት መንበር በቨነዝዋላ ያለው አወዛጋቢው ሁኔታ እልባት እንዲያገኝ የምትሰጠው አስተዋጽኦ አለ ተብሎ የሚታመንበት ከሆን አስተዋጽኦ ለመስጠት ዝግጁ ነች በማለት ከዚህ ቀደም ስለ ቨነዝዋላ ጉዳይ በተመለከተ ቀርቦ ለነበረ ጥያቄ የሰጡት መልስ አስታውሰውና መልሱንም ዳግም በማረጋገጥ ሆኖም ቅድስት መንበር የገለጋይነቱን ሚና ትጫወት ዘንድ የሚል ጥያቄ በቨነዝዋላ ለሚገኘው ለቅድስት መንበር ልኡክ ቢሮም ሆነ በቀጥታ ለቅድስት መንበር አልቀረበም ብለዋል።

የቨነዝዋላ የገቢ ምንጭ የሆነው የነዳጅ ዋጋ ማሽቆልቆል አገሪቱ ለከፋ የኤኮኖሚ ቀውስ ትጋለጥ ዘንድ ካደረገውና እንዲሁም ከ 2013 ዓ.ም.  ከአገሪቱ መሪ የማኅበራዊነት ፖለቲካ አንጸባራቂው ቻቨስ ከዚህ ዓለም በሞት መለየት ተከትሎ የተቀጣጠለው ሰላማዊ ሰልፍ አድማ ያጋባው ያለ መረጋጋት ተከትሎ  እየተስፋፋ ያለው የምግብ የመድሃኒት የኤሌትሪክ ሃይል እጥረት በጠቅላላ ለሕይወት የሚያስፈልጉ መሠረታውያን ነገሮች ሁሉ እጥረት ርእሰ ብሔር ኒኮላስ ማዱሮ የተጋረጠባቸው ጉዳይ ሲሆን። የሟች ቁጥር ከፍ እያለ የኤኮኖሚው ግሽበት 700 በመቶ የደረሰና የሥራ እጦት ጭምር እጅግ ክፍ እያለ መሆኑ ከአገሪቱ የሚሰራጩ ዜናዎች ይጠቁማሉ።

እ.ኤ.አ. ታህሳስ 2015 ዓ.ም. በአገሪቱ ተካሂዶ በነበረው  ምርጫ ተቃዋሚው የፖለቲካ ሰልፍ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ብዙ መቀመጫ እንዲያገኝ ማድረጉና ተቃዋሚው የፖለቲካው ስልፍ የአገሪቱ ርእሰ ብሔር ከስልጣን እንዲወርዱ በሕዝባዊ ድምጽ ውሳኔ እንዲያገኝ ያቀረበው ሕገ መንግሥታዊ ጥያቄ ርእሰ ብሔር ሞዱሮ የበውጭ አገር ጣልቃ ገብነት ሥር የተመራ መንፈንቅለ መንግሥት በቨነዝዋላ ኣውን ለማድረግ ያለመ ነው በማለት ምላሽ የሰጡበት ሲሆን። በአገሪቱ ተከስቶ ያለው ውጥረት መፍትሔው ውይይት ብቻ መሆኑ ከተለያዩ አካላትና ከተለያዩ የአቢያተ ክርስቲያን የበላይ መንፈሳዊ መሪዎች የሚሰጠው መግለጫ ሲያመለክት ሁሉም የውይይት መድረኵ በጉጉብት እየተጠባበቀ መሆኑ ከቨነዝዋላ የሚሰራጩ ዜናዎች ይጠቁማሉ። 








All the contents on this site are copyrighted ©.