2016-07-18 16:21:00

ወጣቱን ትውልድ በፍቅር ለፍቅር ማነጽ


የካሪታስ ኢንተርናዚዮናሊስ ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል አቶኒዮ ታግለ በኵላዊት ቤተ ክርስቲያን አዘጋጅነት እ,ኤ.,አ. ከሐምሌ 26 እስከ ሐምሌ 31 ቀን 2016 ዓ.ም. በክራኮቪያ ወደ ሚካሄደው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ለመሳተፍ በመዘጀት ላይ ለሚገኙት ወጣቶች ባስተላለፉት የድምጸ ራእይ መልእክት ሰብአዊነት ወደ ፍቅር ለመለወጥ የወጣቱ ታታሪነት ኃይልና ጽኑ ስሜት ያስፈልገናል እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ ገለጡ።

ብፁዕ ካርዲናል ታግለ እ.ኤ.አ. ሐምሌ 27 ቀን 2016 ዓ.ም. በካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በካሪታስ ለሚጠራው የተራድኦ ማኅበር ቅርንጫ ተጠሪዎች ከሆኑት ውስጥ ከስምንት አገሮች የተወጣጡ በሊባኖስና በኢራቅ ለሚገኙት ቅርንጫፍች ተጠሪዎች የምገኙባቸው አካላት በክራኮቪያ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ተሳታፊያን ወጣቶች ጋር እንደሚገናኙ ከቫቲካን ረዲዮጋር ቃለ ምልልስ ያካሄዱት በፖላንድ ለካሪታስ ቅርንጫፍ ዋና አስተዳዳሪ አባ ማኢያን ሱቦችዝ ገልጠው፥ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ዙሪያ የሚከበረው የክራኮቪያው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን የመለኮታዊ ምኅረት በዓል ነው። እየተኖረ ባለው ቅዱስ የምኅረት ዓመት ምክንያት በዘንድሮው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በካሪታስ ለሚጠራው የተራድኦ ማኅበር ተጠሪዎች መገኘት እጅግ አስፈላጊ እንዲሆን አድርጎታል፡ ስለዚህ የካሪታስ ኢንተርናዚዮናሊስ ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ታግለ የወጣቶች ጋር በመናኘትም የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የተራድኦ ማኅበር እንቅስቃሴና አገልግሎት ያሰጣጥ ሂደቱን ያብራራሉ። ተከትሎም በተለያዩ የሊባኖስና የኢራቅ የካሪታስ ቅርንጫ ተጠሪዎች የሚገኙባቸው ከስምንት አገሮች የተወጣጡ የካሪታስ ተጠሪዎች የምስክርነት ቃል እንደሚሰጡ ገልጠው አያይዘውም የወጣቱ እምቁ ኃይል እንዳይዛባ በሁሉም መስክ መደገፍ የሁሉም ኃላፊነት ነው፡ ቤተ ክርስቲያን በዚህ አገልግሎትም በዋነኝነት የምትጠቀስ ነች ብለዋል።

በድኽነት ጫንቃ ሥር ለሚገኙት ያንን የጌታ ፍቅር ለመመስከ በተለይ ደግሞ ለእነርሱ የሚሰጠው ፍቅር ለጌታ ያለን ፍቅር ሚዛን መሆኑ በሚገባ አውቀን በዚህ ፍቅር አማካኝነት ወጣቱን በማነጽ የበለጠው ዓለም ግንባታ ታልሞ በሚደረገው ጥረት ወጣቱን ቀንደኛ ተወናያን ማድረግ ያስፈልጋል ብለው የካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን የተራድኦ ማኅበር በዚህ በክራኮቪያ በሚካሄደው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን በኤኮኖሚ ችግር ምክንያት ለመሳተፍ ለማይችሉ ለድኾች ወጣቶች የኤኮኖሚ ድጋፍ እያቀረበ እንደሚገኝም ገልጠዋል።

ሁሉም እንደሚያውቀው የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የተራድኦ ማኅበር ድኾችን የጎዳና ተዳዳሪ ዜጎች በተለያየ ችግር ምክንያት ተነጥለው በከተሞቻችን ጥጋ ጥግና በኅልውና ጥጋ ጥግ የሚገኙትን በድኽነት የተጠቁት አረጋውያንን ሁሉ በመደገፍ ሁሉም መሠታዊ የሆነው አስፈላጊ አገልግሎት እንዲያገኝ በማድረግ ረገድ አቢይ አገልግሎት እንደሚሰጡም በማስታወስ ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.