2016-07-01 16:25:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፥ ሥራ አጥነት ቤተሰብ ለአደጋ ከሚያጋልጡ ችግሮች ውስጥ እጅግ የከፋ ነው


እ.ኤ.አ. ሰኔ 30 ቀን 2016 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በአጸደ ቅዱስ ጴጥሮስ ይፋዊ የኢዮቤልዩ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምሮ በለገሱበት ዕለት እዛው አስተምህሮ ለመቀበል ከተገኙት ከውጭና ከውስጥ ከመጡት በብዙ ሺሕ ከሚገመቱት ምእመናን ውስጥ 7ኛው የሥራ ዓውደ በዓል ተሳታፍያን የሥራ መማክርት አባላንት ለወከሉት ሰላምታቸው አቅርበው፥ ለሰው ልጅ እርግጠኝነት የሚሰጥ ሥራ አስፈላጊ መሆኑ በማሳሰብ ቤተሰብ ለከፋ አደጋ ከሚያጋልጡ ችግሮች ውስጥ አንድ ሰብአዊ ልክነት የሌለው ሥራና የሥራ እጦት በቀዳሚነት ተጠቃሽ ናቸው፡ እናንተ የሥራና ሠራተኛ መማክርት አባላት ዋነኛው ተልእኳችሁ በሥራ ዕጦት ለሚሰቃየው እርዳታ መመጽወት ሳይሆን በብሔራዊ በኤውሮጳ አቀፍ በጠቅላላ በመንግሥታ መዋቅሮች፡ በኤኮኖሚው መስክ የኤኮኖሚ ተንከባካቢ አካላት በጥንቁቅነትና በአተኵሮ የተሟላና የሰብአዊ መብትና ክብር ማእከል የሚያደርግ ሥራ ለዜጎች ማረጋገጥና ሰብአዊ ልክነት ያለው ሥራ ማነቃቃት ነው ያሉትን ሃሳብ መሠረት በማድረግ የኢጣሊያ የሥራ መማክርት ማኅበር ምክር ቤት ሊቀ መንበር ማኢና ካልደኦነ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፥

ሥራ አጥነት እርግጠኝነትን ያገላል። ያንድ ቤተሰብ እርገጠኝነት ኑሮው ቤተሰብአዊነቱ ለአደጋ የሚያጋልጥ ነው ስለዚህ ሥራ እና ቤተሰብ ተያይዘው የሚሄዱ ናቸው፡ ለድጋፍ ማስተግበሪያ ተብሎ የሚወጠነው እቅድ በተረጅነት የሚያስቀር ሳይሆን ሥራ ለመፍጠር በሚያግዝ እቅድ ሊሸኝ ይገባዋል፡ ይኽ ሃሳብ ደግሞ ማኅበሩ የእጅ ድካም በሚል ርእስ ሥር በደረሰው መጽሓፍ ህልው የሥራና የኤኦኖሚ ሁኔታ የሚዳስስ መጻኢን በመመልከት የሚያብራራው ሃሳብ ነው፡ ብዙ አባላት ያሉት ቤተሰብና በሥራ አጥነት ለሚጠቃው ዜጋ የሚንከባከብ ኤኮኖሚያዊ እቅድ፡ የቤተሰብ ሕይወትና የሥራ ሂደት የማዛመድ እቀድ ያለው አስፈላጊነት ያንን ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ለሰው ልጅ እርግጠኝነት የሚሰጥ ሥራ አስፈላጊ መሆኑ በማሳሰብ ቤተሰብ ለከፋ አደጋ ከሚያጋጡ ችግሮች ውስጥ አንድ ሰብአዊ ልክነት የሌለው ሥራና የሥራ እጦት በቀዳሚነት ተጠቃሽ ናቸው፡ እናንተ የሥራና ሠራተኛ መማክርት አባላት ዋነኛው ተልእኳችሁ በሥራ ዕጦት ለሚሰቃየው እርዳታ መመጽወት ሳይሆን በብሔራዊ በኤውሮጳ አቀፍ በጠቅላላ በመንግሥታ መዋቅሮች፡ በኤኮኖሚው መስክ የኤኮኖሚ ተንከባካቢ አካላት በጥንቁቅነትና በአተኵሮ የተሟላና የሰብአዊ መብትና ክብር ማእከል የሚያደርግ ሥራ ለዜጎች ማረጋገጥ እንደሚገባቸውና ሰብአዊ ልክነት ያለው ሥራ ማነቃቃት ነው ያሉትን ጥልቅ የቤተክርስቲያን የማኅበራዊ ትምህርት የሚብራራው ምዕዳን ማእከል ያደረገ መጽሐፍ ነው ብለው ሥራ የሰው ልጅ ክብር መግለጫ እንጂ የሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ክብር የሚጥስ ሊሆን አይገባውም፡ ማንኛውም የሰው ልጅ ክብር ሰራዥ ተግባር ሥራ ብሎ መጥራት አይቻልም። የሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ክብር የሚጥስ ሥራ ሕገወጥ ከመሆኑም ባሻገር ለአገር ኤኮኖሚያዊ እድገት መሰናክልና የሕገ ወጥነት ተግባር ማስፋፊያ ነው የሚሆነው፡  ስለዚህ የሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ክብር የሚያከብር ሲባል ይኸንን ሁሉ የሚያጠቃልል ነው ብለው ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.