2016-05-29 13:49:00

ቅዱስ አባታችን ከ400 መቶ በላይ ከሚሆኑ ሕፃናት ጋር በቫቲካን ተገናኙ።


ቅዱስ አባትችን ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት ማለትም በግንቦት 20/2008 ከተለያየ ባሕል፣ ዘር እና እምነት የተውጣጡ እና የስደተኛ ልጆች የሚበዙባቸው ከ400 በላይ የሚሆኑ ከደቡብ ጣሊያን ከተማ ካላብርያ የመጡ ሕፃናትን በቅዱስ ጴጥሮ አደባባይ መገናኘታቸው ተገለጸ።

የባሕልን ጉዳይ የሚመለከተው የጳጳሳዊ ምክር ቤት በእዚህ ዓመት “በማዕበል ተወስደው” በሚለው መርሕ ቃል ላይ ተመስርቶ ባዘጋጀው እና ስደተኞች እየቀመሱ የሚገኘውን ገፈት፣ እያዳረጉት ያለውን አስከፊ የባሕር ላይ ጎዞ ለመዘከር እና በተለያየ ምክንያት ቤት ንብረታቸውን በመተው የተሻለ ኑሮ ፍለጋ በምያደርጉት ጎዞ አስፈሪ ለሆነው የባሕር ጉዞ እየተጋፈጡ ለሚገኙ ሰዎች ለወደፊቱ የተሻለ ተስፋን በመፍጠር ይህንን አስከፊ የሆነውን ስቃይ፣ ባርነት እና ሞትን ለመቅርፍ እና ግንዛቤን ለማስጨበጥ ታስቦ የተዘጋጀ ጉብኝት መሆኑም ታውቁዋል።

እነዚህ ሕዛናት ቅዳሜ እለት ማለትም በግንቦት 20/2008  እስከ ቫቲካን ቅጽር ግቢ ድርስ በባቡር የዘለቁ ሲሆን በታላቅ መከራ  የታለፈው እና የአስቸጋሪው የባሕር ላይ ጉዞን ተመኩሮ የነበራቸውን ልጆች ያካተተ ሲሆን እነዚህን የመሳሰሉ ሕፃናትን ተቀብሎ የሚንከባከበው የዩሐንስ 23ኛ የበጎ አድራጎት ማህበር፣ ኩዋትሮካንቲ የተባለው እና ከስምንት ሀገሮች የተውጣጡ ሰዎች የተሳተፉበት የፓሌርሞ የሙዚቃ ኦኬስትራ እና የመሳሰሉ የማህበራት ተወካዮች የተካፈሉ ሲሆን በተለይም የቪቦ ማሪያ ትምህርት ቤት ሕጻናት በግሪክ ስደተኞች ተጠልለውባት የምትገኘው ለለስቮስ ዴስት ስደተኞች መርጃ የሚውል ገንዘብ አዋተው በተወካያቸው አማካይነት ለስደተኞቹ መርጃ ይውል ዘንድ ለቅዱስ አባታችን ማቅረባቸው እና አያይዘው በጻፉት ደብዳቤ ሕፃናቱ እንደ ገለጹት “እኛ ሕፃናት ወደ ሀገራችን የሚመጡትን ማንኛቸውንም የሰው ልጆች፣ የተለየ የቆዳ ቀለም፣ የተለየ ቁዋንቋ፣ ወይም ከእኛ የተለየ እምነት በተጨማሪም አደገኛ ጠላት ቢሆንም እንኳን ምንም ሳንለይ ለመቀበል ዝግጁ ነን” በማለት ያስተላለፉት በልዕክት ከገንዘብ ልገሳው በመቀጠል ለቅዱስነታቸው መነበቡም ታውቁዋል።

ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በፊናቸው የሕፃናቱን መልዕክት ካዳመጡ ቡኋላ ያደረጉት የማስገንዘቢያ ንግግር ትኩረቱን አድርጎ የነበረው አሁን አሳሳቢ ሊባል በሚችል ሁኔታ እየታዬ የሚገኘው የስደተኞች ፍሰት ላይ ትኩረቱን እድርጎ እንደ ነበር የተገለጸ ሲሆን በተለይም ደግሞ በነፍስ ማዳን ተግባር ላይ ከተሰማሩ ሰዎች የሰሙትን ታሪክ በማስታወስ እና ባለፈው ሳምንት አንድ የነፍስ አዳኝ የአንድ ሕፃን ልጅ የነበረ በውሃ ላይ የመንሳፈፊያ ጃኬትን ለቅዱስነታቸው ባበረከተበት ወቅት “አባ የአቅሜን ያህል ሞክሬ የነበርኩ ብሆንም ይህችን ትንሽ ልጅ ግን በማዕበሉ ምክንያት ለማትረፍ አልቻልኩኝም፣ የመንሳፈፊያ ጃኬቱዋን ብቻ ነው ላገኝ የቻልኩት” በማለት እያለቀሰ ነግሮኝ ነበር ብለው እና የተበረከተላቸውን የሕፃኗን የመንሳፈፊያ ጃኬት በማሳየት “ይህንን የምንግራችሁ እንድታዝኑ ስለፈልኩኝ ሳይሆን ብርቱዎች ስለሆናቸው እውነትን እንድታውቁ ስለፈለኩኝ እና በጣም ብዙ ወንድ እና ሴት ሕፃናት ትንንሽ ልጆችም፣ እናቶች፣ አባታቶችም ሳይቀሩ በጣም በአደገኛ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ እድታውቁ ስለፈለኩኝ ነው” ብለዋል።

“እስቲ ይህችን ሕፃን ልጅ እናስታውስ፣ ስሟ ማን ነበረ? ብለው ከጠየቁ ቡኋላ “እኔ እንጃ እኔ ስሟን አላውቅም፣ ስም የሌላት ትንሽ ልጅ ነበረች ሁላችሁም የምትፈልጉትን ዓይነት ስም በልባችሁ ስጡዋት። አሁን በመንግሥተ ሰማይ ሆና እኛን እያየች ናት” በማለት በተመስጦ ተናግረዋል።

በስተመጨረሻም ከተሳታፊ ሕፃናት አንዱ ለቅዱስነታቸው “ሊቄጳጳሳት መሆን ማለት ምን ማለት ነው?” ብሎ ለቅዱስነታቸው ላቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ “መሥራት ያለብኝ ያህል መሥራት ማለት ነው” ካሉ ቡኋላ “እኔ እንደ ማስበው ኢየሱስ ክርስቲያን እንድሆን ጠርቶኛል፣ አንድ ክርስቲያን ደግሞ መልካም ተግባራትን የግድ ማከናወን ይኖርበታል፣ ኢየሱስ ካህን እንዲሁም ጳጳስ እንድሆን ፈልጎኛል፣ ካህናት እና ጳጳሳት የግድ የተቻላቸውን ያህል መልካም ተግባራትን ማከናውን አለባቸው። በአጠቅላይ ኢየሱስ ይህንን እንዳከናውን እንደ ጠራኝ ይሰማኛል የማስበውም ይህንኑ ነው” ብለው ከመለሱለት ቡኋል ንግግራቸውን አጠናቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.