2016-05-17 10:25:00

"መንፈሳዊነት ማለት የግድ ለእግዚአብሔር ያለንን ፍቅር በተለያዩ አጋጣሚዎች መግለጽ ብቻ ማለት ሳይሆን መራራት ማለት ነው"


በግንቦት 6,2008  ቅዱስ ልዩ የምህረት ዓመት ኢዩቤሊዩን ምክንያት በማድረግ ለጠቅላላ አስተምህሮ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተገኙ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኚዎች ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ  መንፈሳዊነት ማለት    የግድ ለእግዚአብሔር ያለንን ፍቅር በተለያዩ አጋጣሚዎች መግለጽ ብቻ ማለት ሳይሆን መራራት ማለት ነው ማለታቸው እና ርኅራኄ ከሰባቱ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች አንዱ ነው ማለታቸው ተገለጸ።  

“መንፈሳዊነት የሚለውን ቃል በምንሰማበት ወቅት” አሉ ቅዱስ አባታችን “ሐይማኖተኛ ወይም ለእግዚአብሔር ያለንን ፍቅር መግለጽ ብቻ ተደርጎ ይወሰዳል” ብለው ነገር ግን ይህንን ቃል መረዳት ያለብን ርኅራኄን ማሳየት ወይም ምሕረትን ማድረግ በሚለው ጥልቅ ስንጸ ሐሳብ ላይ ተመስርተን መሆን ይኖርበታል ብለዋል።

መንፈሳዊነት የሚለው ቃል ጽንሰ ሐሳብ በግርኮ-ሮማን ጊዜ ለበላይ አለቃ እራስን ማስገዛት የምለውን ትርጉም ያሰማ ነበር ብለው ይህም ለአማልክት እራስን ማስገዛት እና ልጆች ለቤተሰቦቻቸው እና ለአዛውንቶች እራሳቸውን ማስገዛት  የምለውን ጽንሰ ሐሳብ ያማከለ ትርጉም ነበረው ብለዋል።

ዛሬ ግን መራራት እና መንፍሳዊነት የሚሉትን ቃላት ላለማመሳሰል መጠንቀቅ አለብን ያሉት ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ መንፈሳዊነት በአብዛኛው የእዩኝ እዩኝ ስሜት” ላይ የተመሰረት ነው ብለው በተመሳሳይ መልኩ መራራት የሚለውን ቃል የሰው ልጆች በተለያዩ መከራዎች ላይ መሆናቸውን ችላ በማለት በአንጻሩም ለቤት እንስሳቸው የምያሳዩት እንክብካቤ ወይም ደግነት ተደርጎ ሊወሰድ አይገባውም ብለዋል።

በቅዱስ ወንጌላችን ውስጥ እንደ ምንመለከተው ኢየሱስ ለምሕረት ጥያቄዎች እና ልመናዎች ከፍተኛ ትኩረትን ይሰጥ እንደነበር ማስተዋል ይቻላል ብለው ኢየሱስ ሰብዓዊ ፍላጎቶችን በተመለከተ ለሚቀርቡለት ጥያቄዎች በርዕራኄ እና በፍቅር መልስ ይሰጥ እንደነበረ ገልጸው ዛሬም እኛ በኢየሱስ እና በቃሉ በምንታመንበት ወቅት  የፈውስ ተአምራት በሕይወታችን ያደርጋል ብለዋል።

ኢየሱስ ለሚለምኑት እና ወደ እርሱ ለሚቀርቡለት ለቅሶዎች ሁሉ በርኅራኄ መልስ እንደ ሚሰጥ እኛም ዛሬ ያሳየንን መልካም ተግባር በመላበስ ቸልተኝነትን እና ልዩነቶችን አስወግደን ለወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ፍላጎቶች መልስ መስጠት ይገባናል ብለዋል።

ቅዱስነታቸው በማከልም የምሕረት እናት የሆነችው እናታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም በእዚህ ቅዱስ ልዩ የምሕረት ዓመት የልጇን የኢየሱስ ክርስቶስ ርኅራኄን ተላብሰን ለተቸገሩት ርኅራኄን ማሳየት እንድንችል ትረዳን ዘንድ በእርሷ አማላጅነት ጸሎታችንን እናቀርባለን ብለው “ከሙታን የተነሳው ጌታ እናንተን እና ቤተሰቦቻችሁን  በምሕረታዊ ፍቅሩ ይጎበኛችሁ ዘንድ እማጸናለሁ ሁላችሁንም እግዚኣብሔር ይባርካችሁ ካሉ ቡኋላ ሰላምታን አቅርበው የእለቱ ዝግጅት ተጠናቁኋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.