2016-07-04 16:20:00

የአርጀንቲና ብፁዓን ጳጳሳት መግለጫ


አንዳንድ በአርጀንቲና ለምትገኘው የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን አባላትና ከቤተ ክርሲያኒቱ ጋር ግኑኝነት አላቸው የሚባሉት ሰዎች በምግባረ ብልሽት ተጠያቂዎች ናቸው ተብሎ የቀረበባቸው ክስ ምክንያት የአገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳ ምክር ቤት ጉዳዩ የሚያጣራው ፍርድ ቤት አለ ምንም ውጫዊ ኃይልና ማንኛውም ዓይነት ሥልጣን ተጽዕኖና በነጻ እውነት በመሻት ክብር ተመርተው እውነትና ፍትሕ በመመልከት ጉዳዩን እንዲያጣሩ አደራ የሚል ሃሳብ የተኖረበት መግለጫ ማስተላለፉ የቫቲካን ረዲዮ ጋዚጠኛ ኢዛበላ ፒሮ ሲር የዜና አገልግሎት ጠቅሰው ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋ።

የኅሊና ምርመራ አስፈላጊነት

ኢየሱስ ክርስቶስ ተከታዮች ይላሉ የአርጀቲና ብፁዓን ጳጳሳት ቅንነት የሚከተሉ እንደ ማንኛውም ዜጋ ፍትሃ ብሔር አክባርያን በመሆን ፍትሕና እውነተ እንዲረጋገጥ የሚተባበሩና ፍትሕ እውነት የሚያነቃቃ መሆን ይጠበቅባቸዋል ግዴታቸውም ነው፡ ስለዚህ ጉዳዩ በሚገባ ተጣርቶ ተገቢ ፍርድ እስከሚሰጥ ድረስ መጠበቅና ተጠርጣሪው ገና ከወዲሁ ተጠያቂ አድርጎ ፍርድ የመስጠትና ስም የማጥፋት ተግባር እንዳይኖ አደራ ብለው። በዚህ የምኅረት ዓመት ምክንያት የእግዚአብሔ ምሕረት እውነትና ፍትህ መሆኑ ሁሉ ለማስተዋል የሚያበቃው የኅሊና ምርመራ ያድርግ አደራ እዳንሉ ሲር የዜና አገልግሎት ያስራጨው ዜና የጠቀሱት ልእክት ጋዜጠኛ ፒሮ ይጠቁማሉ።

ምግባረ ብልሽትና ሙስናን እምቢ ማለት፡ ውሁድና ምሉእ ወንጌላዊነት ምስክርነት

ቤተ ክርስቲያን በየፍቅር ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ትታደስ ዘንድ የልብ ጥልቅ መንጻትና መለወጥ ሂደት ለቤተ ክርስቲያን አስፈላጊ መሆኑ የአርጀንቲና ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት በሰጠው መግልጫ በማሳሰብ ግላዊም ይሁን ማሕበራዊ ምሱናና ምግባረ ብልሽት ተቀባይነት የሌለው በተለይ ደግሞ ለተወሃደ ምሉእ ወንጌላዊ ምስክርነት ለወንጌላዊ ተልእኮና አገልግሎት ለተጠሩት በቤተ ክርስቲያን አባላት አማካኝነት ጭርሶ ሊፈጸም የማይገባው ተግባር ነው እንዳሉ የቫቲካን ረድዮ ልእክት ጋዜጠኛ ፒሮ ሲር የዜና አገልግሎት ጠቀስ ካጠንቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችሏል።








All the contents on this site are copyrighted ©.