2016-05-17 11:25:00

ኢራቅ፥ ክርስቲያን ተፈናቃዩ ማኅበረሰብ የኩርዲስታ አገር ቅዋሜ የሚደግፍ የአቤቱታ ሰነድ እንዲስማሙበ ግፊት ተደረገበት


ከተሞቻቸው በዳኢሽ አሸባሪው ኃይል መወረር ምክንያት ለቀው የወጡት ለመፈናቀል አደጋ የተጋለጡት የሶሪያ የከለዳውያንና የማሮናዊ ሥርዓት ለምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ባለፉት የመጨረሻ ቀናት በኢራቅ ኩርድስታን ክልል ራስ ገዝ መሆኑ ቀርቶ ነጻ አገረ ኩርድ በሚል ሉእላዊ አገር መረጋገጥ የሚጠይቀው የአቤቱታ ሰነድ እንዲስማሙበትና ፊርማቸውንም እንዲያኖሩበት መገደዳቸው ከክልሉ የሚሰራጩ የዜና ምንጮች የጠቀሰው ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

አምላዋ የተሰየመው ድረ ገጽ የአቤቱታ ሰነድ መሳይ በገጹ ካወጣው ቅርጽ ለመረዳት እንደተቻለውም ፊርማው የሚያኖረው ዜጋ ከመለያ ሥም በተጨማሪም የመታወቂያ ወረቀ መለያ ቁጥር አድራሻና የቴለፎን ቁጥር ጭምር ያካተተ ሲሆን ይኽ ጉዳይ ፈርመርመዋል የሚባለው ዜጋ ለአደጋ የሚያጋልጥ ጭምር መሆኑ ፊደስ የዜና አገግሎት ድረ ገጹን ጠቅሶ ሲያመለክት፥

ኩርዶች የነነዌ ክፍለ ሃገር በኩርድ ነጻውና ራዝ ገዝ ክልል የሚያጠቃል እንዲሆን

በአቤቱታው ሰነድ የኢራቃዊው ኩርድስታን ራስ ገዝ ክልል በአራት አንቀጽ የተከፋፈለ ሲሆን፡ የመጀመሪያው የኩርድስታን ራዝ ገዝ መንግሥት ርእሰ ብሔር የሚል ሞሱል ከዳኢሽ አሸባሪው ኃይል ነጻ ለማወጣት ኩርዶች የሚያካሂዱት የትጥቅ ትግል እንዲፋጥኑ የሚል ሞሶል የነነዌ ክፍለ ሃገር ርእሰ ከተማ ትሆናለች የሚልና በመጨረሻም ኩርድስታን ራዝ ገዝ ክልል መሆኑ ቀርቶ ነጻ ሉአላዊ አገር የሚል ነጥብ ያካተተ መሆኑ አምላዋ ድረ ገጽ የጠቀሰው ፊደስ የዜና አግልግሎ ይጠቁማል።

የነጻነት ጠያቂው ሰነድ መከፋፈልና ሰላማዊ የጋራው ኑሮ ላደጋ የሚያጋልጥ ነው

ክርስቲያን ተፈናቃዎች ፍሪማቸውን እንዲያኖሩበ ከመገደዳቸውም አልፎ ሰነዱ የክልሉ ያለው ፖለቲካ ለውዝግብ የሚዳርግና ከዛ ክልል የተወጣጡ የፖለቲካ በኢራቅ ይሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአባልነት የሚቀመጡትን ክርስቲያን ምእመን ለአደጋ የሚያጋልጥ መሆኑ ሲነገር።  የአሶራውያን ዴሞክራሲያዊው እንቅስቃሴ በመወከል በኢራቅ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑትት ክርስቲያን ምእመን ኢማድ ዩክሃና የኩርድስታን ነጻው አገር የሚጠይቅ የክልሉ ሕዝብ ፈቃድ መግለጫ ነው ተብሎ በመስራጨት ላይ ስላለው ሰነድ የኩርድስታን ራስ ገዝ መንግሥት እንዲያጣራውና ሰነዱ እንዲከወን ሃሳቡንም ያመነጨና ፊርማ የማሰባሰቡ ዘመቻ ያቀነባበረው አካል ተለይቶ እንዲታወቅ ጥልቅ ምርመራ እንዲያካዲድ በማለት ጥሪ ማቅረባቸው ፊደስ የዜና አገልግሎት ገልጦ፥ ሰነዱ ሰላማዊው ያብሮ መኖር ባህል የሚያናጋ ነው በማለት እንደገለጡትም ይጠቁማል።

አቤቱታው ሰነድ በስተጀርባው የሚያጎላው የጥቅምና ፖለቲካዊ  እቅድ ምን ተመስሎ

በአሁኑ ሰዓት ሞሱልና ሰፊው የነነዌ መሬት በአሸባሪው ዳኢሽ ቁጥጥር ሥር እያለ የአቤቱታው ሰነድ እዲፈረም ማድረጉ ከወዲሁ ሰነዱ በስተጀርባው ሞሶልና የነነቨ ሰፊው ክልል ከዳዒሽ እጅ ነጻ ከወጣ በኋላ የሚያንጸባርቀው ፍላጎትና ፖለቲካዊ እቅድ ለመገመቱ እንደማያዳግትም የክልሉ የፖለቲካ ተንታኞች የሚሰጡት አስተያየ የጠቀሰው ፊደስ የዜና አገልግሎ ያመለክታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.