2016-06-17 15:23:00

ቅዱስ አባታችን ለጎዳና ከያንያን (ኪነ ጠቢባን) የመልካም ዘር ዘሪዎች የውበት ጠቢባን ናችሁ


በዚህ በኵላዊት ቤተ ክርስቲያን እየተኖረ ባለው የምኅረት ዓመት ምክንያት እ.ኤ.አ. ሰነ 16 ቀን 2016 ዓ.ም. የጎዳና ከያንያን (ኪነ ጠበብት) ኢዮቤል መከበሩ ሲገለጥ፡ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ከሰባ ሺሕ የሚገመቱት የጎዳና ከያንያንን በጳውሎስ ስድስተኛ የጉባኤ አዳራሽ ተቀብለው መሪ ቃል መለገሳቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ፓውሎ ኦንዳርዛ አስታወቁ።

ቅዱስነታቸው ለኪነ ጠበብቶቹ በለገሱት ምዕዳን

የበዓል ጠቢባን

የበዓል የእጹብነትና የውሁብ ውበት ጥበበኞች በማለት ከያንያኑን የገለጡት ቅዱስ አባታችን፥ አነዚህ የጎዳና ከያንያን በሚያቀርቡት የጥበብ ወጤት የሆነው ትርኢት በእውነቱ የመልካም ዘር ዘሪዎች ናችው በማለት ከያንያኑን ገጠው፡ በዚህ በሚፈጽሙት ድንቅ ሥራ ምክንያትም ቅዱስነታቸው ከያንያኑን አመስግነው፥ የሚያቀርቡት ተጓዥ ትእይንት የመላ ዓለም ኅብረተሰብ ሃብታም የሚያደርግ ተስፋና እምነት በማነቃቃት መንፈስን እንዲመነጥቅ በማድረ በሰው ልጅ  በኑባሬ ባለው የተደናቂነት መንፈስ በማነቃቃትና በዚያ የሚያስደቅ ትርኢቶቻቸው አማካኝነትም ጤናማ የመዝናናት መንፈስ በመፍጠር ጥንቃቄና አቢይ ትኵረት በሚጠይቅ ትርኢቶቻቸው አማካኝነት የውበት መስካሪያን ናችሁ እንዳሉ ኦንዳርዛ አስታወቁ።

የእግዚአብሔር ምህረት አቅራቢያን

በዓልና ኃሴት የከያንያኑ መለያዎች ናቸው። ልዩ የኪነ ጥበብ ሃብት አላችሁ፡ በተለያየ ክልል እየተዘዋወራችሁ በምታቀርቡት ተጓዥ ትእይንት አማካኝነት ለሁሉም የእግዚአብሔር ፍቅር  ካለ ምንም አድልዎ ሁሉንም የሚያቅፉ እጆቹንና ምኅረቱንም ጭምር ለማድረስ ትችላላችሁ። ስለዚህ ተጓዥ ማኅበረ ክርስትያን በመሆን ክርስቶስን ለሁሉም እሩቅ ላሉትሁም ጭምር የምትመሰክሩ ለመሆን ትችላላችሁ እንዳኡ ኣንዳርዛ ገጠዋል።

ለተናቁት ቅርብ መሆን

ቅዱስ አባታችን የዚህ የጎዳና ከያንያን ኢዮቤል ያዘጋጀው የስደተኞችና የተጓዦች ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤትና የዚሁ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል አንቶኒዮ ማሪያ ቨሊዮን አመስግነው፡ በዚህ የጎዳና ከያንያን ኢዮቤል የተገኙትን ሁሉ አመስግነው ጦርነት እርሃብ ሰው ሠራሽና የተፈጥሮ አደጋ በሚከሰትባቸው የዓለማችን ክልሎች በመሄድ ለተናቁት ከኅብረተሰብ ክፍል፡ ወደ ተነጠሉትና በከፋ አደጋ ወደ ሚገኙት ድረስ በመሄድ ትርኢት በማቅረብ ደስታና ተስፋ ታነቃቃላችሁ፡ ይኽ ደግሞ ኪነ ጥበብ ክፍት ማንም የማያገል መሆኑ የሚመሰክር ነው። ስለዚህ በዚህ የምህረት ዓመት በበለጠም የምታቀርቡት ትርኢት ለሁሉም ለተናቁትና ለድኾች ሁሉ ክፍት በማድረግ የምትሰጡት አገልግሎ ነውና በእውነቱ የሚደነቅ ነው እንዳኡ ኦንድራዛ ያመለክታሉ።

ቤተ ክርስቲያን ለተጋዥና ለጎዳና ከያንያን ቅርብ ነች

ከያንያኑ በሚያቀርቡት ትርኢት በኅብረተሰብ መካከል ግኑኝነት መቀራረብ እንዲኖር የሚያበረታቱና የኪነ ጥበብ ውጤት ለተወሰነ የኅብረተሰብ ክፍል መብት ሳይሆን ከዚህ ውህበት ከሆነው ኪነ ጠቢብነት ከሚያፈራው ትርኢት ማንም የተገለለ እዳልሆነ ትመሰክራላችሁ ያሉት ቅዱስ አባታችን አያይዘው፥ እነዚህ ከያንያን ለተናቁት ቅርብ በመሆን በዚህ ኃዘንና ትካዜ በምሚፈራረቅበ ዓለም ሃሴት ለማነቃቃት በሚሰጡት አገልግሎት ምክንያት ቤተ ክርስቲያን ከጎናቸውና ቅርብ በመሆንም ሁሌ ትሸኛቸዋለች በማለት እንዳረጋገጡላቸው  የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ኦንዳርዛ ገለጡ።

በመጨረሻም ቅዱስ አባታችን የለገሱት ምዕዳን ሲያጠቃልሉ፥ ከያንያኑ እምነታቸውን እንዲንከባከቡ የቅዱሳት ምስጢራት ተሳታፍያን እንዲሆኑና ለልጆቸውም ለዚያ ለባለ እንጀራ በሚኖር ፍቅር አማካኝነት የሚገለጠው ለእግዚአብሔር የሚኖር ፍቅር በማነጽ እዲንከባከቡዋቸው አደራ በማለት፡ የክልሎች ካቶሊካውያን አቢያተ ክርስትያን ለጎዳና ከያንያን ቅርብ እንዲሆኑም በማሳሰብ፡ ቤተ ክርስቲያን ቅርባችሁ ናት እንድሉ የገለጡት የቫቲካን ረዲ ልኡክ ጋዜጠኛ ኦንዳርዛ እያይዘው ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራችነስኮ ጋር የተካሄደው ግኑኝነት ፍጻሜ በኋላ የጎዳና ከያንያኑ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የተለያዩ ትርኦቶች ማቅረባቸው ይጠቁማሉ።








All the contents on this site are copyrighted ©.