2016-07-22 16:40:00

የዛምቢያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ለቀጣዩ ዓስር ዓመት የሚበጅ አዲስ የሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ እቅድ


የዛምቢያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት እ.ኤ.አ. ሐምሌ 21 ቀን 2016 ዓ.ም. ለሚቀጥሉት አስር ዓመታት የዛምቢያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ መርሐ ግብር ለመወጠን ባካሄደው ይፋዊ ስብሰባ የብፁዓን ጳጳሳቱ ምክር ቤት የዛምቢያ ካቶሊካውያን ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት በሚል አዲስ ስያሜ እንዲተካ መወሰኑ የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ ዘንጋሪኒ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችሏል።

የዓለም ሳትሆን ከጊዜ ጋር የምትራመድ ቤተ ክርስቲያን

የዛምቢያ ካቶሊካውያን ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት በሉሳካ ባካሄደው ጉባኤ እ.ኤ.አ. ከ 2017 እስከ 2026 ዓ.ም. እቅዳዊ መርሐ ግብር ማጽደቁ የሉሳካ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ኣቡነ ጆርጅ ተለስፎረ ምፑንዱ ማሳወቃቸው የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ ዘንጋሪኒ አክለው፥ በአገሪቱ የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በመንፈስ ቅዱስ ድጋፍ መሠረት ጥበብ በተካነው አመክንዮ በተላበሰ ቃልና ተግባር በዛምቢያ ወንጌልን ለማስፋፋት የሚደግፍ ቤተ ክርስቲያኒቱ ወቅታዊው ዓለም በጥልቀት ለመተንተን የሚያስችላትና ከጊዜ ጋር ለመራመድ እንድትችል የሚያደርጋት ነው እንዳሉም አስታውቀዋል።

ቃሉ እንደሚለውም አለ እርሱ ቤትን መገንባት ከንቱ ነው በመሆኑም ክርስቲያኖች ክርስቶስን ማእክል ያደረገ ከእርሱ ጋር በመተባበር የሚኖሩት ሕይወት የሚያከናውኑት በተሰማሩበት መስክ ሁሉ ክርስቶስን የሚያንጸባርቁ ሆነው ሊገኙ ይገባቿል። ይኽ ደግሞ ለአንድ ክርስቲያን አማራጭ ሳይሆን የማያሻማ ጥሪ ነው። በዛምቢያ የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ክርስቶሳዊነት በማህበራዊ በፖሊቲካዊና በኤኮኖሚያዊ መስክ ሁሉ በመኖር ንቁ ሆና እንድትገኝ የሚያግዛት ነው እንዳሉ የጠቀሱት የቫቲካን ርዲዮ ጋዜጠኛ ዘንጋሪኒ በማያያዝም፥

የዛምቢያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የሚል አዲስ መጠሪያ የተሰጠው የዛምቢያ ብፁዓን ጳጳሳኣት ምክር ቤት እ.ኤ.አ. በ 1965 ዓ.ም. የተቋቋመና የውስጥ ሕገ መመሪያው እ.ኤ.አ. በ 1984 ዓ.ም. በቅድስት መንበር ጸድቆ ሕጋዊ ቅዋሚው እውቅና ያገኝ ሲሆን የመላ አፍሪቃና ማዳጋስካር ብፁዓን ጳጳሳት ጉባኤ አባል እንዲሁም የዚያ ኤርትራ ኢትዮጵያ ከንያ ማላዊ ታንዛኒያ ደቡብ ሱዳንና ኡጋንዳን የሚያቅፈው የምስራቅ አፍሪቃ አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ኅብረት ጭምር አባል መሆኑ በማስታወስ አመልክቷል።








All the contents on this site are copyrighted ©.