2016-07-08 16:27:00

የኢጣሊያ ብሔራዊ የቅዱስ ቁርባን ጉባኤ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ከመስከረም 15 እስከ መስከረም 18 ቀን 2016 ዓ.ም. በሚካሄደው የኢጣሊያ ብሔራዊ የቅዱስ ቁርባን ጉባኤ እንዲወክሉዋቸው የኢጣልያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር የጀኖቫ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ባኛስኮን መሰየማቸው ለኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ባስተላለፉት መልእክት እንዳሳወቁ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

የኢጣሊያው የቅዱስ ቁርባን ጉባኤ መርህ ቃል ቅዱስ ቁርባን፥ “የቤተ ክርስቲያን ሕያው ምንጭና ለመጻኢው ክብር ቃል ኪዳን ነው” የሚል መሆኑ ያስታወሰው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ፥ ይኽ የኢጣሊያ ብፁዓን ካርዲናላት ሊቀ ጳጳሳት ብፁዓን ጳጳሳት ካህናት ገዳማውያን ዓለማውያን ምእመናን የሚያሳትፍ በእቅድ የተያዘው ብሔራዊ የቅዱስ ቁርባን ጉባኤ ቅዱስ ቁርባን ዘወትር የሚከበር የሚሰገድለት የምኅረት የፍቅር ቃል ኪዳንና የፋሲካ ማእድ መሆኑ የሚያስገነዝብና ቤተ ክርስቲያንን በጋራ ለማነጽና ለመላ ዓለም ጥቅም ለመሻት የሚያበቃ የጋራ ትብብር እንዲኖረን ወንድማዊነት አሃድነት እንዲኖረን የምንመገበው ምግብ ነው ስለዚህ ለቅዱስ ቁርባን ስግደትና አምልኮ በቅዱስ ቁርባን ፊት የሚከናወን ያስተንትኖ ሥርዓት ያለው ጥልቅ መንፈሳዊነት በቃልና በሕይወት መስካሪያን እንሁን። ቅዱስ ቁርባን የክርስቶስ ወሰን የሌለው ፍቅርና ምኅረት ህላዌ ነው፡ በኣቢያተ ክርሲያን የሚታቀብና እኛን የሚያቅብ ከእርሱ ጋር ለመወያየትና እርሱም ከእኛ ጋር የሚወያይበት ህላዌ ሆኖ እያለ ብዙውን ጊዜ መኖሩን ችላ እንለዋለን ህልውናውን እናስተውል ያሉት ቅዱስ አባታችን ያስተላለፉት መልእክት፥ የእግዚአብሔር እናት በሆነችው በቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት እግዚአብሔር ሊካሄድ በተወሰነው የቅዱስ ቁርባን ጉባኤ መንፈሳዊ ጸጋዎችን ያብዛልን በሚል ጸሎት ማጠቃለላቸው አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.