2016-07-08 16:30:00

ብፁዕ ካርዲናል ሸንበርን፥ የፍቅር ሐሴት ዓዋዲ መልእክት ሂደቶች


የአውስትሪያ መዲና ለሆነቸው ለቪየና ከተማ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ክሪስቶፈር ሾንበርን ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ቤተሰብ ዙሪያ ከመከሩት ሁለቱ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶሶች የፍጻሜ ሰነድ ተንተርሰው ለመላ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የፍቅር ሓሴት በሚል ርእስ ሥር የለገሱት ድኅረ ሲኖዶስ ሐዋርያዊ ምዕዳን በማስመልከት በኢየሱሳውያን ማኅበር በሁለት ሳምንት አንዴ ከሚታተመው ካቶሊካዊ ስልጣኔ ከተሰየመው መጽሔት ጋር ያካሄዱት ቃለ ምልልስ ሎ ሶርቫቶረ ሮማኖ የተሰየመው የቅድስት መንበር ዕለታዊ ጋዜጣ በትላትና ኅትመቱ ጽማሬ ሃሳቡን ለንባብ ያበቃው ሲሆን፡ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በሐዋርያዊ ምዕዳን አማካኝነት በቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ  Familiaris consortio-ቤተሰብአዊ አንድነት እርሱም ቤተሰብ በወቅታዊው ዓለም  ዙሪያ ላይ በማተኮር እ.ኤ.አ. ህዳር 22 ቀን 1981 ዓ.ም. የደረሱት ሐዋርያዊ ምዕዳን በጥልቀት ሳያብራራ የተወዉን መለስ ብለው Amoris laetiti-የፍቅር ሐሴት በሚል ርእስ ሥር በደረሱት ሐዋርያዊ ምዕዳን አማካኝነት በጥልቀት በተሟይነት እንዳብራሩት ገልጠው፥ ብፁዕነታቸው የፍቅር ሐሴት የተሰየመውን ሐዋርያዊ ምዕዳን ለንባብ ለማብቃት የተካሄደው ዓውደ ጉባኤ በሳቸው መመራቱ የሚታወስ ሲሆን። ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 16 ቀን 2016 ዓ.ም. በግሪካዊቷ ደሴት ለስቦ የስደተኞች መጠለያ ሠፈር ሐዋርያዊ ጉብኝት ለማካሄድ በጉዞ ላይ እያሉ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ቃለ መጠይቅ የሰጡት መልስ Amoris laetiti-የፍቅር ሐሴት ሐዋርያዊ ምዕዳን በግልጽ አንኳር መልእክቱ ምን መሆኑ ለማስተዋል እንዳበቃቸው ገልጠው። ቅዱስ አባታችን ሁለቱን ሲኖዶሶችን በማማክከር እንደ እረኛ መምህርና የእምነት ሊቅነት ባላቸው ሥልጣን መሠረትም ያንን ያሻሚው ቅጥር መሻራቸው የሚገልጥ ሥልጣናዊ ትምህርት የሰጡበት ምዕዳን ነው።

ብፁዕ ካርዲናል ሾንበርን የመጽሔቱ ዋና አስተዳዳሪ ኢየሱሳዊ ማህበር አባል አባ አንቶኒዮ ስፓዳሮ ላቀረቡላቸው ጥያቄ የሰጡት መልስ በጠቅላላ 15 ገጽ አዘል ሲሆን እ.ኤ.አ. ሐምሌ 23 ቀን 2016 ዓ.ም. መጽሔቱ ለንባብ እንደሚያበቃው ሎሶርቫቶረ ሮማኖ ከወዱሁው ገልጦ፥ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የቤተ ክርስቲያን አነጋገር አድሰዋል። ይኽ ያነጋገር ህዳሴም ሐሴትና ተስፋ በተሰኘው የሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ውሳኔ መሠረት ያደረገ ቅዱስነታቸው በደረሱት ወንጌላዊ ሓሴት በተሰኘው ሐዋርያዊ ምዕዳን ዘንድ የተመለከተ መሆኑ ብፁዕ ካርዲናል ሾንበርን ገልጠው፡ የተለያየው ወቅታዊነት ያለው የቤተሰብ የተለያየው ተጨባጭ ሁነት፡ ችግሮቹንም ለማስተናገድ የቤተ ክርስቲያን ዝግጁነት የሚገልጥ መሆኑ ተበክረዋል። ስለዚህ ለማስተናገድ ዝግጁ መሆን የቤተ ክርስቲያን ሥርወ እምነታዊ ትምህርት ኃይል ያዳክማል ማለት ሳይሆን፡ ለሥርወ እምነት ትምህርት ኃይል ነው፡ ይኽ ማለት ደግሞ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ሥርወ እምነት የሚረዱት የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ምን ይላል በሚል እይታ አማካኝንት ነው። ስለዚህ ያ የተሰባው ቃል ማለት ነው፡ ትስብእቱ ትላንትና ላይ የታጠረ ሳይሆን ዛሬንም ጭምር የሚያካትት መጻኢን ከወዲሁ ነገር ግን በገናነት የሚያረጋግጥ ነው፡ ትስብእት በዛሬው ታሪክ ማንበብ። ቃል በገዛ እራሱ ላይ የተዘጋ ከዚያ ሕይወት ከሚለውጠው ጌታ ጋር ከሚደርገው ግኑኝንት የሚበሰረው አካል የተለየ የማይጨበጥ ብሥራት አይደለም፡ ምክንያቱም ቅዱስነታችው ሊኂቅ ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ እግዚአብሔር ፍቅር ነው በሚለው ዓዋዲ መልእክታቸው እንደሚሉትም ባለንጀራህ ፊት ዓይንን ጨፍኖ ማለፉ እግዚአብሔር ፊት ዓይነን መጨፈን ማለት መሆኑ በመርሳት የእምነት መሠረታዊ ትምህርት ዘንድ በሚደረገው ሪቂቅ ፍልስፍና አማካኘንት ግልጸትን ገርቶ ጠቅለል ያለ አስተያየቱን ለቁንጮዎች ወይን ለልህቆች ማቅረብ ይሆናል።

የፍቅር ሐሴት ሐዋርያዊ ምዕዳን ያንን ደንባዊና ኢደንባዊ የሚለው ፈረጅ ልቆ የሚሄድ ነው ይኽ ደግሞ ባንድ በኩል የተዋጣለት ሥርዓት የጠበቀና ቅን ተዛምዶ ያለው ቃል ኪዳንና ከዚህ ውጭ የሆነው ደግሞ ሥርዓት አልቦ ነው ብሎ የመግለጡ ዘልማዳዊ አገላለጥ የሚያስወግድ ነው፡ ስለዚህ ቅዱስ አባታችን ይኸንን ሃሳብ ሁላችን ተጓዦች ነን በሚለው ቃል ይገልጡታል። ይኽ ደግሞ ለኃጢኣት መጋለጥና የእግዚአብሔር ምኅረት የሚያበስር ሃሳብ ነው፡ ምክንያቱ ደንባዊውም ይሁን ኢደንባውዊ ሰው ሁሉ ለውጥ ያስፈልገዋል። ይኽ አባባል የተዛማጅ ባህል ውጤት ማለት አይደለም፡ ከተዛማጅ ባህል ጋር ምንም ዓይነት ግኑኝነትም የለውም። ቅዱስነታቸው የኃጢአት ተጨባጭነት አበጥረው የሚያወቁት ጉዳይ ነው፡ ደንባዊና ኢደንባዊ ሁነቶች እንዳሉ አልዘነጉትም፡ ሆኖም ወንጌል እግብር ላይ ለማዋል በሚል እይታ የሚመራ ሥልጣናዊ ትምርት ነው ያኖሩት እርሱም ወንጌል እንደሚለው ከእናንተ መካከል ኃጢአት የሌለበት በመጀመሪያ ድንጋይ ይወርውርባት (ዮሐ. 8፡7) ነው ሥርወ ሃሳቡ።

በመሠረተ ደንቡ ቃል ኪዳንና ባጠቃላይ ቅዱሳት ሚሥጢራት የሚመለከተው ሕገ እምነት ግልጽ መሆኑ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በሐዋርያዊ ምዕዳኑ ዘንድ ጥርት ባለ አነጋገር አስምረውበታል። ሕገ እምነት የማያሻማ ነው፡ በመሆኑም በሥርዓት ደረጃ ሲታይ የተለያዩና እጅግ የተወሳሰቡ ተጨባጭ ሁኔታዎች እንዳሉ እንገነዘባለን፡ ስለዚህ ቤተሰብ ጉዳይ በተመለከተ ከሲኖዶሱ ምንም ጠቅላል ባለ መልኩ ሁሉንም ጉዳዮች በችግር ላይ ያለውና የቆሰለውም ቤተሰብ ጭምር የሚመለከት እግብር ላይ የሚውል  ሕገ ቀኖናዊ ውሳኔ አልሰጠም። ስለዚህ ቅዱስ አባታችን ይኸንን የቤተሰብ ተጨባጭ ሁኔታ ግምት የሚሰጥ ለእያንዳንዱ የቤተሰብ ሁነት የሚመለከት ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ መለየት ያለው አስፈላጊነት ያሳስባሉ (የፍቅር ሐሴት ሐዋርያዊ ምዕዳን ገጽ 300)።

ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ቤተሰባዊ ማሕበርነት በሚል ርእስ ሥር በደረሱት ሐዋርያዊ ምዕዳን ቁጥር 84 የተቀበሉትን ምሥጢረ ተክሊል ለማዳን ስለ ሚታገሉት ጉዳይ ይናገራሉ። ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ከዚህ ጋር በማያያዝም እነዚይ ተኪልል ለማዳን የሚታገሉትና ምስሥጢረ ተኪል የተዉ በመቀጠልም ሕገ ቀኖናዊ የሆነውን ተኪሊል በማፍረስ ከባድ ኃጢኣት የሚፈጽሙ እንዳሉ በማስታወስ ከዚህ ጋር አያይዘው ዳግም የተጋቡት የልጆቻቸው ሕንጸት ጉዳይ ይናገራሉ።  ስለዚህ ምሥጢረ ተኪል ትርጉሙ የማያሻማ ቢሆንም ቅሉ ይኽ ምሥጢር የተሰራለት ሰው ግን ይለያያል ሁሉም አንድ አይደለም። ተጠያቂነቱም በዚሁ ፈረጅ የተለያየ በመሆኑም በክርስቶስና በቤተ ክርስቲያኑ መካከል ባለው የፍቅር ሱታፌ በማንበብ የእያናንዱ ቤተሰብ ሁኔታ በተናጥል በመመልከት ሊሰጥ የሚገባው ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ እንዲለይ ያሳስባሉ። ይኽ ነው ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በሐዋርያዊው ምዕዳናችው አማካኝነት የከፈቱት አዲስ በር። ይኽ ደግሞ የቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ቤተሰብአዊ አንድነት የተሰየመው ሐዋርያዊ ምዕዳን በጥልቀት የሚያብራራና የሚተነትን ነው ካሉ በኋላ በ 1994 ዓ.ም. የሥርወ እምነት ጉዳይ ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ በነበሩት በቅዱስነታቸው ሊኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ከሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ በፊት የእያንዳንዱ ቤተሰብ ውስጥ ያለው ችግር በተናጥል በመመልከት ቅዱሳት ምሥጢራት ይካፈል አይካፈል የሚለው ጉዳይ አበ ነፍስ የሚመለከት ኃላፊነት ነው በማለት የሚሰጠው ትምህርት ተፋተው ዳግም ቃል ኪዳን ያሰሩት የሚመለከት መሆኑ ባወጡት ሰንድ ተመልክቶ የሚገኘው ውሳኔ ጠቅለል አድርጎ ሁሉንም ባንድ ላይ መመልከት እንደማያስፈልግ የሚያሳስብ ሲሆን ይሕ ሃሳብ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ከገለጡት ሃሳብ ጋር ጥልቅ ግኑኝነት ያለው ነው እንዳሉ ሎ ሶርቫቶረ ሮማኖ ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.