2016-06-09 10:44:00

ቅ.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ "በቃና ዘ ገሊላ ሰርግ ወቅት የቤተ ክርስቲያን እምነት ተወለደ" ማለታቸው ታወቀ።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት ማለትም በግንቦት 1/2008 ለጠቅላላ ሳምንታዊ አስተምህሮ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ከተገኙ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኚዎች ጋር የተገናኙ ሲሆን የእለቱን አስተምህሮ ከመጀመራቸው በፊት የ50ኛ ዓመት የጋብቻ ኢዩቤሊዩ ለማክበር በእዚያ የተገኙት ባለትዳሮችን እግረ መንገዳቸውን ተገናኝተው እና ሰላምታቸውን ባቀረቡበት ወቅት ለ50 ዓመታት አብረው መቆየታቸው “ግሩም ምስክርነት” መሆኑን በደስታ ገልጸውላቸዋል።

ቅዱስነታቸው በእለቱ ያሰሙት አስተምህሮ ትኩረቱን አድርጎ የነበረው ኢየሱስ በቃና ዘ ገሊላ የስርግ ሥነ-ሥርዓት ላይ የፈጸመውን የመጀመሪያ ተዐምር ላይ ሲሆን ይህ ኢየሱስ የፈጸመው ተዐምር አላማው ሰዎችን “ለማስደነቅ” ተፈልጎ ሳይሆን ነገር ግን በእዚህ ተዐምር አማካይነት ክርስቶስ፣ አብ ለእኛ ያለውን ፍቅር ለመግለጽ ፈልጎ መሆኑን አብራርተው እምነታችንን እንድናድስ የቀረበልን ጥሪ መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል።

“በቃና ዘ ገሊላ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ሁሉ የእርሱ ቤተሰብ አባል ሁነዋል፣ በቃና ዘ ገሊላ የቤተ- ክርስቲያን እምነት ተወለደ” በማለት አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህ በቃና ዘ ገሊላ የተፈጸመው ተዐምር “በቃላት እና በተግባር የክርስቶስን የብርሃን ምስጢር በመግለጽ የሐዋሪያቱን ልብ ለእምነት የከፈተ የመግቢያ በር ነው” ብለዋል።

የኢየሱስ በቃና ዘ ገሊላ ከሐዋሪያቶቹ ጋር አብሮ መገኘቱ የሚያሳየውን እድምታን በማስቀደም እና ትኩረታቸውንም በእዚሁ ሀረግ ላይ በማድረግ አስተምህሮዋቸውን የቀጠለት ቅዱስነታቸው "አንድ ልዩ ቤተሰብን" በመመስረት በእዚህም አማካኝነት "በነቢያት እንደተገለጸው ኢየሱስ የእግዚአብሔር ሕዝብ ሙሽራ አድርጎ እራሱን ይገልጻል" ብለው “በእዚህም ከእርሱ ጋር ያዋሀደንን ጥልቅ ግንኙነት በመግለጸ አዲስ የፍቅር ቃል ኪዳን መስርቱዋል” ብለዋል።

የእምነታችን መሠረት ምንድን ነው? ብለው ጥያቄን በማንሳት አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉ ቅዱስነታቸው ይህም ኢየሱስ በምህረት ተግባሩ ከእራሱ ጋር አቆራኝቶናል ካሉ ቡኋላ የክርስቲያን ሕይወት አሉ ቅዱስነታቸው “የክርስቲያን ሕይወት በጣም እንደ ሚዋደዱ ሁለት ሰዎች ዓይነት የእዚህ ታላቅ ፍቅር መልስ ነው” ብለው ሌሎች በቀጣይነት የሚከተሉ ነገሮች ሁሉ የእዚሁ ግንኙነት ድምር ውጤቶች ናቸው ካሉ ቡኋላ ቤተ ክርስቲያን በኢየሱስ ፍቅር የተሞላች የእርሱ ቤተሰብ ናት፣ የህም ቤተክርስቲያን በአደራ የተሰጣት ፍቅር ለሁልም ልበረከት እንደ ሚገባ” ገልጸዋል።

ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ የአስተምህሮዋቸው ቀጣይ ትኩረት የነበረው “የወይን ጠጅ የላቸውም እኮ! ባለችሁ በቅድስት ማሪያም ላይ ሲሆን “ውሃ ለሕይወት መሠረታዊ ነገር ነው፣ ነገር ግን የወይን ጠጅ የተትረፈረፈ በዓል መሆኑን የሚያሳት እና የደስታ መግለጫ” መሆኑን ገልጸው “የወይን ጠጅ የሌለበት ሰርግ ለሙሽሮች እንደ ውርደት ይቆጠራል፣ አስቡት እስቲ. . . አንድ ትልቅ ሰርግ በሻይ ተጀምሮ በሻይ ሲጠናቀቅ ለሙሽሮች ውርደት ነው” ብለዋል።

ማሪያም ለአገልጋዮቹ “እርሱ የሚላችሁን ነገር ሁሉ አድርጉ” ብላ በተናገርችሁ አረፍተ ነገር ላይ ተመስርተው የወይን ጠጅ ለበዓል ድምቀት አስፈላጊ ነገር ነው በማለት የሁለተኛውን ክፍል አስተንትኖዋቸውን  የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህም  በወንጌል ውስጥ የተጠቀሰ የማሪያም የመጨረሻ ቃሉዋ እና ለእኛ ለሁላችን እንደ ወርስ የተሰጠን ዐረፈፍተ ነገር ነው” ካሉ ቡኋላ ዛሬም ቢሆን እናታችን ማሪያም ለሁላችን “እርሱ የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ” ብላ በውርስ የተወችልን መልካም ነገር ነው ብለዋል።

በእዚህ የሰርግ ግብዣ ላይ “በእርግጥ አዲስ የትዕዛዝ ቃል ኪዳን ለእግዚአብሔር አገልጋዮች ተሰቱዋል፣ የሄውም ለቤተ ክርስቲያን የተሰጠ አንዲስ ተልዕኮ ነው” በማለት አስተምህሮዋቸውን የቅጠሉት ቅዱስነታቸው የእግዚአብሔር አገልጋይ ማለት እርሱ የሚለውን ማዳመጥ እና በተግባር ማሳየት ማለት ነው ካሉ ቡኋላ በጣም ቀጭን ትዕዛዝ ቢመስልም ቅሉ የኢየሱስ እናት ክርስቲያኖች በሕይወታቸው እንዲተገብሩት ያስተላለፈችሁ  በጣም መሰረታዊ ትዕዛዝ መሆኑን አክለው ከገለጹ ቡኋላ የመላዕከ እግዚአብሔርን ጸሎት ከምዕመናን ጋር ደግመው እና ቡራኬን ሰጥተው የእለቱን አስተምህሮዋቸውን አጠናቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.