2016-06-29 15:32:00

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ለኦርቶዶክሳውያን ያስተላለፉት መልእክት


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ሰኔ 29 ቀን 2016 ዓ.ም. የላቲን ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የምታከብረው ዓመታዊ የቅዱሳን ጴጥሮስ ዎጳውሎስ በዓል ምክንያት በዕለተ ዋዜማው ቅድስት መንብር የገቡትን የቁስጥንጥንያ የውህደት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ልኡካን ተቀብለው የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ጠባቂ ቅዱሳን ጴጥሮስ ዎጳውሎስ የምህረትን የጸጋ ተመክሮ ዝካሬ የእነርሱ ሕይወት መጀመሪያ በኃጢኣት ቀጥሎ በምህረት የተመላከተ ሲሆን ይኽ ደግሞ ሁሉም በክርስቶስ የሚያምኑት የሚያገናኝ ተመክሮ ነው የሚል ማእከል ያደርገ ንግግር ማስደመጣቸው የቫቲካን ርዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ፍራንቸስካ ሳባቲነሊ ገለጡ።

ምንም’ኳ በሊጥርጊያዊ ባሕረ ሃሳብ በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንና ያንን የተገለጠው እውነት የአደናገጉ ዘዴ ልዩነት ያለ ቢሆንም ቅሉ ወሰን በሌለው የእግዚአብሔር ፍቅር ዙሪያ በሚኖረን ገጠመኝ አንድ ነን፡ የእግዚአብሔር ምሕረት ይላሉ ቅዱስ ኣባታችን፥ የሚያስተሳስርና እያደገ በመሄድ ላይ ያለው የጋራ ግኑኝንት እንደ ካቶሊክና ኦርቶዶክስ በአንድነት እጹብ ድንቅ የሆነውን የእግዚአብሔር ምሕረት በጋራ ለዓለም ሁሉ ለማወጅ የምንሻ ከሆን በመካከላችን የወዳሪነትና የተጻራሪነት የጥላቻ መንፈስ ማቀብ አይገባም። ከዚያ ግጭት ጥሎት ካለፈው የጥላቻ መንፈስ ነጻ የሚያወጣንና መንፈስ ቅዱስ ወደ ሚያመላክተው መጻኢ ክፍት እንድንሆን የሚያበቃን  የእግዚአብሔር ምህረት ነው እንዳሉ የገለጡት  የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ሳባቲነሊ እያይዘው፥

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በቅርቡ በግሪካዊቷ ደሴት ለስቦ ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ በርተጠለመዎስ ቀዳማዊና እንዲሁም ከኣቴንስና የመላ ግሪክ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ወቅዱስ ሄሮኒሞስ ዳግማዊ ጋር በመሆን በስደተኞች መጠለያ ሰፈር ያከናወኑት ሐዋርያዊ ጉብኝት መለስ ብለው በማስታወስ፥ በብዙ ሰዎች ፊት በወንዶች በሴቶችና በሕጻናት ፊት የሚነበበው ቀቢጸ ተስፋነት ያልተረጋገጠ ዕጣ ፈንታ ፊት መገናኘት የኖሩት  እየኖሩት ያለው ከባድና አሳዛኝ ገጠመኝ ሁሉ  መትሔ እንዲያገኝ ለማድረግ በቂ ኃይል የሌለህ መሆንህ ብታውቅም ማዳመጥና ቆም ብሎ በዚያ የብዙ ንጹሓን ስደተኞች ሕይወት ሰጥሞ በቀረበት የባህር ዳር ተገኝቶ አብሮ መጸለይ የተኖረበት ሁነት በእውነቱ ልብን በኃዘን የነካ ገጠመኝ ከመሆኑም ባሻገር በእውነቱ የወንድሞቻችንና እህቶቻችን ሰብአዊ መብትና ክብር ዋስትና ለማረጋገጥ የሚደረገው ጥረት አሁንም ብዙ መሰራት እንዳለበት ያመለክትልናል።

ለዚያ በደሴቲቱ የሚገኘው የተከዘውና ልቡ በኃዘን ለተነካው ስደተኛ ሁሉ ቅርብ በመሆን ብፅዕ ወቅዱስ በርጠለመዎስ ቀዳማዊና ብፁዕ ወቅዱስ ሔሮኒሞስ ዳግማዊ የሚሰጡት ሰብአዊና መንፈሳዊ ድጋፍ በእውነቱ አጽናኝ ነው። ለወንጌል ታዛዥ በመሆን ለድኾች ለተናቁት ላዘኑት ሁሉ ማጽናናት የካቶሊኮችና የኦርቶዶክሶች የጋራ ኃላፊነት ነው እንዳሉ አስታውቀዋል።

ቅዱስ አባታችን ያስደመጡት ንግግር፥  በጋራ ክርስቲያን መሆናችን እሳማኝነቱና ታማኝነቱን ለማውሳት ይኽ ዓይነቱ ኃላፊነት መወጣት ግዴታ ነው። ስለዚህም በካቶሊኮችና ኦርቶዶክሶች መካከል ያለው ማንኛውም ዓይነት ለሚሰቃየው ስብአዊ ፍጡር የሚሰጠው ተጨባጭ አገልግሎትና የሚደረገው ትብብር ሊበረታታ ይገባዋል ብለው ባለፈው እሁድ እ.ኤ.አ. 26 ቀን 2016 ዓ.ም. የተጠናቀቀው በክሬታ የተካሄደው የመላ ኦርቶዶክሳውያን አቢያተ ሲኖዶስ አስታውሰው ለቤተ ክርስቲያን ጥቅም የተትረፈረፈ ጸጋ የሚያሰጥ ይሁን በማለት ማጠቃለላቸው ሳባቲነሊ ገለጡ።








All the contents on this site are copyrighted ©.