2016-06-10 15:16:00

በቅዱስ የምኅረት ዓመት፥ የኅሙማንና አካለ ስንኵላን ኢዮቤል


በዚህ በቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ውሳኔ መሰረ በኵላዊት ቤተ ክርስቲያ  እየተኖረ ባለው ቅዱስ የምኅረት ዓመት ምክንያት ሰኔ 12 ቀን 2016 ዓ.ም. እሁድ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በአጸደ ቅዱስ ጴጥሮስ በሚያሳርጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ የሚጠናቀቅ የኅሙማንና የአካለ ስንኵላን ኢዮቤል እ.ኤ.አ. ከሰኔ 10 ቀን 2016 ዓ.ም. በይፋ መጀመሩ የአዲስ አስፍሆተ ወንጌል ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ሪኖ ፊዚከላና ዋና ጸሓፊያቸው ብፁዕ አቡነ ኾሰ ኦክታቪዮ ሩኢዝ አረናስ በቅድስት መንበር የዜናን ኅትመት ሕንፃ በሚገኘው የኡጉባኤ አድራሽ ተገኝተው የሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የተከታተሉ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ደቦራ ዶኒኒ ገለጡ።

ብፁዕ አቡነ ፊዚከላ፥ እሁድ ቅዱስ አባታችን የአካለ ስንኩላንና ህሙማን ኢዮቤልይ ምክንያት በአጸደ ቅዱስ ጴጥሮስ በሚመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ ለመጀመሪያ ጊዜ በላቲን ሥርዓት የዕለቱ ወንጌል አካለ ስንኵላንና ኅሙማን በተለይ ደግሞ የአእምሮ ስንኩላንና የማስተዋልና የማሰላሰል ስብአዊ ባህርይ ጉድለት ያለባቸው ኅሙማን በቀላሉ ሊረዱት በሚችሉበት ዜዴ ማለትም በትያትር መልክ እንደሚቀርብ ገልጠው፡ መሥዋዕተ ቅዳሴ በቀጥታ በተለያዩ ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን አማካኝነት በተለያዩ ቋንቋ ትርጉም ተሸኝቶ እንደሚሰራጭና አንድ መስማት ተስኖ ያለባቸው ቋሚ ዲያቆን በምልክተ ቋንቋ አማካኝነት በሥርጭቱ የሚሳተፉም ሲሆን፡ በመንበረ ታቦቱ አጠገብ ቅድስት ድንግል ማርያም ፈውሰ ኅሙማን የተሰየመው ቅዱስ ምሥል እንደሚቀመጥም ማሳወቃቸው ዶኒኒ ጠቁመው፥ በዚህ አጋጣሚም ከተለያዩ አካለ ስንኩላን ቃለ ምስክርነት እንደሚደመጥ ያመለክታሉ።

ከተጀመረ ስድስተኛው ወሩ እያገባደደ ያለው ቅዱስ የምኅረት ዓመት ምክንያት ወደ ሮም የጎረፈው መንፈሳዊ ነጋዲያን ብዛት ዘጠኝ ሚሊዮን የደረሰ ሲሆን ሮማ የሚገኙትን አራቱ ጳጳሳዊ ባዚሊካዎችና እንዲሁም የፍቅር እመቤት ቅዱስ ሥፍራን ጨምሮ ዕለት በዕለት በቅዱስ በር ለማለፍ ሮማ የሚገባው መንፈሳዊ ነጋዲያን ብዛት ከፍ እያለ መምጣቱን የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ዶኒኒ አያይዘው፥ በዚህ እስከ እሁድ በሚዘልቀው የኅሙማንና እካለ ስንኩላን ኢዮቤል ተሳታፍያን መንፈሳዊ ነጋዲያን በቀላሉ ሊከታተሉት በሚችሉበት ዘዴ ትምህርተ ክርስቶስ እንደሚቀርብ ብፁዕ አቡነ ፊዚከላ የሰጡትን መልጫ ጠቅሰው ይጠቁማሉ።

ቅዳሜ እ.ኤ.አ. ሰኔ 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ምኅረት የኃሴት ምንጭ በሚል ርእስ ሥር በአጸደ ካስተል ሳንት’ኣንጀሎ በተለያዩ ቋንቋዎች መንፍሳዊ አስተምህሮ ከቀረበ በኋላ ወደ ከሰዓት በኋላ የመንፈሳዊና ባህላዊ መዝሙር ትርኢትና በታዋቂ የትያትርና የሙዚቃ ባለ ሙያዎችና ከያንያን ተመርቶ በተቀነባበረ መልኩ ለኅሙማንና ለአካለ ስንኩላን የተለያዩ የመዝናኛ ትርኢቶች እንደሚቀርብና በዝግጅቱ ለሚሳተፉት ኅሙማንና አካለ ስንኩላን የተለያየ አገልግሎት ሰጭ የበጎ አድራጎት ማኅበራ በሥፍራው ተገኝተው ዘርፈ ብዙ ግልጋሎት ይሰጣል ማለታቸውንም ዶኒኒ አስታወቁ።

ሮማ በሚገኙት ዓበይት ቤተ መዘክሮችና ታሪካውያን ሥፍራዎች የጉብኝት መርሐ ግብርና የተለያዩ የጤና ጥበቃ ሰጭ ግብረ ሠናይ ማኅበራትም በዚሁ በኅሙማንና አካለ ስንኩላን ኢዮቤል ተገኝተው በጤና ጥበቃው ዘርፍ በሮማው አቢይ በጀመሊ ሆስፒታል ሥር በሚተዳደረው የታዋቂው የሥነ ህክምና መንበረ ጥበብ ፕሮፈሰር ራፋኤሌ ላንዶልፊ የተመራ አገልግሎት እንደሚሰጥም ብፁዕ አቡነ ፊሲከላ ሲገልጡ፡ ዋና ጸሓፊያቸው ብፁዕ አቡነ ኾሰ ኦክታቪዮ ሩይዝ አረናስ በበኵላቸው ቤተ ክርስቲያን ከጥንት ጀምራ እንደ መሥራችዋ ለኅሙማን ለአካለ ስንኩላን ያላት አሳቢነት የሚመሰክር መርሐ ግብር ነው ብለው፥ ቅድስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እንደሚሉትም በኅሙማን በድኾች በተናቁት በተነጠሉት ከሚገለጠው ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር መገናኘትና በእነርሱ አካል የጌታ አካል መንካት የእምነት ጥያቄ ነው፡ ስለዚህ እነዚህ የጌታ አካል የሆኑትን ማገልገል ጌታን ማገልገል ነው እንዳሉ ዶኒኒ ያመለክታሉ።








All the contents on this site are copyrighted ©.