2016-05-17 10:34:00

ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ ኪኮ የሚባለውን የአዕምሮ ዘገምተኞች መኖሪያ ማዕከል ጎበኙ።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በግንቦት 5,2008 በሮም ከተማ አከባቢ የሚገኘውን ኪኮ የሚባለውን በተለያዩ ማሕበራዊ ችግሮች በተለይም በአዕምሮ ዘገምተኛነት ሰላባ የሆኑትን ሰዎች ተቀብሎ የምያስተናግደውን ማዕከል በድንገት መጎብኘታቸው ተገለጸ። ይህ ኪኮ የተባለው ማሕበር በ1964 ጂን ቫየር በተባለ ግለሰብ የተቋቋመ ማሕበር ሲሆን በአሁኑ ወቅትም በ5 አህጉራት ውስጥ በሚገኙ በ30 የተለያዩ ሀገሮች ውስጥ የግብረ ሰናይ አገልግሎት እየሰጠ እንደ ሚገኝም ታውቁዋል።

በሮም የሚገኘው የኪኮ ማዕከል በ1981 የተቋቋመ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም 18 የአዕምሮ ዘገምተኛ የሆኑ ሰዎችን እየተንከባከበ እንደ ሚገኝ ያታወቀ ሲሆን በማዕከሉም የሚኖሮ ሰዎች ነጻ የሆነ ሕይወት እና ደስ የተሰኙበትን ተግባር እየፈጸሙ በጋራ በታላቅ ፍቅር እና ወንዳማማችነት ስሜት እንደ ሚኖሩም ታውቁዋል።

ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ ይህንን የኪኮ ማዕከል በጎበኙበት ወቅት በማዕከሉ ከሚኖሩ ሰዎች ጋር መክሰስ አብረው የተቋደሱ ሲሆን በወቅቱም ከአንድ አንድ ሰዎች ግራ በግል መወያየታቸው እና በእዚህም ድርጊታቸው በማዕከሉ የሚገኙ ነዋሪዎች ከቅዱስ አባትችን ፍራንቸስኮ ጋር ተገናኝተው መነጋገራቸው ከፍተኛ የሆነ ደስታን እንደ ፈጠረባቸውም መግለጻቸውም ታውቁዋል።

ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በእዚህ ጉብኚታቸው ወቅት በማዕከሉ የሚገኘውን የእደጥበብ ማዕከል የጎበኙ ሲሆን በማዕከሉ የሚገኘውን የጸሎት ቤት ጎብኝተው ከኑዋሪዎች ጋር ጸሎት ካደረጉ ቡኋላ ለማዕከሉ የቋሳቁስ እርዳታን ካደረጉ ቡኋላ ወደ ቫቲካን መመለሳቸው ታውቁዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.