2016-05-07 10:42:00

በታላቅ መከራ ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን ለማጽናናት በማሰብ “እንባን ማበስ” በሚል አርዕስት በተዘጋጀው የጸሎት ስነ-ስረዓት ላይ ቅዱስንታቸው መገኘታቸው ተገለጸ።


በሚያዚያ 27,2008 እንደ አውሮፓዊያን የላቲን ስርዓተ ሉጥርጊያ ደንብ መሰረት የተከበረውን የክርስቶስ ዕርገት በዓልን ምክንያት በማድረግ በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚልካ በተዘጋጀው እና ትኩረቱንም በታላቅ መከራ ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን ለማጽናናት በማሰብ “እንባን ማበስ” በሚል አርዕስት የተዘጋጀ የጸሎት ስነ-ስርዓት በቅዱስ አባታችን መሪነት መከናወኑ ተገለጸ።

በእለቱ በጣልያን ከምትገኘው የሲራኩዛ ከተማ የመጣ የአዛኝቱ ማሪያም ምስል የተገኘ ሲሆን በተጨማሪም ተጋባዢ የነበሩ የአንድ ቤተሰብ አባል እና ሁለት የተለያዩ ግለሰቦች ምስክርነት መስጠታቸው የታወቀ ሲሆን በጣም አስቸጋሪ በሚባል ችግር ውስጥ ተዘፍቀው እንደ ነበረ እና ልዩ እገዛ ስለተደረገላቸው ከእዚህ ከፍተኛ ሊባል ከሚችል ችግራቸው ማገገማቸውን ለተሰብሳቢው አስረድተዋል።

ከምስክርነቱ በመቀጠል ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በእለቱ በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ለተሰበሰቡ ምዕመናን “አሁን የሰማነው ምስክርነት መመልከት ያለብን ለመከራችን ትርጉምን በሚሰጠው በእግዚአብሔር ቃል ላይ ተመስርተን ሊሆን ይገባል ብለው በቅድሚያ ግን መንፈስ ቅዱስ በመኋከላችን ይሆን ዘንድ እና አዕምሮኋችንን እንዲያበራ፣ ትክክለኛውን የመጽናኛ ቃል እንዲያጎናጽፈን፣ በእርግጠኛነት በመከራችን ጊዜ ሁሉ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር እንደ ሚሆን እና በመከራችን ጊዜ ሁሉ ብቻችንን እንደማይተውን እንገነዘብ ዘንድ ልባችንን እንዲከፍትልን ልንጋብዝ ያስፈልጋል በማለት የእለቱን ንግግራቸውን ጀምረዋል።

ቅዱስነታቸው በመቀጠል “ጌታ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ ብቻቸውን እንደ ማይተዋቸው ቃል ገብቶላቸው እንደነበር” ገልጸው “በሕይወታቸው ዘመን ሁሉ አጽናኝ የሆነውን መንፈስ ቅዱስን በመላክ ይረዳቸው፣ ይደግፋቸው፣ በተጨማሪም ያጽናናቸው እና አለኝታነቱን ይገልጽላቸው እንደነበረ” ገልጸዋል።

“በሐዘናችን፣ በስቃያችን፣ በህመማችን ወቅት ሁሉ እና በስደት እና በጭንቀት ውስጥ እየኖሩ ያሉ ሰዎች ሁሉ የመጽናኛ ቃል ያስፈልጋቸዋል” በማለት ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “በእነዚህ የመከራ ጊዜያት ሁሉ አጠገባችን የሚሆን  እና የምያዝንልን አንድ ኋይል አስፈላጊ መሆኑ ይገባኛል” ብለዋል። “በእነዚህም ወቅቶች ሁሉ መንገድ መሳት እና ግራ መጋባት ማለት ምን እንደሆነ እንማራለን፣ ከመቼው ጊዜ በበለጠ ልባችን አይተነው በማናውቀው መልኩ ይናወጣል” ብለዋል።

“ምን ያህል ሐዘን ነው በዓለም ዙሪያ በሚገኙ የሰዎች የፊት ገጽታ ላይ የምንመለከተው! ምን ያህል ሰዎች ናቸው በየቀኑ በዓለም ዙሪያ እያነቡ የሚገኙ፣ ሁሉም የተለያየ ዓይነት እንባ ብያነቡም ቅሉ፣ ሁሉም ግን የምያነቡት ምሕረትን፣ ርኅራኄን እና መጽናናትን ለማግኘት ይጮኻሉ” ብለው “ከሁሉም በላይ መራር የሆነው ለቅሶ የሚመነጨው የሰው ልጆች በሚፈጽሙት አስከፊ ተግባር ምክንያት ነው” ካሉ ቡኋላ “የሚወዱዋቸው ሰዎች በጦርነት በሞት ሲነጠቁ  አያቶች፣ ቤተሰቦች እንዲሁም ልጆች የምያነቡት መራር እንባ ምሕረት እና መጽናናትን ከጌታ ያስፈልጋቸዋል ሁላችንም ሐዘን ላይ ለሚገኙ ቤተሰቦች እግዚአብሔር እንባቸውን ከዓይናቸው ያብስ ዘንድ ልንጸልይ ያስፈልጋል” ብለዋል። 

በሕመማችን ጊዜ ሁሉ ብቻችንን አይደለንም ምክንያቱም ኢየሱስ ሐዘን ምን መሆኑን በደንብ ስለሚረዳ” ያሉት ቅዱስ አባታችን “በቅዱስ ወንጌላችን እንደ ተጠቀሰው ማሪያም በወንድሟ ዓላዛር መሞት ምክንያት በሐዘን ላይ በነበረችበት ጊዜ ኢየሱስም በሐዘን እንዳነባ እና ዓላዛርን ከሞት በማስነሳት ሐዘኑዋን ወደ ደስታ እንደ ቀየረው፣ በተጨማሪም ኢየሱስ እራሱ እንደ ተሰቃየ እና እንደ ሞተ፣ በይሁዳ እና በጴትሮስ እንደ ተካደ የሚያሳየው የሰው መከራ እና ችግር ምን መሆኑን ጠንቅቆ ማወቁን ነው” ብለዋል።

“ኢየሱስ ለእኛ የሚያነባው እንባ ችግራችንን ለማርከስ ይችላል” ያሉት ቅዱስ አባታችን “ በመከራችን እና በለቅሶኋችን ጊዜ ሁሉ ወደ ኢየሱስ መጮኽ ይሳፈልጋል ምክንያቱም ጸሎት ለመከራችን ሁሉ ፍቱ መድኋኒት እና የእግዚአብሔርን አጋርነት እንዲሰማን የሚያደርግ በመሆኑ፣ የእርሱ ቃል አጽናኝ በመሆኑ እና ደጋፊ ስለሆነ፣ ኢየሱስ በዓላዛር መቃብር ፊት ለፊት ቆሞ ‘አባት ሆይ ስለሰማህኝ አመሰግናለው፣ ሁል ጊዜም ቢሆን እንደ ምትሰማኝ አውቃለሁ’ ብሎ እንደ ጸለየ እኛም በተመሳሳይ መልኩ ለእግዚአብሔር አባታችን ጸሎታችንን ማቅረብ ይገባናል” ብለዋል።

በመጨረሻም በማንኛውም መስቀል ስር የኢየሱስ እናት በእዚያ ትገኛለች ብለው በካባዋ እንባችንን ታብሳለች በማይታጠፈው እጆችዋ ከመከራችን ታነሳናለች በተስፋ ጎዳና ላይ እንድንራመድ ትደግፈናለች በማለት ንግግራቸውን አጠናቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.