2016-07-20 16:50:00

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ወደ ፖላንድ የሚያደርጉት ሐዋርያዊ ጉዞ ምክንያት የድምጸ ርእየት መልእክት አስተላለፉ


በአገረ ፖላንድ እ.ኤ.አ. ከ ሐምሌ 26 እስከ ሓምሌ 31 ቀን 2016 ዓ.ም. የሚካሄደው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ምክንያት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ   እ.ኤ.አ. ሐምሌ 19 ቀን 2016 ዓ.ም. ለፖላንድ ወጣቶችና በአገሪቱ ለምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የድምጸ ርእየት መልእክት ማስተላለፋቸው የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ ሊዛ ዘንጋሪኒ ገለጡ።

ይኽ በክራኮቪያ በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ዙሪያ የሚካሄደው 31ኛው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን እውን የሚሆንበት ዕለት በተቃረበበት ወቅት ቅዱስነታቸው በፖላንድ የሚያካሂዱት ሐዋርያዊ ጉዞ በማስመልከት፥ ከተሳታፊያን ወጣቶች እንዲሁም ከተወዳጅዋ አገረ ፖላንድ ጋር ለመገናኘት ያላቸው ፍላጎት ገልጠዋል። ጉዞውና ዓለም አቀፉ የወጣቶች ቀን በዚህ በምኅረት ዓመት ወቅት የሚካሄድ በመሆኑም በመለኰታዊ ምኅረት የተመራ የወጣቶች ቀን ላስጀመሩትና ለፖላንድ ሕዝብ ወደ ነጻነት የመሩት ለአገሪቷ ተወላጅ ለሆኑት ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በልብ አመስግነዋል።

ወድ የፖላንድ ወጣቶች ይኸንን የወጣቶች ቀን ለማስተናገድ በአቢይ ቅድመ ዝግጅት ተወጥራችሁ በተለይ ደግሞ በጸሎት ተግታችሁ የምታካሂዱት መንፈሳዊና ሰብአዊ እንቅስቃሴ የወጣቶች ቀን የተዋጣለት ለማድረግ የሚል ነው፡ እያከናወናችሁት ባለው መፈሳዊ ቅድመ ዝግጅት ልትመሰገኑ ይገባል። በፍቅር ተነቃቅታችሁ ስላደረጋችሁትና እያደረጋችሁ ስላለው ሁሉ ከልብ አመስግናችኋለሁ ገና ከወዲሁ በእቅፌ ሥር አኖራችኋለሁ ሐዋርያዊ ቡራኬ ጭምር አስተላልፍላችኋለሁ እንዳሉ ዘንጋሪኒ አስታውቀዋል።

ከኤውሮጳ ካፍሪካ ከአመሪካዎች ከእስያና ከኦቻይና የተወጣጡ ወጣቶች ጉዞአቸውን ወደ ክራኮቪያ አቅንቷል። ጉዞው የእምነትና የወንድማማችነት ንግደት እንዲሆን ወጣቱ ለተነሱባቸው አገሮችና  ወደ ክራኮቪያ የሚደረገው ጉዞ ሁሉ እባርካለሁ።  ቡራኬየን አስተላልፋለሁ፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያንን “ምህረትን የሚያደርጉ ምሕረትን ስለሚያገኙ ደስ ይበላቸው (ማቴ. 5,7) የሚለውን ቃሉ በሕይወታችሁ ለማጣጣም የሚያበቃችሁ ጸጋው ይስጣችሁ ብለው፥ ለዓለም የውህደት ትእምርትና ምስክርነት ለማቅረብ ያንን የተለያዩ አሕዛብ ባህሎች ቋንቋና ዘውገ በጠቅላላ ኅብረ ቅንስል የሚያጸና የምኅረት አካል በሆነው በኢየሱስ ስም የምታሳዩት አንድነት የውህደት ውበት የሚመሰክር የውሁድነት ትእምርት ነው ከእናንተ ጋር ለመገናኘት ትልቅ ጉጉት አለኝ እንዳሉ ዘንጋሪኒ ገለጡ።

ለእናንተ የዚያች በፈተና ባስቸጋሪ ሁነት ላለፈቸው በእምነት በመጓዝና በቅድስት ድንግል ማርያም እጅ ለተደገፈችው የአገረ ፖላንድ ዜጋ ወጣት ልጆቼ በመካከላችሁ ለመገኘት ያለኝ ጉጉት አቢይ ነው፡ እዛ መገኘት ጸጋ ነው ብለዋል። ወደ ክዘስቶቾኮዋ የሚደረገው መንፈሳዊ ንግደት ለእኔ በእውነት በዚያ በትልቅ ፈተና ባለፈው እምነትችሁ ውስጥ እንድገባ የሚያደርገኝ ነው። ለጸሎታችሁ አመሰግናችኋለሁ። የሆላንድ ብፁዓን ጳጳሳትና ካህናት ገዳማውያንና ደናግል ዓለማውያን ምእመናን በተለ ደግሞ ለዚያ በሃሳቤ ያንን የድኅረ ሲኖዶስ የፍቅር ሐሴት የተሰየመው ሓዋርያዊ ምዕዳን ለማቅርብላቸው ቤተሰቦች ሁሉ ምስጋናዮን አቀርባለሁኝ።

የአንዲት አገር ግብረ  ገባዊና መንፍሳዊ ጤንነት መመዘኛው ቤተሰብ ነው። ለዚህም ነው ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ እጮኞች ወጣት ባለ ትዳሮችንና ቤተሰቦችን ያፈቅሩ የነበሩት፡ በእምነት ጉዞ ወደ ፊት በሉ።

ይኽ መልእክት ለእናንተ ያለኝ ፍቅር ማረጋገጫ እንዲሆናችሁ አስተላልፋለሁኝ። በጸሎት አንድ መሆናችንን እንቀጥልበት። በአገረ ፖላንድ ያገናኘን፡ በማለት ያስተላለፉት የድምጸ ርእየት መልእክታቸው እንዳጠቃለሉ ዘንጋሪኒ አስታውቀዋ።








All the contents on this site are copyrighted ©.