2016-05-18 16:30:00

ብፁዕ ካርዲናል ባኛስኮ፥ የሕይወት ባህል ግብረ ገባዊና ሥነ ምግባራዊ መመዘኛው


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ባስደመጡት ንግግር እ.ኤ.አ. ግንቦት 16 ቀን 2016 ዓ.ም. በይፋ በተከፈተው 69ኛው የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ጠቅላይ ጉባኤ እ.ኤ.አ. ግንቦት 17 ቀን 2016 ዓ.ም. ጧት የምክር ቤቱ ሊቀ መንበር የጀኖቫ ሊቀ ጳጳሳት ብፅዕ ካርዲናል አንጀሎ ባኛስኮ በአሁኑ ወቅት በዓለም ከ 200 ሚሊዮን በላይ የሚገመተው ክርስቲያን ለስደት መዳረጉና እውነቱም ይኽ  ሆኖ እያለ ይኸንን ጸረ ክርስቲያን ድርጊት እንዲገታ ብዙ እንደማይደርግ ነው ብለው፡ ማንኛውም ዓይነት አሳዶ አሰቃቂ ዓመጽ መሆኑ በማብራራት የስደተኞና ተፈናቃዮች ጉዳይ ዳሰው በመጨረሻም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የለገሱት የፍቅር ሐሴት የተሰየመው ድኅረ ሲኖዶሳዊ ሐዋርያዊ ምዕዳን የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ለቤተሰብ ለምታቀርበው ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ መርህ መሆኑና በኢጣሊያ የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የምትከተለውም የቤተሰብ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ በዚህ ሐዋርያዊ የሚመራ መሆኑ ገልጠው አያይዘውም ቅዱስ አባታን ር.ሊ.ጳ. ሁሉም የቤተ ክርስቲያን አባል እንደየጥሪውና ኃላፊነቱ ለመለወጥ ዕለት በዕለት የሚጠራና በግልም ሆነ በሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ለውጥ ያለው አስፈላጊነት በቃልና በሕይወት የሚያነቃቁ ናቸው። በመጨረሻም የኢጣሊያ ማኅበራዊ ፖሊቲካዊና ኤኮኖሚያዊ ወቅታዊው ሁነት ዳሳሽ ንግግር ማስደመጣቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ደቦራ ዶኒኒ ገለጡ።

ብፁዕ ካርዲናል ባኛስኮ ባስደመጡት ንግግር ፍትኃ ጋብቻ ማሕጸን የማከራየት ተግባር እንዲሁም ተባዕትና አንስት ከሚለው ባህርያዊ በሰዎች መካከል ያለው መሆናዊ ልዩነት ውጭ አዲስ የፆታ ሥነ ትምህርት እየተባለ ሁለት ዓይነት ፆታ መሆኑ ቀርቶ ኅብረ ፆታዊ ግንዛቤ የሚያፋፋ እየተሰጠ ያለው ርእዮተ ዓለማዊ ስብከት በወንድና በሴት መካከል የሚጸናው ጋብቻ ና ከዚህ ዓይነት ውህደት የሚጸናው ቤተሰብ ወጭ ማንኛውም ዓይነት አብሮ መኖር ጋር በማመሳሰል በወንድና በሴት መካከል የሚጸናው ጋብቻ ከሚሰበኩት አዳዲስ የጋብቻ ዓይነት ውስጥ አንዱ እንደሆነ አድርጎ ማቅረብ የመሳሰሉት አመለካከቶችና ሕግ አድርጎ የማጽደቁ ውሳኔ ነቅፈው፡ ማሕጸት ማከራየት የተፈቀደ ነው በሚል መንግሥታት የሚያጸቁት ሕግ ሥር ጸረ ሕይወት ባህል እየተስፋፋ ነው፡ በድኽነት ጭንቃ ሥር የሚገኙ ሴቶች ማሕጸንቸውን ለማከራየት ተግባር እየተገፋፉ ነው እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ደቦራ ዶኒኒ ያመለክታሉ።

ማንኛውም ዓይነት አብሮ መኖር በወንድና በሴት መካከል ከሚጸናው ጋብቻ ጋር የማዛመዱ ሂደት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮና የመላ ሩሲያና ሞስኮ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ኪሪል በተገናኙበት ወቅት በሰጡት የጋራ መግለጫ፥ ምንም አይነት ተምሳይነት የሌለው ነው በማለት እንዳሰመሩበት ያስታወሱት ብፁዕ ካርዲናል ባኛስኮ አክለው፥

የፍቅር ኃሴት ሐዋርያዊ ምዕዳን አማካኝንት የቤተሰብ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ በቅዱስ የምኅረተ ዓመት መንፈስ ሥር ማደስና ማነቃቃት ያለው አንገብጋቢነት እንዳሰመሩበት ዶኒኒ አስታወቁ።

ኤውሮጳ ያስተናጋጅነት ባህሏ ዳግም ኅያው ታድርግ

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በግሪካዊቷ ደሴ ለስቦ የሚገኘውን የስደተኞች መጠለያ ሰፈር ጎብኝተው ከስደተኞች ጋር በመገናኘት ባስደመጡት ንግግር በእውነቱ ኤውሮጳ እንግዳ ተቀባይነቷና አስተናጋጅ ባህሏ ዳግም ኅያው እንድታደርግ የሚያሳስብ መሆኑ ያስታወሱት ብፁዕ ካርዲናል ባኛስኮ አክለው፥ በኢጣሊያ የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በጠቅላላ 23 ሺሕ ስደተኞች በማስተናገድ ላይ ነች እንዳሉ ዶኒኒ ያመልክታሉ።

የክርስቲያኖች ለስደትና ለመፈናቀ አደጋ መጋለጥ

በመካከለኛው ምስራቅ በሰሜን አፍሪቃ በአንዳንድ ክልሎች ማኅበረ ክርስቲያን ለመሰደድ አደጋ የተጋለጠ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ከ 200 ሚሊዮን በላይ ክርስቲያኖች ለስደት መዳረጋቸው ያስታወሱት ብፁዕ ካርዲናል ባኛስኮ አክለው ማኅበረ ክርስቲያን ከገዛ አገሩ እንዲሰደድ እየተገደደ ይኽ ደግሞ በመካከኛ ምስራቅ አገሮች የነበረው የክርስቲያን ብዛት እጅግ እየቀነሰ መጣቱና በሶሪያ ያለው ሁኔታ ያርጋግጠዋል ብለው የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ይኸንን ጉዳይ በዝምታ ሊመለከተው አይገባም እንዳኡ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ዶኒኒ አክለው፥ ብፁዕነታቸው ስለ ውሉደ ክህነት ተሃድሶና የዘርአ ክህነት ትምህርት ቤቶች ጉዳይ ርእስ በማድረግ፥ የቤተ ክርስቲያን ሥልጣናዊ ትምህርት በተለይ ደግሞ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ይኽ የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ይፋዊ ጠቅላይ ጉባኤ ለማስጀመር ባስደመጡት ንግግር፡ የካህን ሕይወትና ተልእኮ በሚል ርእስ ሥር የካህናት ሰብአዊ መንፈሳዊ ባህላዊ ሕንጸት አደራ ብለው ከዚህ ጋር በማያያዝም ብፁዓን ጳጳሳት ስለ ካህናቶቻቸው እዲያስቡና ካህናቶቻቸውን እንዲንከቡ ኃላፊነት አለባቸው ያሉትን ሃሳብ ጠቅሰው በጳጳስና በካህን መካከል ውህደት እንዲኖር እደራ እንዳሉ አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.