2016-06-01 15:41:00

በአገረ ደሞክራሲያዊት ረፓብሊክ ኮንጎ ሰላም እንዲረጋገጥ የአገሪቱ ካቶሊክ ምእመን ጥሪ


እ.ኤ.አ. ሰነ 30 ቀን 2016 ዓ.ም. በደሞክራሲያዊት ረፓብሊክ ኮንጎ የሚከበረው ብሔራዊ የነጻነት ቀን ምክንያት የአገሪቱ ካቶሊካውያን ምእመናን ሐዋርያዊ ምክር ቤት ባወጣው  ይፋዊ መግለጫ፥ በአገሪቱ የሚካሄደው የእርስ በእርስ ግጭት እንዲገታ ያለመ ጥሪ ለአገሪቱ የፖለቲካ ዓለም ብዙኃንን ኃዳጥን የፖለቲካ ሰልፎች የአገሪቱ እድገትና ብልጽግና የሚገታ የህዝብ በሰላም መኖር ጥያቄው እንዲከበር የእርስ በእርስ ግጭት መስፋፋት ምክንያት የሆነው የትጥቅ ትግል ሁሉ እንዲገታና በአገሪቱ የሚካሄደው የርእሰ ብሔር ምርጫ በተረጋጋና በሰላማዊ መገድ እንዲረጋገጥ ጥሪ ማቅረቡ የማኅበሩ ደረ ገጽ አስታወቀ።

ውይይትና ነጻነት

ብሔራዊ የነጻነት ቀን መሠረታዊው የሰብአዊ መብትና ክብር እንዲከበር ግድ የሚል ብሔራዊና ዜጋዊ ኃላፊነትና ተጠያቂነትም ጭምር የሚያበክር ከመሆኑም ባሻገር ለአገርና ሕዝብ እድገት መሠረት የሆነው የጋራው እሴት የሚያነቃቃ መሆኑ ያብራራው የአገሪቱ ካቶሊካውያን ምእመናን ሐዋርያዊ ምክር ቤት መግለጫ አክሎ፥ ምክር ቤቱ ለአሪገቱ ርእሰ ብሔር ጆሰፍ ካቢላ የፖለቲካ እሰረኞች ነጻ እንዲልቀቁና ብሔራዊ ፖለቲካዊ ውይይት የሚደግፍ ስነ አእምሮአዊና ግብረ ገባዊ ቅምደ ሁነት እዲፈጠርና አገር የሁሉም በሁሉም አማካኝነት እንደየ ኃላፊነቱ ትገነባ ዘንድ እድሉ ለሁሉም በእኩል እንዲረጋገጥ በማድረጉ ረገድ እንዲተጉ ጥሪ በማቅረብ፡ የሁሉም ዜጋ እኩልነት በማረጋገጥ እውነት በመከላከል ፖለቲካዊ ልዩነትና አለ መግባባት በውይይት ብቻ እንዲፈታ ማድረግ እንዲቻልም በዚሁ ሰላማዊ ሂደት መንፈስ ቅዱስ የሁሉም ዜጎች የፖለቲካና የመንግሥት አካላት አእምሮ ያብራ በሚል ጸሎት ያስተላለፈው መልእክት ማጠቃለሉ የማኅበር ይፋዊ ድረ ገጽ ይጠቁማል፡








All the contents on this site are copyrighted ©.