2016-07-13 16:15:00

በተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል የሚደረገው የጋራው ግኑኝነት ለማጎልበት


ከተለያዩ ኃይማኖቶች ጋር የሚደረገው የጋራ ውይይት የሚያነቃቃው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ምክትል ሊቀ መንበር ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ሚገል አንገል ኣዩስ ጉይሮት ግንቦት 23 ቀን 2016 ዓ.ም.  በቅድስት መንበር ይፋዊ ጉብኝት በማካሄድ ከቅዱስ አባታች ጋር ከተገናኙት የካይሮው አል አዝሃር መንበረ ጥበብ አቢይ ዒማም ፕሮፈሰር አህማድ አል ታዪብ ጋር ለመገናኘት እ.ኤ.አ. ከሐምሌ 13 ቀን 2016 ዓ.ም. በካይሮ ሐዋርያዊ ግቡኝት በማካሄድ ላይ መሆናቸው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ ይጠቁማል።

ከዓቢይ ኢማም ፕሮፈሰር አህማድ አል ታዪብ ጋር የሚደረገው ግኑኝነት ማሰናጃ እ.ኤ.አ. ሐምሌ 13 ቀን 2016 ዓ.ም. ከቀትር በፊት 11 ሰዓት ላይ በካይሮ ከሚገኙት በቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡክ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ብሩኖ ሙስሮ ተሸኝተው ከአል አዝሓር መንበረ ጥበብ የአበይት ቀደምት ምሁራን ምክር ቤት አባል የመንበረ ጥበቡ ከተለያዩ ኃይማኖቶች ጋር የሚደረገው ውይይት የሚከታተለው ማእከል ዋና አስተዳዳሪ ከሆኑት ከዶክተር ማህሙድ ሃሚድ ዛክዙክ ጋር የጋራ ውይይት ማካሄዳቸው የገለጠው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አክሎ፥ ይኽ የብፁዕ አቡነ ኣዩሶ ጉይሮት በካይሮ አል አዝሓር መንበረ ጥበብ የሚያካሂዱት ጉብኝት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በተለያዩ ኃይማኖቶች መካከል የሚደረገው የጋራ ውይይት የሚያነቃቃው ጳጳሳዊ ምክር ቤትና በአል አዝሓር መንበረ ጥበብ መካከል የጋራ ውይይት ዳግም ለማስጀመር ያላቸው ፍላጎት ለመግለጥና የጋራው ውይይት ዳግም ለማስጀመር የሚያበቃው መንገድ በጋራ መቀየስ የሚል ተልእኮ ያለው መሆኑ ያመለክታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.