2016-06-08 16:18:00

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. መልእክት ለአርጀንቲናው ብሔራዊ የቅዱስ ቁርባን ጉባኤ


እ.ኤ.አ. ከሰኔ 16 እስከ ሰኔ 19 ቀን 2016 ዓ.ም. የአርጀንቲና ሁለት መቶኛው የነጻነት በዓል ከሚከበርበት ቀን ጋር በማያያዝ በሳን ሚገል ደ ቱክማን ሊካሄድ ወደ ተወሰነው አስራ አንደኛው ብሔራዊ የቅዱስ ቍርባን ጉባኤ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ፊርማ የተኖረበት መልእክት ማስተላለፋቸው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አስታወቀ።

በዚህ በሚካሄደው ብሔራዊ የቅዱስ ቍርባን ጉባኤ ቅዱስነታቸው እሳቸውን ወክለው እንዲሳተፉም የብፁዓን ጳጳሳት ጉዳይ ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ልኂቅ ኅየንተና ጳጳሳዊ የላቲን አመሪካ ጉዳይ ተንከባካቢ ድርገት ልኂቅ ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ጆቫኒ ባቲስታ ረ መሰየማቸው የጠቆመው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አክሎ፥ የአርጀንቲና ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የቅዱስ ቁርባን ጉባኤውን በሳን ሚገል ቱክማን ከተማ ለማካሄድ ሲወስን አለ ምክንያታ እንዳልሆነም ሲያብራራ ከተማይቱ እ.ኤ.አ. ሐምሌ 9 ቀን 1816 ዓ.ም. የሪዮ ደ ፕላታ ውህድነት ራስ ገዝ ክልል በሚል መጠሪያ ከስፓንሽ ቅኝ ግዛት ነጻ ከወጣችበት ታሪካዊ ቀን ጋር በማገናኘት መሆኑ ገልጦ፡ ጉባኤው “የታሪክ ንጉሥ ኢየሱስ እንተን እንሻለን” የሚል ሲሆን ይኽ መርህ ቃል “ኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ የሕይወት እንጀራና ለህዝባችን ሱታፌ” በሚል ታካይ መርሆ የሚሸኝ መሆኑም ያመለክታል።

ቅዱስነታቸው በዚህ የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ፊርማ በተኖረበት በአርጀንቲና የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ኣቡነ ኾሴ ማሪያ አራንሰዶ ስም በአርጀንቲና ለምትገኘው ካቲሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ባስተላለፉት መልእክት፥ የተወዳጇ አርጀንቲና ምእመናን ያንን ዕለት በዕለት እምነትን ወንድማማችነትን  እንዲሁም ስለ ድሆች ለመቆም የሚደረገው አገልግሎትን ለሚያጎለብት ቅዱስ ቍርባን ያለው ፍቅር በጥልቀት መኖርና ማጤን እንዲቀጥልበት አደራ በማለት ለመላ አርጀንቲና የዚያች ታላቅ አክብሮትና ፍቅር ያላቸው የቅድስት ድንግል ማርያም ዘ ሉኻን እናታዊ ጥበቃ መማጸናቸው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.