2016-05-17 16:00:00

“እናንተን አባት እንደሌላቸው ልጆች ብቻችሁን አልተዋችሁም”


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በላቲን የስርዓተ ሊጡርጊያ አቆጣጠር መሰረት እና  እንደ አውሮፓዊያን የቀን አቆጣጠር በግንቦት 15/2016 የተከበረውን የጳራቅሊጦስ በዓልን በማስመልከት በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ብዙ ካህናት፣ ደናግላን፣ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኚዎች በተገኙበት ባሳረጉት ስርዓተ ቅዳሴ ላይ ያሰሙት ስብከት መሰረቱን ያደርገው ከዩሐንስ ወንጌል ከምዕራፍ 14:18 ላይ በተወሰደው  “እናንተን አባት እንደሌላቸው ልጆች ብቻችሁን አልተዋችሁም” በሚለው ዓረፈተ ነገር ላይ የተመረኮዘ  ነበር።

የቅዱስነታቸው የዕለቱ ስብከት እንደ ሚከተለው ነው።

የኢየሱስ ተልዕኮ ማዕከላዊ ዓላማ በኋጥያት ምክንያት ተጎድቶ የነበረውን ከእግዚአብሔር አብ ጋር የነበረን ግንኙነት ማደስ እና በእዚህም ከወላጅ አልባ ልጅነት ወደ እርሱ ልጅነት የተለወጥንበትን አጋጣሚ የፈጠረ በመሆኑ ይህም ተልዕኮ በእዚህ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ፍጻሜን አግኝቱዋል።

ቅዱስ ሐዋሪያው ጳውሎስ ወደ ሮም ሰዎች በጻሐፈው መልዕክቱ “በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው። ስለእዚህ ‘አባባ’ ብላችሁ የምትጠሩበትን የልጅነት መንፈስ ተቀበላችሁ እንጂ በፍርሃት ለመኖር የባርነት መንፈስን አልተቀበላችሁም” (ሮሜ. 8:14-15)። እዚህ ላይ ከእግዚኣብሔር ጋር ያለን ግንኙነት እንደ ታደሰ እናያለን፣ ክርስቶስ ለከፈለልን የማዳን መስዋዕትነት እና ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይድረሰው ምክንያቱም የእግዚአብሔር አባትነት በድጋሚ ታድሱዋልና።

መንፈስ ቅዱስ  በእግዚአብሔር አብ ለእኛ የተሰጠ ወደ እግዚአብሔር አብ መልሶ እኛን እንዲመራን ነው። በእግዚአብሔር አባትነት፣ በልጁ ስጦታነት እና በመንፈስ ቅዱስ መሪነት እኛን ለማዳን የተደረገው ጠቅላላ ጥረት እኛ ገብተንበት ከነበረው  የወላጅ አልባነት ሁኔታ ነፃ ወጥተን "ዳግም-እንድነውለድ" የምድረገን ተግባርን ያማከለ ነው።

ዛሬ እኛ ባለንበት ጊዜ ምንም እንኳን በብዙ ሰዎች ተከበን ያለን ብንሆንም ቅሉ ውስጣዊ ብቸኝነት እንዲሰማን የሚያደርጉ እና ወላጅ አልባነት ስሜት እንዲሰማን የሚያደርጉ ብዙ ምልዕክቶች ይታያሉ። ይህ የብቸኝነት ስሜት ሕልውናችንን ወደ ሐዘን ያስገባዋል። ምንም እንኳን እርሱ በሕይወታችን እንዲኖር ብንፈልግም ከእግዚአብሔር ነፃ ለመሆን የምናደርገው ጥረት፣ ሁላችንም በጋራ ለጸሎት የምናሳየው ቸልተኝነት ወደ መንፈሳዊ ድንቁርና የሚያመራን እና እውነትን ለመጨበጥ በአሁኑ ጊዜ ያለውን አስቸጋሪነት እንዲሁም ከእዚህ አሁን ካለንበት ምድር በምንፈጥረው ሕብረት የሚጀመረው ከሞታችን ቡኋላ ለሚከተለው የዘላልም ሕይወት እውነታ፣ ሁላችንም የአንዱ እግዚአብሔር አባት ልጆች በመሆናችን ወንድሞቻችን እና እህቶቻችንን ለመገናኘት የምናደርገው ጥረት እነዚህን እና እነእዚህን የመሳሰሉ ምልክቶች በእዚህ ዘመን ይታያሉ።

የእግዚአብሔር ልጆች መሆን ማለት እነዚህን ከላይ የተጠቀሱ ምልክቶች ሁሉ ጋር የሚቃረን የማሳሰቢያ ጥሪን መቀበል ማለት ነው። የእግዚአብሔር ልጆች ልንሆን ተጠርተናል ይህም የዘር ግንዳችን ወይም ተክለ መለያችን ነው። ነግር ግን ይህ ተቋርጦ የነበረው ግንኙነታችን ይጠግን ዘንድ የእግዚአብሔር አንድኛ ልጅ እራሱን መስዋዕት በማድረግ ግንኙነቱን ማስቀጠል ነበረበት። በጣም ትልቅ የፍቅር ስጦታ ከሆነው ከኢየሱስ የመስቀል ላይ ሞት አንስቶ በሰው ልጆች ሁሉ ላይ እስከዘነበው የመንፈስ ቅዱስ የፀጋ ስጦታ ተስጥቶናል። በእዚህ ታላቅ እምነት የተጠመቁ  ሁሉ ዳግም ተወልደው ሙሉ የሆነ የዘላለም ሕይወትን ያገኛሉ።

““እናንተን አባት እንደሌላቸው ልጆች ብቻችሁን አልተዋችሁም”። ዛሬ በእዚህ በጴንጤቆስጤ በዓል ኢየሱስ እናታችን የሆነችው ቅድስት ድንግል ማሪያም በላይኛው ክፍል ውስጥ እንደነበረች ያስታውሰናል። የኢየሱስ እናት ሐዋሪያት በአንድነት በጸሎት ላይ በተሰበሰቡበት ክፍል ውስጥ ነበረች፣ የኢየሱስ ሕያው መታሰቢያ እና የመንፈስ ቅዱስ ሕያው መጠየቂያ ናት። የቤተ ክርስቲያን እናትም ናት። በእርሷ አማላጅነት ጸሎታችንን በተለይም ለሁሉም ክርስቲያኖች፣ መንፈስ ቅዱስን አጥበቀው ለሚሹ ቤተሰቦች እና የማሕበረሰብ አባላት፣ ጠባቂ፣ አጽናኝ የእውነት፣ የነጻነት እና የሰላም መንፈስ የሆነው መንፈስ ቅዱስ ጴራቂሊጦስ ከልጇ ታሰጠን ዘንድ መማጸን ይኖርብናል።

መንፈስ ቅዱስ ሐዋሪያው ጳውሎስ እንደሚለው ከክርስቶስ ጋር ህብረት እንዲኖረን ያደርጋል “የክርስቶስ መንፈስ የሌለው ሁሉ የክርስቶስ አይደለም” (ሮሜ. 8:9)። ከኢየሱስ ጋር ያለንን ግንኙነት እና ወዳጅነት እንዲጠናከር መንፈስ ቅዱስ አዲስ የሆነ የወንድማማችነት መንፈስን እንድንለማመድ ያግዘናል። ዓለማቀፋዊ በሆነ ክርስቶስ ወንድማችን አማካይነት እርስ በእርሳችን አዲስ በሆነ መንገድ ግንኙነት እንፈጥራለን፣ ወላጅ አልባ ልጆች አንሆንም ነግር ግን የአንዱ መሐሪ የእግዚኣብሔር ልጆች እንሆናለን። ይህም ሁሉንም ነገር ይቀይረዋል! ሁላችንም እንደ ወንድም እና እህት በመሆን ልዩነቶቻችን ደግሞ ደስታችን እንዲጨምር በማድረግ ለየት ባለ መንገድ የአባትነትን እና የወንድማማችነትን  ስሜት ያጎናጽፈናል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.