2016-07-20 16:54:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፥ ዕረፍት ለሚነሳው ጭንቀታችን ብቸኛው መፍትሔው ኢየሱስ ነው


ቅዱስ አባኣችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ከሐምሌ 26 ቀን እስከ ሐምሌ 31 ቀን በክራኮቪያ በሚካሂደው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ምክንያት ወደ ፖላንድ ለመነሳት ከጥቂት ቀናት  ቀደም በማድረግም በዋሽንግተን የተለያዩ አቢያተ ክርስቲያን ለአንድነት አቅንቶ የሚደረገው የጋራው ውይይት የሚያንጸባርቅ ከተለያዩ አቢያተ ክርስቲያን የተወጣጡ በበዙ ሺሕ የሚገመቱ ወጣቶች በአንድነት 2016 ዓ.ም. በሚል መርሕ ቃል ሥር እ.ኤ.አ. ሐምሌ 16 ቀን 2016 ዓ.ም. ተካሂዶ ወደ ነበረው የተለያዩ አቢያተ ክርስቲያን ወጣቶች ቀን የድምጸ ርእየት መልእክት አስተላልፈው እንደነበር የቫቲካን ርዲዮ ጋዜጠኛ ኢዛበላ ፒሮ ይጠቁማሉ።

ያ በዋሽንግተን ከተማ የተካሄደው የተለያዩ አቢያተ ክርስቲያን ለውህደት ዓልመው የሚያደርጉት ጉዞና የጋራ ውይይት ባህርይ ያለው የተለያዩ አቢያተ ክርስቲያን ወጣቶች ቀን በኒክ ሃል የተመሰረተው የጸሎና ያስፍሆተ ወንጊል እንቅስቃሴ ያሰናዳው መሆኑ የገለጡት ፒሮ አያይዘውም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ለዚህ ጉባኤ ባስተላለፉት መልእክት

የተከበራችሁ ወጣቶች በወጣትነት ዕድሜው ጭንቀት የማይሰማው ወጣት ቢኖር ገና ያለ እድሜውያረጀ ነው። ስለዚህ በውስጣችሁ ጭንቀትና አለ ማረፍ ሲሰማችሁ እትፍሩ፡ የወጣትነት እድሜያችሁ የሚጠይቀው ሁነት ነው። የሚጠበቅባችሁ የሚሰማችሁ አለ ማረፍ መለየት ብቻ ነው። ስለዚህ አለ ማረፍ ይሰማችኋል ወይ የሚል ጥያቄ አቅርበው፡ የዚህ በውስጣችሁ ያለው ያለ ማረፍ ስሜት ብቸኛው መልሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡ ከእርሱ ጋር ለመገናኘት በእርሱ ለመገኘት ፍቀዱ። ከኢየሱስ ጋር ሽረትም ሆነ ክሽፈት ፈጽሞ አይኖርም። ይኽ እውነት ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ። እግዚአብሔር አያታልልም አያደናግርም ስለዚህ ኢየሱስ ይጠብቅሃል ይጠብቅሻል ይጠብቀናል። እርሱ ነው በልባችሁ የአለ ማረፍ ዘር ያኖረው ከእርሱ ጋር መሆን የሚያከስር መሆን አይደለም፡ በርቱ፡ ኢየሱስ ና ነይ ከኔ ጋር ሁን ከእኔ ጋራ ሁኚ ይለናል በማለት ያስተላለፉት የድምጸ ርእየት መልእክት ማጠቃቀላቸው ገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.