2016-05-31 15:14:00

ቅዱስነታቸው በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ከመላው ዓለም የተውጣጡ ቋሚ ዲያቆናት በተገኙበት መስዋዕተ ቅዳሴን አሳረጉ።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቼስኮ ቅዱስ ልዩ የምህረት ዓመትን ለማክበር እና እንዲሁም በሁለተኛ የቫቲካን ጉባሄ ሕዳሴ የተደረገበት የቍዋሚ ዲያቆናት አገልግሎት 50ኛ ዓመትን ኢዩቤሊዩ ለሶስት ቀናት ማለትም ከግንቦት 19-21/2008 ለመዘከር ከመላው ዓለም የተውጣጡ ቍዋሚ ዲያቆናት እና ቤተሰቦቻቸው ወደ ቫቲካን እንዲመጡ ተጋብዘው የነበረ ሲሆን ጥሪውንም በማክበር በግንቦት 21/2008  በቫቲካን በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ በቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ መሪነት የተካሄደውን ስርዓተ ቅዳሴ መካፈላቸው ተገለጸ።

በእለቱ ቅዱስ አባታችን ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት “አገልጋይ ሰው ጊዜዬን ለእራሴ ብቻ እጠቀማለሁ የሚለውን ሐስተሳሰብን አስወግዶ ትርፍ ጊዜውን እንኳን ሳይሰስት ለሌሎች ይሰዋል ምክንያቱም ጊዜ የእራሱ ሳይሆን ከእግዚአብሄር የተሰጠው ፀጋ መሆኑን ስለምያውቅ መልሶ ለእርሱ በመስዋዕትነት ያቀርበዋል” በማለት ስብከታቸውን የጀመሩት ቅዱስነታቸው የእዚህን ዓይነት አስተሳሰብ ስናዳብር ብቻ ነው ፍሬያማ መሆን የምንችለው ብለዋል።

ቅዱስነታቸው አንድ ዲያቆን መልካም እና ታማኝ አገልጋይ መሆን ይኖርበታል በሚል ሐሳብ ዙሪያ ትኩረቱን ባደረገው ስብከታቸው  እንደ ገለጹት “አንድ የምያገለግል ሰው የእራሱ አጀንዳ ባሪያ መሆን የለበትም ነገር ግን ያልተጠበቁ ነገሮች በምያጋጥሙበት ወቅት ይህንን ሁኔታ ለመቋቋም ዝግጁ የሆነ፣ ለወንድም እና እህቶቹ ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ ተገኝ የሆነ እና ለአምላክ የማያቋርጥ አስገራሚ ስጦታ እራሱን ክፍት አድርጎ የሚጠብቅ” ሊሆን ይገባዋል ብለዋል።

ቅዱስነታቸው በስብከታቸው እንዳሳሰቡት አስሮ የያዛችሁን የጊዜ ሰሌዳ ስንሰለት በጥሱ ወይም ችላ በሉት ካሉ ቡኋላ በቤተ ክርስቲያን እና በቁምስናዎች በር ላይ የጊዜ ሰሌዳ በመለጠፉ ደስተኛ አይደለውም ካሉ ቡኋላ ምክንያቱም አሉ ቅዱስነታቸው ምክንያቱም ይህ የጊዜ ሰሌዳ የምያሳየው የቤተ ክርስቲያን በሮች ሁል ጊዜ ክፍት እንዳልሆኑ እና ካህናት፣ ዲያቆናት ወይም ምዕመናን ሰዎችን ለመቀበል ሁል ጊዜ ዝግጁ እንዳልሆኑ ስለ ሚያመለክት ነው ብለዋል።

“አንድ አገልጋይ” አሉ ቅዱስነታቸው “የእራሱን የጊዜ በር ክፍት ማድረግን ያውቃል እንዲሁም በማይሆን ሰዓት እንኳን በሩን ለምያንኳኩ ሰዎች እየሠራ የሚገኘውን መልካም ነገር ወይ ደግሞ (እረፍት ሊሆን ይችላል) ትቶ በዙሪያው ለሚገኙ ሰዎች እራሱን ክፍት የሚያደርግ ልሆን ይገባል” ማለታቸው ተወስቱዋል።

“ውድ ዲያቆናት” አሉ ቅዱስነታቸው “ለሌሎች ሁል ጊዜ የዝግጁነትን መንፈስን የምታሳዩ ከሆነ፣ ይህ ተግባራችሁ የግል አገልግሎት ሳይሆን ወንጌላዊ ፍሬያማነት ነው” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉ ቅዱስነታቸው “የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ” ብሎ ሐዋሪያው ጳውሎስ (ገላቲያ 1:10) በጻፈው መልዕክቱ እራሱን ገልጾ ነበር ብለዋል። ጳውሎስ በመልዕክቱ መግቢያ ላይ  በኢየሱስ ፈቃድ እራሱን “ሐዋሪያ” ብሎ ሰይሞ ነበር ያሉት ቅዱስነታቸው እነዚህ ማለትም ሐዋሪያ እና አገልጋይ የሚሉት ሁለት ቃላት ሁል ጊዜም አብረው የሚሆኑ እና የማይነጣጠሉ መሆናቸውን ያሳያል ካሉ ቡኋላ ልክ እንደ የአንድ ሜዳሊያ ሁለት ገጽታዎች፣ ኢየሱስን የሚሰብኩ አገልጋይ እንዲሆኑ የተጠሩ ናቸው እዲሁም የሚያገለግሉ ኢየሱስን ይመሰክራሉ ብለዋል።

“የህንንም በቀዳሚነት ያሳየን ጌታ ነበር” በማለት ስብከተ ወንጌላቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው እርሱ ነው የአብን የምስራች ቃል ያመጣልን (ኢሳ 61,1) ይህ የምስራች ቃል በእርግጥ እርሱ እራሱ ነው  (ሉቃ 4,18) የእኛ አገልጋይ ሆነ (ፍሊ. 2,7) ብለው የመጣውም “ልገለገል ሳይሆን ልያገለግል ነው” (ማር. 10,45) “የሁሉም አገልጋይ ወይም በግሪክ ዲያኮኖስ” ሆነ ካሉ ቡኋላ የቤተ ክርስቲያን አባት የነበረው ቅዱስ ፖሊካርፕ “እኛ እርሱን የምንመሰክር ሁላችን ተግባራችን የእርሱን እንዲመስል ተጠርተናል” ያለውን ካስታወሱ ቡኋላ የኢየሱስ ሐዋሪያት ጌታቸው ካሳያቸው ጎዳና ሌላ በሌላ ጎዳና ላይ ልራመዱ አይችሉም፣ ልያውጀው የምፈልግ ሁሉ እርሱን መምሰል ይጠበቅበታል ብለዋል።

እንደ ሐዋርያው ጳውሎስ አገልጋይ ለመሆን ጥረት ማድረግ ይጠበቅብናል በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በሌላ አነጋገር በጥምቀት ሁሉም ክርቲያኖች የተቀበሉትን መንፈሳዊ ተልዕኮ መወጣት የምችሉት በአገልጋይነት ስሜት መሆን ይኖርበታል ብለው ይህም የኢየሱስ ሐዋሪያ ለመሆን ብቻኛው መንገድ ነው ብለዋል።

በማስከተል ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት የእርሱ መስካሪዎች እርሱ ያደርገውን የሚተገብሩ ብቻ መሆናቸውን ገልጸው ይህም ወንድም እና እህቶቻቸውን ደከመኝ ሳይሉ የክርስቶስ ትህትናን ተላብሰው የምያገለግሉ ክርስቲያኖች መሆናቸውንም ጨምረው ገልጸዋል።

እንዴት ነው “መልካም እና ታማኝ አገልጋይ መሆን የምንችለው?(ማቴ. 25,21) በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህንን ለመተግበር በመጀመሪያ በቀላሉ የሚገኝ ሰው መሆን ይጠበቅብናል ብለው አገልጋይ ከምያከናውናቸው የግል ተግባራት እራሱን ማላቀቅን እና እንደ ፈለገ መኖርን ማቆም መማር ይጠበቅበታል ካሉ ቡኋላ ለጋስ የሆነ ሕይወት ይኖረው ዘንድ በእየ እለቱ እራሱን የምያሰለጥን እና የተቀረው ቀን የእርሱ ብቻ ሳይሆን ለሌሎች አገልግሎት ይውል ዘንድ የተሰጠ መሆኑን ሊገነዘብ የሚችል ሰው መሆን ይኖርበታል ብለዋል።

መልካም እና ታማኝ አገልጋይ የተሰጠው ጊዜ የእርሱ ብቻ እንዳልሆነ እና ነገር ግን ከእግዚአብሔር የተሰጠ ስጦታ እና ተመልሶ ለእግዚአብሔር  መሰዋት እንዳለበት ያውቃል ያሉት ቅዱስነታቸው በእዚህ ዓይነት መንገድ ብቻ ነው ፍሬያማ መሆን የሚቻለው ብለዋል።

የዛሬ ወንጌል ስለ አገልግሎት ነው የሚናገረው በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉ ቅዱስነታቸው ብዙ ትምህርት ሊሰጡን የሚችሉ ሁለት አገልጋዮች የተጠቀሱበት ነበር ብለው ኢየሱስ ከበሽታው የፈወሰው የመቶ አለቃው አገልጋይ እና የንጉሠ ነገሥት አገልጋይ የነበረው የመቶ አለቃ የነበርው ሰው ታሪክን እንደነበረ ጠቅሰዋል።

መቶ አለቃው ኢየሱስ ወደ ቤቱ ሄዶ የታመመውን አጋልጋዩን ይፈውሰው ዘንድ ያግባባው ግሩም በሆነ መንገድ ነበር ያሉት ቅዱስነታቸው ይህም እርሱ ከሚተገብረው ፍጹም ተቃራኒ በሆነ መልኩ “ጌታ ሆይ አንተ ወደ ቤቴ ትገባ ዘንድ ያልተገባው ነኝ እና ወደ እኔ ለመምጣት አትድከም፣ እኔ ራሴ ወደ አንተ ለመምጣት የበቃው ሰው አይደለሁም፣ እኔ ራሴ ለባለ ስላጣናት ታዛዥ ነኝ” በሚሉት እነዚህ ቃላት ኢየሱስ እራሱ በጣም ተገርሞ እንደነበር የጠቀሱት ቅዱስነታቸው በመቶ አለቃው ትህትና እና የዋህነት ተነክቶ እንደ ነበር አውስተው የመቶ አለቃው ስልጣኑን ተጠቅሞ የፈለገውን ነገር ኢየሱስ እዲፈጽምለት ሊጠይቅ ይችል እንደነበረም ጨምረው ገልጸዋል።

ከዚህ ይልቅ አሉ ቅዱስነታቸው የመቶ አለቃው ልኩን የሚያውቅ ሰው ስለነበረ ድምፁን ከፍ አድርጎ ወይም ነገሩን አወዛጋቢ ሳያደርግ ይልቁንም ልክ እንደ እግዚኣብሔር እራሱን “ትሁት እና የዋህ” (ማቴ. 11,29) ማድረግን መርጦ ነበር ብለዋል። እግዚአብሔር ፍቃር ነው ከፍቅሩም የተነሳ ልያገለግለን ዝግጁ ነው በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው እርሱ ታጋሽ፣ ደግ እና ሁል ጊዜም ለእኛ አልኝታ ነው ብለው እርሱ ለስተታችን ይሰቃያል ከስተታችንም እንድንላቀቅ መንገድን ያዘጋጃል ብለዋል።

ትህትና እና የዋህነት የአንድ አገልጋይ ክርስቲያን መገለጫ ባህሪያት ናቸው በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ምክንያቱም ለሎችን በማገልገል እግዚአብሔርን እንድንመስል ስለምያደርጉን ነው ካሉ ቡኋላ በማይበርድ ርኅራኄ እና ታጋሽ በሆነ ፍቅር እንድንቀበላቸው፣ እነሱን በቤተ ክርስቲያን ማኅበራት እንደ ተቀበልናቸው እንዲሰማቸው በማድረግ፣ ትልቅ ልባሉ የሚችሉ የምያዙ ሰዎች ሳይሆኑ የምያገለግሉ (ሉቃ. 22,26) መሆናቸውን መረዳት እና በተለይም እናንተ የተወደዳችሁ ዲያቆናት የተጠራችሁት የፍቅር አገልጋይ እንድትሆኑ በመሆኑ የዋኅነትን ማጎልበት ይኖርባችዋል ብለዋል።

ዛሬ ካዳመጥናቸው ምንባባት በመነሳት ከሐዋሪያው ጳውሎስ እና ከመቶ አለቃው ታሪክ ቡኋላ የሚመጣው ሦስተኛው ሰው የመቶ አለቃው አገልጋይ የነበረው እና ኢየሱስ የፍወሰው ሰው ነበር በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉ ቅዱስነታቸው ቅዱስ ወንጌላችን እንደ ምያስረዳን በጌታው ዘንድ ተወዳጅ እንደ ነበረ እና በምን አይነት በሽታ እንደ ታመመ ግን ባይታወቅም ቅሉ በጠና ታሞ እንደ ነበረ ግን ያወሳል ብለዋል።

በመቀጠልም አንድ አንዴ በእዚህ አገልጋይ ሁኔታ ውስጥ እራሳችንን እናገኛለን ያሉት ቅዱስነታቸው እያንዳንዳችን በጣም በሚወደን፣ በመረጠን እና እንድናገለግል በጠራን በአምላክ ዘንድ በጣም ውድ ሰዎች ነን ብለው ነገር ግን እያንዳንዳችን በመጀመሪያ በስውር ተመልክቶን ይፈውሰን ዘንድ ያስፈልጋል ምክንያቱም ለአገልግሎት ዝግጁ ለመሆን በመጀመሪያ ጤናማ የሆነ እና በእግዚአብሔር የተፈወሰ ልብ ስለ ምያስፈልግ መሆኑን ገልጸው ይህም ልብ ይቅርታን ማድረግ የሚያውቅ፣ ያልተዘጋ እና ደንዳና ያልሆነ መሆን ስለሚገባ መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል።

በእየቀኑ በኢየሱስ እንፈውስ ዘንድ ጸሎት ማድረግ ያስፈልጋል እርሱን ለመምሰል እና ከአሁን ቡኋላ አገልጋዮች ሳይሆን ወዳጆቼ ብያችኋለው ኢየሱስ እንዳለ ሁሉ፣ ውድ ድያቆናት ይህንን ዓይነት ጸጋ ነው ዘወትር በጸሎታችሁ መሻት የሚኖርባችሁ ሥራችሁን በመስዋዕትነት አቅርቡ፣ችግሮቻችሁን፣ግራ መጋባታችሁን እና በተስፋ በተሞላ ተአማኒነት ባለው ጸሎት  ለጌታ ሕይወታችሁን ወደ ጌታን ደግሞ ወደ ሕይወታችሁ አስገቡት ካሉ ቡኋላ ቅዱስ ቁርባን መስዋዕት በሚሆንበት በመበረ ታቦት ላይ ሆናችሁ በምታገለግሉበት ጊዜ ሁሉ እራሳችንን ለሌሎች እንሰጥ ዘንድ እራሱን በመስጠት ምሳሌ የሆነውን የኢየሱስን መኖር ትረዳላችሁ በማለት ስብከታቸውን አጠናቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.