2016-07-25 16:30:00

ብፁዕ ካርዲናል ታውራን፥ የግኑኝነት ባህል ብቻ ነው አሸባሪነትና የጥላቻ መንፈስ ለማስወገድ የሚያስችለው


ከተለያዩ ኃይማኖቶች ጋር የሚደረገው የጋራ ወይይት የሚያነቃቃው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ዣን ልዊስ ታዉራን ዓለማችን እያናጋ ያለው ግብረ ሽበራና አሸባሪነት እያስፋፋው ያለው የጥላቻ መንፈስ ለማስውገድ የሚቻለው የግኑኝነት ባህል በማስፋፋትና በማረጋገጥ መሆኑ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ አስታውቀዋል።

በአለማችን ክልል እየተከሰቱ ያሉት ግብረ ሽበራ ስትመለከት በእውነቱ ለምን የሚለው ጥያቄ እንድታቀርብ ትገደዳለህ። ሰው ለሞት ነውን የተፈጠረው የሚለውን ጥያቄ እንድታነሳም ያስገድደኻል።

ባንድ ወቅት የሰው ልጅ ሟች መሆኑ በመታመን አንድ ቀን መሞት አይቀርም የሚል አነጋገርና ልምድ ያዘወትር ነበር። በአሁኑ ወቅት ግን መሞት አይቀርም ሳይሆን በሞት ተከበህ የምትኖር ሆኖህ ነው የሚሰማኽ ከቤት ወጥተኽ መመለስህንም በምንም ተአምር እርግጠኝነት የሌለው ሁሉም በጊዚያዊነት ባህል ተከቦና ተውጦ የሚኖርበት ጊዜ ነው። በተለያየ ክልልና አካባቢ ሕይወትን ለአደጋ የሚያጋልጥ ሰው ሰራሽ ጥቃት ሲጣል ይታያል። ይኽ ደግሞ በእውነቱ በሰው ልጅ ልብ ውስጥና አእምሮ የአለ ማረፈ መንፈስ እንዲሰርጽ ያደርጋል። የመከባበርና የመገናኘት ባህል ብቻ ነው በሁሉም አገሮች ውስጥ ሰላም ለማረጋገጥ የሚቻለው። እያንዳንዱ የኅብረተሰብ ክፍል ማክበር አዛውንቱ ወጣቱን ወላጅ ልጆቹን ልጆች ወላጆች እንዲያከብሩ ከተደረገ የመከባበርና የግኑኝነት ባህል ለማስፋፋት ከተቻለ በዓለማችን የሚታየው የሰላም እጦት ይወገዳል። አንድ አዲስ የግኑኝነት ፍልስፍና ማረጋገጥ ያስፈልጋል። አንዱ አለ ሌላው ደስተኛ ሊሆን እይችልም። በበለጠ ደግሞ አለ ግኑኝነት ደስታ አይኖርም። ስለዚህ የግኑኝነት ባህል ማስፋፋት፡ ታሪክን ማንበብ ታሪክ ማወቅ ያስፈልጋል ብለዋል።

የሰው ልጅ ልብ በጥላቻና በቂም በቀል የተሞላ ሆኗል። ሽክም የከበዳችሁ ወደ እኔ ኑ የሚለው ጌታ ማዳመጡ ያስፈልጋል። ሸክም በዕለታዊ ሕይወት ባህርያዊ ነው። ስለዚህ ይኸንን ከባዱ ሸክም አለ ምንም ቁጣና ንዴት ለመወጣት የሚያስችለው የትብብርና የግኑኝነት ባህል ነው። የመተሳሰብ ባህል ነው። በሃይማኖቶች መካከል መቀራረብና መተዋወቅ እጅግ ያስፈልጋል። የዮርዳኖሱ ልዑል ቢን ታላል እያንቃቁት ያለው የግኑኝነት ባህል ካይሮ ከሚገኘው አል አዝሓር መንበረ ጥበብ ጋር እየተካሄደ ያለው ግኑኝነት እንደ አብነት ጠቅሰው፡  መፍትሔው ውይይትና ግኑኝንት ነው፡ ወደድንም ጠላንም ልንወያይ የተበየነብን የአንድ አባት ልጆች ነን በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.