2016-06-11 13:15:00

ቅዱስነታቸው “የሰው ልጅ ከእግዚአብሔር ጋር ለመገኛኘት ከፈለገ በፍጥረት ጊዜ ወደ ነበረበት ሁኔታ መመለስ ይኖርበታል" አሉ።


የአንድ ክርስቲያን ሕይወት በሦስት ባሕሪያት ውስጥ ሊጠቃለል ይችላል እነዚህም አምላክን ለመቀበል "ተዘጋጅቶ" መጠበቅ፣ በትዕግሥት "በዝምታ" የእርሱን ድምጽ ማዳመጥ፣ “በመውጣት” ለሌሎች እርሱን ማወጅ መሆናቸውን በመገለጽ በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ካህናት፣ ደናግላን እና ምዕመና በተገኙበት ስብከታቸውን የጀመሩት ቅድሱ አባታችን ፍራንቸስኮ በኋጥያትህ ተጸጽተህ ከእግዚኣብሔር ጋር ያለህን ግንኙነት በአዲስ መልክ ለመጀመር ያስብክ ሰው ልትሆን ትችላለህ፣ ለእርሱ ሕይወት የተቀደሰ ወይም የተመረጠ ሰው ሆነህ ሊሰማህ ይችል ይሆናል፣ በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ውጤታማ አይደለም ከሚል አስተሳሰብ የመነጨ "ፍርሃት" ሊያጠቃህ ይችላል፣ እምነት ጀርባውን በሚስጥህ ወቅት ተስፍ ቆርጠህ “የመንፍስ ጭንቀት” ሊያድርብህ ይችላል በማለት ስብከታቸውን መጀመራቸውን የቫቲካን ጋዜጠኛ አሌሳንድሮ ዲ ካርሎስ ዘግቡኋል።

ይህንን ሁኔታ በጥልቀት ለማብራራት በማሰብ እና ከእዚህ አይነቱ ሁኔታ እንዴት መውጣት እንድሚቻል መንገድ ለመጠቆም በማሰብ ጥፍቶ የተገኘውን ልጅ ምሳሌ በማስታወስ ስብከታቸው የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህ ጠፍቶ የተገኘው ልጅ በተራበበት ወቅት እና የአሳማዎችን ምግብ ይበላ በነበረበት ጊዜ የመንፈስ ጭንቀት ውስጥ ገብቶ እንደ ነበር በማውሳት እና በእለቱ በተነበበው የመጀመሪያ ምንባብ ጋር በማቆራኘት ስለ ነቢዩ ኤሊያስ ታሪክ በተጠቀሰው ላይ ተመርኩዘው እነዚህ ሁለቱ ሰዎች አሉ ቅዱስነታቸው “ለ እምነታቸው ብዙ የታገሉ” በመጨረሻም ትግሉን “በአሸናፊነት” የተወጡ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ነቢዩ ኤሊያስ በቀርሜሎስ ተራራ ላይ ለብዙ ጣዖታት ፈታና ሳይበገር ሁሉንም አሽነፎ ነበር በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉ ቅዱስነታቸው ከዓላማው እንዳይሰናከል ከፍተኛ ትግል ከማድረጉም የተነሳ ደክሞ እና ተስፋን ቆርጦ በዛፍ ሥር ተቀምጦ ሞቱን ይጠባበቅ በነበረበት ወቅት እግዚአብሔር መላዕክቱን ልኮ “ተነስ እና ብላ!” በሚል ትዕዛዛዊ አነጋገር ለነቢዩ ኤሊያስ ማስተላለፉን አውስተዋል።

“የሰው ልጅ ከእግዚአብሔር ጋር ለመገኛኘት ከፈለገ በፍጥረት ጊዜ ወደ ነበረበት ሁኔታ  መመለስ ይኖርበታል፣ ይህም “መጽናት እና ከራሳችን መውጣት መሆኑን” ገልጸው “እግዚአብሔር የፈጠረን በራሱ መልክ፣ አምሳል እና እንዲሁም ከራሳችን እንድንወጣ መሆኑንም ጨመረው ገልጸዋል። “ወደ ፊት ሂድ! ምድርን አልማ፣ እንድትበለጽግ እና እንዲባዙም አድርግ. . . ‘ወደ ተራራው ሂድ በእዚያም እኔ በምገኚበት ተራራ ላይ ቁም። ኤሊያስም በተጠንቀ ለመቆም ወደ ተራራው ላይ ወጣ”’ በማለት አብራርተዋል።

ስለዚህም ከራስ መውጣት ማለት የእግዚአብሔርን ቃል ማዳመጥ ማለት ነው በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስ አባታችን “እንዴት ነው ጌታን በእርግጠኛነት ልገናኘው የምንችለው? በማለት ጥያቄን አንስተው በመጻሐፈ ነግሥት እንደ ተጠቀሰው ኤልያስ የመላዐኩን ጥሪ ሰምቶ እግዚአብሔርን ለመገናኘት እና በእግዚአብሔር ፊት ለመቆም ወደ ሆረብ ተራራ መውጣቱን እና በእዚያም ዓለቶች ሲናወጡ፣ መሬት ሲንቀጠቀጥ እና በመቀጠልም የሚንበለበል እሳት ማየቱን” ጨምረው ገልጸዋል።

“ታላቅ እና ኋይለኛ ነፋስ ተራሮቹ ሰነጣጠቀ፣ አለቶቹንም በእግዚአብሔር ፊት ብትንትናቸውን አወጣ፣ እግዚአብሔር ግን በነፋሱ ውስጥ አልነበረም” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “ከእሳቱ  ቀጥሎ ለስለስ ያለ ድምጽ ተሰማ ፣ በእዚያ ጸጥታ ውስጥ ግን እግዚአብሔር ነበረ” ካሉ ቡኋላ ጌታን ለመገናኘት ወደ ራሳችን ውስጥ በጸጥታ መግባት ያስፈልጋል በዚያም እግዚአብሔር ያናገረናል” በማለት ገልጸዋል።

“መልዐኩ በሦስተኛነት ለኤሊያስ ያቀረበለት ጥያቄ ‘ውጣ!’ የሚለው ነበር” ያሉት ቅዱስነታቸው “መልዐኩ የተላከው እርሱን ወደ ትክክለኛው ጎዳና እንዲመለስ እና በአደራነት የተሰጠውን ኋላፊነት እንዲወጣ” ለማስቻል መሆኑን የገለጹት ቅዱስነታቸው “ሁል ጊዜም ቢሆን በራስ ወዳድነት መንፈስ እና በምቾት እራሳችንን ገድበን  መኖር ሳይሆን የሚጠበቅብን ነገር ግን የጌታን መልዕክት ለሌሎች ለማዳረስ በርትተን መውጣት ያስፈልጋል ይህም ማለት ደግማ ሚሲዮናዊ መሆን ማለት ነው” ብለዋል።

በመጨረሻም “ ሁል ጊዜም ቢሆን ጌታን መፈለግ ይገባናል ምክንያቱም ሁላችንም ክፉ ጊዜያት፣ መንፍስን የሚያውኩ ወቅቶችን፣ እምነት የጎደለው ሕይወት፣ ጨለማ የሆነ ኑሮ፣ ከአድማስ ማዶ አሻግረን የማናይበት እና ተነስተን ለመቆም ያዳገተን ጊዜያት ምን እንደ ሆኑ እናውቃለን ነግር ግን ጌታ ለኤልያስ እንዳደርገው እኛንም በዳቦ ከመገበን ቡኋላ “ተንስ እና በፊቴ ቁም!” ወደ ፊት ተራመድ! ይለናል እና ጌታን ለመገናኘት ከፈለግን መቆም እና ወደ ፊት መራመድ ይጠበቅብናል” በማለት የእለቱን ስብከታቸውን አጠቃለዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.