2016-07-11 16:07:00

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ባላቸው የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይነት ሥልጣን ያስተላለፉት አዲስ ደንበ ሕግ


የቅድስት መንበር ሃብት የሚያስተስድርና የሚቆጣጠር አካል ያለው ልዩነት በግልጽ በማብራራት የሚያስቀምጥ አዲስ ሕግ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ባላቸው የቅድስት ጴጥሮስ ተከታይነት ልዩ ሥልጣን መሠረት ማጽደቃቸው የቫቲካ ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ሰርጆ ቸንቶፋቲ አስታወቁ።

የቤተ ክርስቲያን የሆነው ምድራዊ ሃብት ለመለኰታዊ ስግደትና አምልኰ፡ ተገቢና ቅንነት ለተካነው የካህናት ዕለታዊ ህይወት ማስተዳደሪያ ለግብረ ሐዋርያዊ አገልግሎት ለግብረ ሰናይ በተለይ ደግሞ በከፋ ድኽነት ለተጠቁት አገልግሎት የሚውል ነው የሚል ቅዉም ሃሳብ የተኖረበ አዲስ የቤተ ክርስቲያን ንብረት ማስተዳዳርና መቆጣጠር ጉዳይ የሚመለከት ቅዱስ አባታን ያጸደቁት አዲስ ሕግ ቤተ ክርስቲያን ያላት የገቢ ምንጭ ለዚህ እላይ ለገጠቀሰው ተግባር ማስፈጸሚያ የሚውል መሆኑ ባጸደቁት እዲስ ሕግ በጥልቀት እንዳብራሩት ቸንቶፋቲ ያመለክታሉ።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ቤተ ክርስቲያንን ለማደስ የወጠኑት እቅድ እግብ ለማድረስ የሚጠቀሙባቸው የተለያዩ ውስጠ ድርገቶች ማቆማቸው የሚታወስ ሲሆን፡ ካቆሙዋቸው ድርገቶች ውስጥ አንዱም እ.ኤ.አ. ከ 2014 ዓ.ም. አገግሎት መስጠት የጀመረው የኤኮኖኢ ጉዳይ የሚከታተል ምክር ቤት፡ የኤኮኖሚ ጉዳይ ጽሕፈት ቤትና የኤኮኖሚ ተቆጣጣሪ አካል የሚሉትን ለመጥቀስ ይቻላል።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ባጸደቁት አዲስ ሕግ የቅድስት መንበር የኤኮኖሚ ጉዳይ የሚከታተለው ጽሕፈት ቤትና የሐዋርያዊ መንበር ሃብት አስተዳዳሪ አካል ያለበት ኃላፊነት በመለየት ሆኖም በተቀናጀ መልኩ በመተባበር የሚሠሩ መሆናቸው በማብራራት ስለዚህ የቅድስት መንበር ንብረት ማስተዳደርና መቆጣጠር መካከል ያለው ልዩነት በሚገባ ለይቶ ማስቀመጥ ግድ ይሆናል።  የኃላፊነት መዛባትና መደናገር እንዳይኖርም ያግዛል። እያንዳንዱ እደየ ኃላፊነቱ ነገር ግን በመተባበር ቤተ ክርስትያንን ማገልገል የተጠሩ ናቸው። ተቆጣጠሪና ቁጥጥር የሚደረግበት አካል አንድ ሊሆን አይችልም። አስተዳዳሪው ተቆጣጣሪ ወይንም ተቆጣጣሪው ያስተዳዳሪ አካል ሊሆን አይገባውም፡ የሚል ሃሳብ በትክክል የተኖረበ አዲስ ሕግ መሆኑ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ቸንቶፋንቲ በማስከተል ከህዳሴው ጋር በተያዥነት ለሚነሱት ጥያቄዎች በቅርብ የሚመለከትና ውሳኔ የሚያስተላልፍ በልዩ አካል ሥልጣን ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ለብፁዕ ካርዲናል ቨላሲዮ ደ ፓውሊስ መሰየማቸው ያመለክታሉ።








All the contents on this site are copyrighted ©.