2016-06-13 15:41:00

ብራዚል


በብራዚል የሪዮ ደ ጃነይሮ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ኦራኒ ዥዋው ተምፐስታ እ.ኤ.አ. ሰኔ 10 ቀን 2016 ዓ.ም. በአንድ ሪዮ በሚገኘው የድኾች መኖሪያ ሰፈር ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ በማከናወን ላይ እያሉ በዚያ እሳቸው በነበሩበት ክልል በሚገኙት የወንጀል ቡድኖች መካከል ከተካሄደው በቶክስ ልውውጥ ከተሸኘው ግጭት ከነ ሹፌራቸው ከሞት አደጋ መትረፋቸው የሪዮ ደ ጃነይሮ ሰበካ ያስራጨው ዜና የጠቀሰው ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

ከአደጋው የተረፉት ብፁዕ ካርዲናል ተምፐስታ የዚህ አይነቱ በቶክስ ልውውጥ የተሸኘ ግጭት በከተሞች የሚታየው አደገኛው የወንጀል ቡድኖች የሚቀሰቅሱት ግጭት ሁሉ ያንድ ኅብረተሰብ  የማኅበራዊ ፖለቲካ የኤኮኖሚው ፖለቲካ የመስተዳድር ፖለቲካዊ ጉዳይም ሳይቀር ውድቅ መሆኑ የሚያስገነዝብ ነው፡ ስለዚህ ይኸንን የታመመው ኅብረተሰብ ዳግም ከወደቀበት ሰብአዊነት ልክነት ከሌለው ውድቀት እንዲላቀቅ ልቡ ለእግዚአብሔር ክፍት በማድረግ እንደ የወንጌል እሴት እንዲኖር የሚያግዘው ሕንጸት ማቅረብ ያስፈልጋ፡ ድኽነት ሥራ አጥነት የመሳሰሉት ሰብአዊ ማኅበራዊ ችግሮች ሁሉም ለተለያዩ ክብር ሰራዥ አደጋዎችና ለወንጀል ብድኖች መገልገያ መሣሪያ ለመሆን የሚገፉ ማኅበራዊና ሰብአዊ ችግሮች ናቸው፡ ስለዚህ ሁሉም እንደየ ኃላፊነቱ ኅብረተሰብ ለተለያዩ አደጋዎች ሊያጋልጡት የሚችሉት ችግሮች መፍትሔ በማፈላለጉ ረገድ እንዲተጋ አደራ እንዳሉ የሪዮ ደ ጃነይሮ ሰበካ ያስራጨው ዜና የጠቀሰው ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.