2016-06-11 13:09:00

ቅዱስነታቸው "ግትርነትን የሚያሳዩ ሰዎች ካቶሊኮች ተብለው ሊጠሩ አይገባም ነገር ግን መናፋቃን ናቸው" ማለታቸው ተገለጸ።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ ዘወትር ጥዋት በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት መስዋዕተ ቅዳሴን ካህናት፣ ደናጋላን እና ምዕመናን በተገኙበት እንደ ሚያሳርጉ የሚታወቅ ሲሆን በግንቦት 2/2008 ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙ ስብከት እንደገለጹት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚኖሩ አንድአንድ ሰዎች “ይህ ነው እንጂ ያ አይደለም” ብለው ከመጠን በላይ የሆነ ግትርነት የሚያሳዩ ሰዎች ካቶሊኮች ተብለው ሊጠሩ አይገባም ነገር ግን መናፋቃን ናቸው ማለታቸው ተገለጸ።

ቅዱስነታቸው በስብከታቸው እንደ ገለጹት አንድአንድ የቤተ ክርስቲያን ሰዎች ከሚሰብኩት ስብከት በተቃራኒ በሚፈጽሙት ተግባራት ምክንያት እየተከሰተ ባለው ጉዳት ላይ ባጠነጠነው ስብከታቸው  እንደ ገለጹት እንደ እነዚህ ዓይነት ሰዎች እርስ በእርሳችን እርቅ እንዳንፈጽም እንቅፋት ከሚሆነው የግትርነት አስተሳሰብ እራሳቸውን ነፃ ማድረግ እንደ ሚኖርባቸው አሳስበዋል።

በእለቱ  ከማቴዎስ ወንጌል ከምዕራፍ 5: 20-26 በተነበበው እና ኢየሱስ ሐዋሪያቱን “የእናንተ ጽድቅ ከሙሴ ሕግ መምህራን እና ከፈሪሳዊያን ጽድቅ ካልበለጠ ወደ መንግሥተ ሰማይ ከቶም አትገቡም” ብሎ እንዳስጠነቀቃቸው በሚገልጸው ዐረፍተ ነገር ላይ ባጠነጠነው ስብከታቸው ቅዱስነታቸው አስረግጠው እንደ ገለጹት የክርስቲያን እውነታን መመልከት እና መገንዘብ አስፈላጊ ነገር መሆኑን አበክረው ገልጸው ኢየሱስ ከሕግ ባሻገር በመሄድ እና እግዚኣብሔርን እና ባልጄራችንን እንድንውድ  ስለሚያሳስበን ይህንን በመተላለፍ በወንድሞቹ ላይ በቁጣ የሚነሳ ማንኛው ሰው ፍርድ የገባዋል ብለዋል።

“ሌሎችን ለመሳደብ የሚረዳንን ቃላትን ለመፍጠር ብቃቱ አለን” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው መሳደብ በራሱ ኋጥያት እና የሚያበሳጭ ነገር በመሆኑ ምክንያት የወንድሞቻችን መብት መጋፋት እና በጥፊ እንደ መምታት ስለሚቆጠር መሆኑንም ጨምረው ገልጸው ለምሳሌም በመስዋዕተ ቅዳሴ ወቅት ብዙ ሕጻናት በቤተ ክርስቲያን በሚገኙበት ወቅት ተረጋተው እንዲቀመጡ የምንሰጠው ማሳሰቢያ ጥንቃቄ ልናደርግበት ይገባል ካሉ ቡኋላ ከአንድ ካህን፣ ጳጳስ ወይም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ይልቅ የአንድ ሕጻን ልጅ በቤተ ክርስቲያን መገኘት በጣም ደስ የሚያሰኝ ነገር ነው ብለዋል።

ኢየሱስ ግራ የተጋቡ ሕዝቦቹን ለመርዳት አሻግረን መመልከት እና ወደ ፊት መጓዝ እንዳለብን ያሳስበናል በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉ ቅዱስነታቸው በተመሳስይ መልኩም ክርስቶስ በእግዚኣብሔር ሕዝብ ላይ የራሳቸውን አስተምህሮ በማይከተሉ ክርስቲያኖች አማካይነት እየደረሰ የሚገኘውን ጉዳት እንድናጤን ያስተጠነቅቀናል ብለዋል።

“ስንት ጊዜ ነው እንደዚህ ዓይነት ነገሮች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሲከሰቱ የሰማነው? ስንት ጊዜ! በማለት ጥያቄዋችን ደጋግመው በማንሳት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ‘ያ ካህን፣ በካቶሊክ መሥሪያ ቤት የሚሥራው ያ ሰው ወይ ያቺ ሴት፣ ያ ጳጳስ ወይም ያ ሊቃነ ጳጳሳት እነርሱ የሚሉንን ነገር ሁሉ እነርሱ እንዳሉት የግድ እንተገብራለን!` ነገር ግን እነርሱ የሚፈጽሙት ተቃራኒውን ነው ይሉናል ካሉ ቡኋላ እንዲህ ዓይነቱ መጥፎ ምሳሌ ነው እንግዲህ የእግዚኣብሔርን ሕዝብ በማቁሰል እንዳያድጉ እና ወደ ፊት እንዳይራመዱ ጥፍሮ የሚያዛቸው” የዚህ ዓይነቱ አስተሳሰብ መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል።

የዚህ ዓይነቱ አስተሳሰብ “ነፃ አያደርጋቸውም በተጨማሪም እነዚህ ሰዎች የፈሪሳዊያን እና የሕግ መምህራንን ግትርነት በቀመሱበት ጊዜ እና ነቢያት ትንሽ ደስታን ለሕዝቡ ባመጡበት ወቅት፣ እነዚህ ፍሪሳዊያን እና የሕግ መምህራን አሳደዱዋቸው በተጨማሪም ገደልዋቸው፣ በአጠቃላይ ለነቢያት ምንም ዓይነት ቦታ አልነበራቸውም ነበር” ካሉ ቡኋላ ለዚህም ነበር ኢየሱስ ለፈሪሳዊያን “ንጹህ አየር ያመጡትን ነቢያትን ያሳደዳችሁት እና የገደላችሁት” ማለቱንም አስታውስዋል።

ቅዱስነታቸው ስብከታቸውን ለሚታደሙ ሁሉ በሰጡት ማሳሰቢያ እንደ ገለጹት ኢየሱስ ሁልጊዜም ርኅራኄ እና ወደ ፊት እንድንራመድ የሚያደርገንን ቅድስናን እንድንላበስ እና ሁልጊዜም ከራሳችን በላይ አሻግረን እንድንመለከት አደራ ይለናል ካሉ ቡኋላ ይህም አሉ ቅዱስነታቸው ይህም በሕግ ረገድ ከለን ግትርነት እና እኛን ከሚጎዳን ከእውነታ የራቀ አስተሳስብ ነፃ እንድንሆን ያደርገናል ብለዋል።

ኢየሱስ የእኛን ተፈጥሮ በሚገባ ስለሚረዳው በምንጋጭባቸው ወቅቶች ሁሉ እርቅን እንድንፈጥር ይጠይቀናል በማለት ስብከታቸው የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ኢየሱስ በተጭማሪም ተጨባጭ የሆነ እውነታን እንድንከተል ያስተምረናል ነገር ግን ብዙን ጊዜ “እኛ ፍጹም መሆን ባንችልም” እንኳ “የምንችለውን ያህል በመትጋት አለማግባባቶችን መፍታት” ያስፈልጋል ብለዋል።

“ይህ ነው ትክክለኛው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ተጨባጭ እውነታ! ቤተ ክርስቲያን በፍጹም ‘ወይም ይህን ወይም ያን` ብላ አስተምራን አታውቅም። ይህም የካቶሊክ አስተምህሮ አይደለም” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “ቤተ ክርስቲያን ለእኛ የምትለን `ይህንን እና ያንን`” የሚለውን በመሆኑ “ፍጽምናን ለማግኘት ጥረት በማድረግ ከወንድሞቻችን ጋር እርቅ መፍጠር እንዳለብን ነው” ብለዋል። “በፍጹም አትሳደቡ፣ ነገር ግን ተዋደዱ፣ አንድአንድ ችግሮች ካሉ ግጭት ሳይፈጠር በፊት አለምግባባታችሁን ፍቱ፣ ይህ ነው ተጨባጭ እውነታን የያዘ ካቶሊካዊነት” በማለት አጽኖት ሰጥተው ተናግረዋል።

ቅዱስነታችው በስብከታቸው ማገባደጃ ላይ እንደ ጠቀሱት ጌታችን ከግትርነት ባሕሪ እንድያላቅቀን እና ከራሳችን ባሻገር በመሄድ እንድናመልከው እና እንድናመሰግነው እንዲሁም እርስ በእርሳችን እርቅን መፍጠር እንድንችል በተጨማሪም መግባባትን መፍጠር እንድያስተምረን ልንለምነው ያስፈልጋል በማለት ስብከተ ወንጌላቸውን አጠናቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.