2016-07-04 16:10:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፥ በዳካ የተፈጸመው ሽበራዊ ጥቃት ጸረ እግዚአብሔርና ጸረ ሰብአዊ ጨካኝ ተግባር ነው


በባንግላደሽ መዲና በሆነቸው በዳካ ከተማ እ.ኤ.አ. ሐምሌ 2 ቀን 2016 ዓ.ም.  አሸባሪያን በጣሉት ጥቃት ሳቢያ ለሞት የተዳረጉት በማሰብ ቅዱስ አባታችን ር.ኢ.ጳ. ፍራንቸስኮ የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊን ፊርማ የተኖረበት የሀዘን መግለጫ መልእክት አስተላልፈዋል ሲል የገለጠው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ ቅዱነታቸው የተጣለው ግብረ ሸበራው ጸረ እግዚአብሔና ጸረ ሰብአዊ ተግባር ነው በማለት ገልጠው፡ ለሞት የተዳረጉትን ለእግዚአብሔር ምሕረት አወክፈው የመቍሰል አደጋ ላጋጠማቸው ሁሉ ፈጣን መዳንን ተመኝተው፡ ለሟች ቤተሰቦች መጽናናቱን የቆሰሉትና በጠቅላላ ለአገረ ባንግላደሽን እንደሚጸልዩ ማረጋገጣቸው ያመለክታል።

ስለ ተጣለው ግብረ ሽበራ በማስመልከት የኢጣሊያ የሥነ ዓለም አቀፍ የጥናት ተቋም ሊቀ መንበር ስተፋኖ ሲልቨስትሪ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፥ የተጣለው ግብረ ሽበራ ተጠያቂ ነኝ ያለው ዳኢሽ የሽበራው ኃይል በሶሪያና በኢራቅ ተያይዞት የነበረው ወደ ፊት በመግፋ ከተሞችን የመቆጣጠር አቅሙ እየዳሸቀ በመጣቱና ብሎም ከሚቆጣጠራቸው ክልሎች ጭምር እያጋጠመው ባለው የጸረ አሸባሪያን ኃይል ጥቃት እየተመታ ለቆ ለመውጣት እየተገደደ በመሆኑ ምክንያት ይኸንን እየደረሰበት ያለውን ሽንፈት ለመበቀል በተለያዩ አገሮች የግብረ ሽበራ ተግባሩን እያፋጠነ መሆኑ ይኸው በዳካ የተጣለው ግብረ ሽበራ የሚያረጋግጠው ተጨባጭ አብነት መሆኑ ሲገልጡ፡ የኢሺያን ኒውስ የዜና አግልግሎት ዋና አስተዳዳሪ በርናርዶ ቸርቨለራ በበኩላቸውም ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፥ ዳኢሽ ያሸባሪያኑ ኃይል የሚሰነዝረው ግብረ ሽበራዊ ጥቃቱን በተለያየ ግንባር የሚያሰፋፋበት ሌላው ምክንያት ተከታዮች ለማግኘት የሚጠቀምበት ሥልት ነው፡ በባንግላደሽ የምዕራብ አገሮች የኤኮኖሚ ባለ ሃብቶች በአገሪቱ ያለው የሥራ ዋጋ ዝቅተኛነት ምክንያት በዚያች አገር መዋዕለ ንዋይ ሥራ ላይ የሚያውሉ ብዙ ናቸው፡ ይኽ የኤኮኖሚው ጉዳይ አሸባሪያኑ የገንዘብ ሃብት ሊያካብቱበት እንደሚችሉ በመገንዘብ ሲሆን። ስለዚህ በባንግላደሽ ጥቃት መጣል በቅድሚያ ተከታዮች ለማግኘት ያለመ የኤኖሚው ሂደት ለራስ ጥቅም ለማዋል በመሻትና በዚያች አገር የሚገኙትን የውጭ አገር የልማትና የኤኮኖሚ አውታሮችን አገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ለማስገደድ ነው ካሉ በኋላ ከዚሁ ጋር በማያያዝም በባንግላደሽ ከባለፉት አሥር ዓመታት ወዲሁ አክራሪ የቁራን ትምህርት ቤቶች እጅግ አየተባዙ መጥተዋል። ለዚህ ምክንያት አንዱ የአገሪቱ መንግሥት ብቃት ያለው ከዚያ የአክራሪያኑ የቁራን ትምህርት ቤቶች በጥራትም ሆነ በሕንጸት መርሃ ግብር እጅግ የላቀ የትምህርት አሰጣጥ እቅድ ካለው ድኽነት አንጻር ለማቅረብ ባለ መቻሉ ብዙ ወጣት በቀላሉ በተለያዩ በጋልፍ የምስልምና ሃይማኖት ተከታይ አገሮች በተለይ ደግሞ በሳውዲ አረቢያ በሚለገሰው የገንዘብ ሃብት ድጋፍ በሚገነቡት በቁራን ትምህርት ቤቶች እየተሳበ መጥቷል። እነዚህ ትምህርት ቤቶች ከምስልምና ሃይማኖት ውጭ የሌላ ሃይማኖት ተከታይም ይሁን እምነት የሌለው ሁሉ እንደ ጠላት እንዲታዩ የሚያደርጉ ናቸው፡ በሌላው ረገድ በአገሪቱ ያልነበረ ውጥረት እንዲጋባ የሚያደርግ አክራሪነት ለማስፋፋት ይሚቃጣ ተግባር ነው፡ ይኽ ደግሞ የተጣለው ግብረ ሸበራ ይመሰክረዋል በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋ።








All the contents on this site are copyrighted ©.