2016-05-24 11:23:00

ቅዱስነታቸው "የእግዚአብሔርን ቃል በምናወጅበት ወቅት ሰባዊ ድክመትን ከግንዛቤ ያስገባ መሆን ይኖርበታል" ማለታቸው ተገለጸ።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በግንቦት 12/2008 በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ባሳረጉት ስርዓተ ቅዳሴ ላይ ያሰሙት ስብከት በእለቱ ወንጌል ላይ ትኩረቱን ያደረገ እና ኢየሱስ ከፈሪሳዊያን ጋር ስለ አመንዝራነት ያደርገውን ወይይት ተንተርሰው  ቅዱስነታቸው እንደገለጹት የእግዚአብሔርን ቃል በምናወጅበት ወቅት ሰባዊ ድክመትን ከግንዛቤ ያስገባ መሆን ይኖርበታል ብለው ለእግዚአብሔር ያለንን ምልከታ የሚቀንሱ ነገሮችን እንድንወጣ ጌታ ይረዳናል ማለታቸው ታወቃ።

ቅዱስ ወንጌል አሉ ቅዱስነታቸው ኢየሱስን በማሳሳት እና ወጥመድ ውስጥ በማስገባት ሥልጣኑን ለማዳከም እንዲሁም በሕዝቡ ዘንድ ያለውን ሞገስ ለማሳጣት በሚፈልጉ በፈሪሳዊያን እና በሕግ መምህራን ምሳሌዎች የተሞላ ነው ብለው ፈሪሳውያን “አንድ ሰው ሚስቱን ሊፈታ ተፈቅዶለታልን?” ብለው ኢየሱስን ለመፈታተን  በዛሬ ወንጌል ያቀረቡት ጥያቄ ለእዚህ እውነታ በማሳያነት ሊጠቀስ ይችላል ብለዋል።

ቅዱስነታቸው በማከልም “ወጥመድ” እና “ማጋጨት” የሚሉት ሁለት ቃላት በአንድ አንድ የነገረ መለኮት ጠቢባን ዘንድ ሲተረጎም ኢየሱስ የእግዚአብሔርን ሕዝብ ሁሉ እውቀትና ጥበብ ጠንቅቆ ስለሚያውቅ እነዚህን ሁለት መሰናክሎች በሚገባ አልፉዋቸው ሁኔታውን ከጋብቻ ሙሉነት ጽንሰ ሐሳብ ልቆ ተመልክቶት ነበር የሚል ትርጓሜን ይሰጡታል ብለዋል።

ኢየሱስ የጋብቻን ምስጢር የተመለከተው ፈሪሳዊያን እንደ ተገነዘቡት ምድራዊ በሆነ ገጽታው ብቻ ሳይሆን በአንጻሩም ኢየሱስ የጋብቻን ምስጢር የተመልከተው ላቅ ያለ ምልከታን ተጠቅሞ “የፍጻሜ ሙላት” በሚለው ትርጉሙ ሲሆን ይሄውም “እግዚአብሔር ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠረ፣ እንርሱም አንድ አካል ይሆናሉ” በሚለው ትርጉሙ ነበር ብለዋል።

ቅዱስነታቸው በማስከተልም “እነዚህ ሰዎች ከአሁን ቡኋላ ሁለት አይደሉም ነግር ግን አንድ ናቸው እግዚአብሔር ያጣመረውን ሰው ሊለየው አይችልም” የሚለውን የመጸሐፍ ቅዱስ ቃል ጠቅሰው በጋብቻ እነዚህ ሁለት ሰዎች ወደ ሙላት ተሻግረዋል እውነታውም ይህ ነው፣ ኢየሱስ በእውነት ላይ አይደራደርም” ብለዋል።

“ነገር ግን” አሉ ቅዱስነታቸው “ነገር ግን ኢየሱስ ሁልጊዜም መኅሪ ነው” ካሉ ቡኋላ “ኢየሱስ በፍጹም በሩን ለኋጥያተኛ የማይዘጋ በጣም መኅሪ እና በጣም ትልቅ ነው” ብለው “እራሱን የእግዚአብሔር እውነትነትን በመመስከር ላይ ብቻ ሳይገድብ ሙሴ ስለ ፍቺ ምን ብሎ እንዳዘዛቸው ወደ ኋላ ተመልሰው ያገናዝቡ ዘንድ ፈሪሳዊያንን ጠይቆዋቸው ነበር” ብለዋል።

ነገር ግን ፈሪሳዊያን “ሙሴ የፍቺ ወረቀቱዋን ሰጥቶ ይፍታት ብሎ አዞናል” ብለው በመለሱ ጊዜ ኢየሱስም ይህን ያላችሁ “የልባችሁን ድንዳኔ ስለተመልከተ ነው” ብሎ መመለሱ ኢየሱስ በሰው ድክመት እና ቃላትን ማጣመም መኋከል ያለውን ልዩነት ጠንቅቆ እንደ ምያውቅ ያሳይል ብለዋል።

አሁን እኛ በምንኖርበት ዓለም ውስጥ የሚታየው  ከእዚህ ዓይነት የኃጢያት ባሕል እውነታ ጋር በጣም የተቆራኜ ነው። ልክ ኢየሱስ ለፈሪሳዊያን እንዳላቸው ልበ ደንዳናነት እና ኋጥያት በዓለማችን ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ ይታያል ለእዚህም መላ ሊበጅለት ይገባል ብለዋል።

በተለይም ይቅር ማለት፣ መረዳት፣ ማጀብ፣ ማዋሃድ እና ጉዳዩን የተመለከት ውስኔን ማድረግ የመሳሰሉ ተግባራትን እውነት ላይ ተመርኩዘን መመስከር እና የኋጥያተኛውን ነባራዊ እውነታ ተርድተን ከድክመቱ እንዲወጣ ልናግዘው ይገባል ብለዋል።

ኢየሱስ በእዚህ የወንጌል ክፍል ልያስተምረን የሚፈልገው “እውነት እና መረዳት” የሚሉትን ቃላት በአግባቡ እንድንረዳ ነው ያሉት ቅዱስነታቸው ኢየሱስ ሁል ጊዜ እውነትን በልባችን እንድናኖር ይርዳን እንዲሁም በእዚህ ዓይነት ችግር ውስጥ የሚገኙ ወንድም እና እህቶች ግንዛቤን ይፈጥሩ ዘንድ ማገዝ እንደ ምያስፈልግ አበክረው ገልጸው የእውነት አስተማሪ የሆነው መንፈስ ቅዱስ ልባችንን በእውነት እንዲሞላው እና እግዚአብሔር በፀጋው ሁላችንንም ይሙላን ብለው የእለቱን ስብከት አጠናቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.