2016-06-07 13:00:00

ቅ.አ. ፍራንቸስኮ ጳጳሳትን ከሹመታቸው ልያስወግድ የሚችል አዲስ ሕግ አወጡ


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በግላቸው አዲስ ባቋቋሙት አቃቢ-ህግ አማካይነት ብጹዐን ጳጳሳት በግለሰቦች  ወይም በማኅበርሰቡ ላይ በቸልተኝነት እራሳቸው የፈጸሙት፣ ወይም ሌሎች በሰዎች ላይ በፈጸሙት ጥቃት ምክንያት የደረሰውን ከፍተኛ በደል የሚሸሽጉ ጳጳሳትን የሚቀጣ እና አሁን ካለው ሕገ ቀኖና ጋር መሳ ለመሳ በማገልገል ጳጳሳቱን ከሹመታቸው ማስወገድ የሚችል የመቅጫ ህግ አዲስ በጻፉት ሐዋሪያዊ መልዕክታቸው ላይ  ማውጣታቸው ተገለጸ።

Come una madre amorevole” (እንደ አንድ አፍቃሪ እናት) በሚል አርዕስት ሥር የጻፉት ሐዋሪያዊ መልዕክታቸው ላይ በግልጽ እንደ ተቀመጠው “በህጻናት ወይም ለጥቃት ተጋላጭ በሆኑ አዋቂ ሰዎች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ጳጳሳት ተግተው አለመቃወማቸው በእራሱ ለከፍተኛ ቅጣት የሚዳርግ በቂ” መረጃ መሆኑም ተጠቅሱዋል።

የእዚህን ሐዋሪያዊ መልዕክት ጠቅላላ ይዘት በጣሊያነኛ ቋንቋ እዚህ ታገኛላችሁ።

የቫቲካን የሕትመት ክፍል ኋላፊ የሆኑት አባ ፈሬድሪኮ ሎምባርዲ የወጣውን አዲስ ህግ የአፈጻጸም ሂደቶችን ባብራሩበት ወቅት እንደ ገለጹት “አዲስ የወጣው ሐዋሪያዊ መልዕክት ለህፃናት እና ተገላጭ ለሆኑ አዋቂ ሰዎችን ከጥቃት ለመከላከል በንቃት መጠበቅ አስፈላጊ እንደ ሆነ እና በተለይም ደግሞ ጥቃቱን ለመቃወም ጳጳሳት ‘ልዩ ትጋት” እንዲያሳዩ የሚያሳስብ መሆኑን ገልጸዋል። በመቀጠልም አባ ሎምባርዲ እንደገለጹት “ይህ ህግ በህፃናት ላይ ወይም ለጥቃት ተጋላጭ በሆኑ አዋቂ ሰዎች ላይ የሚደረሰውን ወሲባዊ ጥቃትን ችላ የሚሉ ጳጳሳትን ጨምሮ ሁሉንም የቤተ ክርስቲያን ኋላፊዎችን ከሹመታቸው ለማንሳት ‘ከባድ ምክንያቶች’ መሆናቸውን ጨምሮ ገልጸዋል።

አዲስ የወጣው ሐዋሪያዊ መልዕክት ቀደም ሲል የነበረውን የቤተ ክርስቲያ አጠቃልይ ህገ-ቀኖና እና የምስራቃዊ አብያተ ክርስቲያናት ህገ-ቀኖናን የአፈፃጸም ቅደም ተከተል ያጠቃለለ መሆኑን የገለጹት የቫቲካን የህትመት ክፍል ኋላፊ አባ ፈሬድሪኮ ሎምባርዲ ይህ አዲሱ ሐዋሪያዊ ደብዳቤ የቸል ባይነትን ጉዳዮችን የሚመለከት በመሆኑ  እንደ የወንጀለኛ መቅጫ ስነ-ስርዐት ሳይሆን ሊወሰድ የሚገባው ነገር ግን ለተፈጸሙት ጥቃቶች ስለ ሚወሰደው እርምጃ የሚያወሳ መሆኑ ገልጸዋል።

 በእዚህ ምክንያት ጥቃት ፈጻሚዎች ሁሉ የመቅጫ ሂደት ማለፍ የሚገባው በተለያዩ ጳጳሳዊ ምክር ቤቶችን ሲሆን እነዚህም ምክር ቤቶች፣ የስብከተ ወንጌልን ጉዳይ የሚመልከተው ጳጳሳዊ ምክር ቤት፣ የምስራቃዊ አብያተክርስቲያናትን የሚምለከተው የጳጳሳዊ ምክር ቤት፣ የመናንያን ሕይወትን የሚምለከተው ጳጳሳዊ ተቁዋም እና እንዲሁም የእምነት ዶክትሪንን በሚመለከተው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ምትክ የሐዋሪያዊ ሕይወትን የሚመልከተው ጳጳሳዊ ማህበርን ያካተተ ሂደት እንደ ሚከተልም ጨምረው ገልጸዋል።

Come una madre amorevole” (እንደ አንድ አፍቃሪ እናት) በተሰኘው እና በቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ የተጻፈው ሐዋሪያዊ መልዕክትን ዋቢ በማድረግ በሁለት ዋና ዋና ነጥቦች ላይ ትኩረትን ባደረገው መግለጫቸው የቫቲካን የህትመት ክፍል የሆኑ አባ ፈሬድርኮ ሎምባርዲ እንደገለጹት በቀዳሚነት ሊወሳ የሚችለው አንኳር ነጥብ “የትጋት ማነስ” የሚለው መሆኑን አውስተው ምንም እንኳን አንድ ጳጳስ ከፍተኛ የሚባል የሥነ-ምግባር ግድፈት ባይታይበትም ቅሉ የእርሱ ትጋት ማነስ በፈጠረው ክፍተት ምክንያት በተፈጠረው ጥቃት ብቻ ከጵጵስናው ሊነሳ እንደ ሚችል ገልጸዋል።

ሁለተኛው አንኳር የሆነው ነጥብ በሕፃናት ላይ የሚደረሰው የወሲብ ጥቃት ነው ያሉት አባ ሎምባርዲ ጥቃቱን ለማስቀረት የሚያስችል “የትጋት ማነስ” በእራሱ ከባድ እና በቂ ማስረጃ ነው ብለው በተለይም በሕፃናት ላይ የተፈጸመ የወሲብ ጥቃትን የተመለከተ ከሆነ አንድ ጳጳስ ከጵጵስናው እንዲነሳ በቂ ምክንያት ሊሆን ይችላል ካሉ ቡኋላ በእዚህ ረገድ ለሚደርጉ ማነኛውም ዓይነት ውሳኔዎች ተፈጻሚ ከመሆናቸው በፊት በቅዱስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት መጽደቅ እንደ ሚኖርባቸው እና በሐዋሪያዊው መልዕክት ላይ እንደ ተገለጸውም የመጨረሻ ውሳኔ ከመደረጉ በፊት ሁኔታውን በመመርመር ሂደት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስቱን የሚያግዝ ጳጳሳትን እና ካርዲናሎችን ያካተተ አንድ  የሕግ ቡድን አባላት  መቋቋም እንደ ሚኖርበትም በሐዋሪያዊ መልዕክቱ መካተቱንም አባ ሎምባርዲ ጨምረው ገልጸዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.