2016-06-28 11:13:00

ር.ሊ.ጳ. ፍራንሲስ በአርመን ለሶውስት ቀናት ያካሄዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት አገባድዱ


ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በኤስያ ክፍለ ዓለም በአርመን ለሶውስት ቀናት ያካሄዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት አገባድደው ትላንትና አምሻቸው በሰላም ወደ ሐዋርያዊ መንበረ ቅዱስ ጰጥሮስ ተመልሰዋል። ቅደስነታቸው እና የኩላዊት አርመን ካቶሊኮስ ብጹዕ ወቅዱስ ካረኪን ዳግማዊ አርመን ውስጥ ያለውን ህያው ክርስትና ከሃሌ ኩሉ እግዚአብሔርን ካመስገኑ በኋላ የጋራ መግለጫ የሰጡ ሲሆን ሰላም በአክራሪነት ላይ ድል ይሆናል ለሰላማዊ አብሮ ለመኖር ለተለያዩ እምነቶች ክብር እንዲሰጣቸው አሳስበዋል።

ሁለቱ ብፁዓን አበው በሰጡት የጋራ መግለጫ፣ በአክራርነት የተነሳ የሚካሄዱ ሁከቶች ግጭቶች እና ማሳደድ እንዲገታ በአጽንኦት ጠይቀዋል ። በመካከለኛው ምስራቅ  እና  በተለያዩ የዓለም ክፍሎች  በሃይማኖት በፖሊቲካ እና ጐሳዊ ግጭቶች  የተነሳ  የሚገደሉ የሚሰቃዩ  እና  ለስደት የሚዳረጉ ህዝቦች  እንደሚያሳስባቸው ጠቁመው ዓለም አቀፍ ማሕበረ ሰብ  ህዝቦችን  እንዲረዳ ጠይቀዋል።

ርእሰ ሊቃነ  ጳጳሳት ፍራንሲስ እና የአርመን ካቶሊኮስ ብጹዕ ወቅዱስ ካረኪን ዳግማዊ በሰጡት  የጋራ  መግለጫ  በሚልዮኖች የሚቆጠሩን የዓለም ህዝቦች  ሰላም እና ፍትሕ  እየጠየቁ  መሆናቸው እና  ፍትሕ እና ሰላም እንድያገኙ የማጽነዋል። 

ከማኝኛውም ሃይማኖት የሚመጣ አክራርነት ተቀባይነት እንደሌለው እና ሃያምኖት የሰላም እንጂ የሁከት መሳርያ መሆን የለበትም ምክንያቱ  እግዚአብሔር በራሱ ሰላም ስለ ሆነ  ብጹዓን አበው  አሳስበዋል።

በአጠቃላይ  ህዝበ እግዚአብሔር  የሰላም  እና የእድገት መሳርያ እንዲሆን የሰላም ባህል እንድያዳብር ቅድስነታቸው እና የአርመን ካቶሊኮስ ብጹዕ ወቅዱስ ካረኪን ዳግማዊ  በሰጡት የጋራ መግለጫ ጠይቀዋል።

ናጎሮ ካራባክ  በተመለከተ በአርመን እና የአዘርባጃን መንግስታት መካከል ያለውን አለመጣጣም  እና ይህን ተከትሎ የተከሰተው ፍጥጫ በሰላማዊ  መንገድ መፍትሔ እንድያገኝ ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ እና የአርመን ካቶሊኮስ ብጹዕ  ወቅዱስ  ካረኪን ዳግማዊ  አሳስበዋል። ሰብአውነት ምህረት እና ርህራሔ  እንዲኖር  በተለያዩ ምክንያቶች  የሚፈልሱ  ስደተኞች  ሰብአዊ  ተገን  እንዲሰጣቸው ሰው በሌላ  ሰው ላይ መጨከን  እንደይማይገባ  ብጹዕን  አበው  ጠይቀዋል።

ይህ በዚህ እንዳለ ሆኖ   የቅድስት መንበር ቃል አቀባይ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በአርመን ያካሄዱት 14ኛ ሀገራት  አቀፍ  ሐዋርያዊ  ጉብኝት  ስኬታማ   ሐዋርያዊ ጉብኝት  መኖሩ  ለጋዜጠኞች   መግለጫ ሰጥተዋል። ርእሰ  ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በአርመን ያካሄዱት ሐዋርያዊ ጉብኝትለኤኩመኒዝም ለክርስትያን አንድነት የሚካሄደው ጥረት ጠቃሚ  ከመኖሩ ባሻገር ታሪካዊ ሐዋርያዊ ጉብኝት መኖሩ ቃል አቀባዩ አክለው ገልጠዋል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በአርመን ያካሄዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት የቅዱስ ወንጌል አገልጋይ በመሆን  መጀመርያ ክርስትና የተቀበለችው አረመን በደስታ  መጐብኘታቸው አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ  ገልጠዋል። 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.