2016-05-26 11:31:00

ቅዱስነታቸው በቅ.ጴጥሮስ አደባባይ ለተገኙ ምዕመናን "ሳንታክት ዘወትር መጸለይ ያስፈልጋል” ማለታቸው ተገለጸ።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በግንቦት 17/2008 በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሳምንታዊው የጠቅላላ አስተምህሮ ለተገኙ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኚዎች የሰጡት ትምህርት ትኩረቱን አድርጎ የነበረው በሉቃስ ወንጌል በምዕራፍ 18: 1-8 የተጠቀሰው የድኻዋ መበለት እና የዐመጸኛው ዳኛ ምሳሌ ላይ ትኩረቱን አድርጎ የነበረ ሲሆን ቅዱስነታቸውም በእዚህ ምሳሌ ላይ ተመርኩዘው “ሳንታክት ዘወትር መጸለይ ያስፈልጋል” ማለታቸው ተገለጸ።

“አንድ አንዴ እኛ ስንፈልግ ብቻ መጸልይ ሳይሆን የሚገባን ኢየሱስ እንዳዘዘን እና በድኻዋ መበለት ምሳሌ እንዳስተማረን ሳንታክት ሁልጊዜ መጸለይ ይገባናል” በማለት አስተምህሮዋቸውን የጀመሩት ቅዱስነታቸው “አመጸኛው ዳኛ በጊዜው በነበረው የሙሴ ሕግ ላይ ያልተመሠረተ እና  ሕግን የሚተላለፍ ኃይለኛ ሰው” እንደ ነበር ገልጸው “ለእዚም ሲባል ነው በመጻሐፍ ቅዱሳችን ዳኞች እግዚአብሔርን የሚፈሩ፣ ታማኞች እና በማታለል የሚገኘውን ጥቅም የሚጸየፉ ይሁኑ የሚለው” (ዘፀአት 18:21) ማለቱን አውስተው ይህንን ዘሬ እኛ ማዳመጥ ይኖርብናል ብለዋል።

ይህ ዳኛ ግን የእግዚአብሔር ቃል ከምያዘው በተቃራኒ “እግዚአብሔርን የማይፈራ ሰውንም የማያፍር” ነበር ብለው ሕግን በተጻረረ መልኩ የእራሱን ፍላጎት ብቻ የሚተገብር ፍትሐዊ ያልሆነ እና ይሉኝታ ቢስ እንደ ነበረ አብራርተው ይህ ሰው ነው እንግዲህ ለእዚህቺ ድኻ መበለት ሴት ፍርድ እንዲሰጥ የተመረጠው ብለዋል።

በጊዜው መበለቶች፣ ወላጅ አልባ ልጆች እና ባዕዳን  በህብረተሰቡ ውስጥ በጣም ተጋላጭ ልባል የሚችል ቦታ ነበራቸው በማለት አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉ ቅዱስነታቸው አቅመ ደካሞች ወይም የምያግዛቸው ሰው ባለመኖሩ ምክንያት ብቻ ሕግ የሰጣቸው ከለላ በቀላሉ ይገፈፍ ነበር፣ መብታቸውን እንኳን ለማስከበር የሚቸገሩ፣ የተዘነጉ በሕግ የተፈቀደላቸውን መብት እንዃን ለማግኘት የሚቸገሩ ነበሩ በለዋል።

ምንም እንኳን ዳኛው በጣም ግድ የሌሽ ሰው የነበረ ቢሆንም ይህቺ ድኻ መበለት ሴት ግን ፍትህ ይሰጣት ዘንድ አጥብቃ ከመወትወት አልቦዘንችም ነበር ያሉት ቅዱስነታቸው በእዚህ ጽናቷ ነው የፈለገችሁን ፍትህ ልትጎናጸፍ የበቃቸሁ ብለዋል። ይህ አመጸኛ ዳኛ ግን ለድኻዋ መበለት የፈረደላት ስላዘነላት ወይም ጉዳዩ አሳሳቢ ሆኖ ስላገኘው ሳይሆን ስለነዘነዘችሁ ብቻ ነበር የፈረደላት ብለዋል።

“በእዚህ ምሳሌ ኢየሱስ ልያስተምረን የፈለገው ነገር” አሉ ቅዱስነታቸው “ይህቺ ደኻ መበለት በተከታታይ አመጸኛውን ዳኛ ነዝንዛ ፍርድ እንዳገች ሁሉ መልካም እና አባት የሆነው እግዚአብሔር ደግሞ አጥብቆ ለሚለምኑት ሰዎች ሁሉ እና “ቀን ከሌት ወደ እርሱ ለሚጮኹ ልጆቹ ፍትህን እንደ ማይነፍጋቸው” ልያስተምረን ፈልጎ ነው ካሉ ቡኋላ “እግዚአብሔር ግን እንደ አመጸኛው ዳኛ ብዙ የምያስጠብቀን ሳይሆን  ወዲያውኑ እርምጃን የሚወስድ አምላክ ነው” ብለዋል።

“ስለእዚህም ሳናቋርጥ እና ሳንሰላች የምንፈልገውን ነገር እስኪያጎናጽፈን ድርስ ተግተን መጸለይ ያስፈልጋል” ያሉት ቅዱስነታቸው “ሁላችሁንም በድጋሜ የምጠይቀው ነገር ቢኖር ያለማቋረጥ  ወደ መኅሪው አባት እና ወደ እናታችን ቅድስት ማሪያም ለሞቱት ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን የዘላለምን እረፍት ይሰጥ ዘንድ፣ ያዘኑ ቤተሰቦች እንዲጽናኑ፣ ሞት እና ጥፋትን የሚዘሩ ሁሉ ልባቸው ይቀየር ዘንድ፣ ሁላችንም በአንድነት ፀጋ የሞላሽ የሚለውን ጸሎት እንጸልይ ካሉ ቡኋላ ሰላምታን እና ቡራኬን ስጥተው የእለቱ ዝግጅት ተጠናቁዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.