2016-05-06 16:56:00

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፥ በብራዚል ተከስቶ ያለው ቀውስ በሰላማዊ መንገድ እዲፈታ አደራ ይላሉ


የብራዚል ርእሰ ብሔር ዲልማ ሩሰፍ ከቢቢሲ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ በማጭበርበርና ሥልጣን ለግል ጥቅም አውለዋል በሚል ክስ በአገሪቱ ተከስቶ ያለው የኤኮኖሚ ቀውስ ገሃድ ሆኖ እንዳይገለጥ ሥልጣናቸውን  ለኃሰት መሣሪያ ተጠቅመዋል የሚል ክስ በኃሰት ላይ የተገነባ ተጨባጭ ያልሆነ ክስ ነው በማለት። እየቀረበባቸው ካለው ክስ ሁሉ ነጻ ነኝ ብለዋል።

የብራዚል የሕግ መወሰኛው የበላይ ምክር ቤት እ.ኤ.አ. ግንቦት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ርእሰ ብሔሯ በሕግ ይከሰሱ ወይህም አይከሰሱ በሚለው ውሳኔ ድምጽ እንዲሰጥ የተጠራ መሆኑ ለማወቅ ሲቻ። የሕግ የመወሰኛው የበላይ ምክር ቤት ውሳኔውን ካጸደቀው ርእሰ ብሔሯ ለ180 ቀን ከሥልጣናቸው እንደሚገለሉ ከወዲሁ ሲገለጥ ሆኖም ርእሰ ብሔር ሩሰን የሕግ መወሰኛው የበላይ ምክር ቤት ድምጽ እንዲሰጥ ያስጠራው በሳቸው ላይ እየቀረበ ያለው ክስ  መረጃ የሌለው ሕገ ወጣዊ ተግባር ነው በማለት ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ገልጠዉታል፡

በብራዚል ተከስቶ ያለው ፖለቲካዊ ቀውስ በማስመከትም በብራዚል የሪዮ ደጃነይሮ ሊቀ ጳጳሳት ብፅዕ ካርዲናል ዥዋው ተምስታ እ.ኤ.አ. ግንቦ 5 ቀን 2016 ዓ.ም. ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ጋር ባካሄዱት ግኑኝነት የአገራቸው ወቅታዊ ሁኔታ በማስመልከት ከቅዱስ አባታችን ጋር መወያየታቸው ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ገልጠው፥ ቅዱስነታቸው የብራዚል ወቅታዊው ሁኔታ በቅርብ እየተከታተሉ መሆናቸውና የተከሰተው ቅውስ በውይይት እንዲፈታ ጥሪ በማቅረብም ስለ ብራዚል እንደሚጸዩም እንዳረጋገጡላቸው ጠቅሰው፡ የዚህ አይነቱ ርእሰ ብሔሩ በሕግ ተከሰው ለ 180 ቀናት ከሥልጣናቸው ተገለው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እንዲከታተሉ የማድረጉ የሕግ መወሰኛው የበላይ ምክር ቤት ውሳኔ ከጸደቀ። የዚህ አይነቱ ውሳኔ ሲተገበር ባገሩቱ በርእሰ ብሔር ኮሎር ደ መሎ ላይ ነው የተላለፈ ውሳኔ በማስታወስ ለሁልተኛ ጊዜ እንደሚሆን ነው ብለው።  በአሁኑ ወቅት በብራዚል የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ተከስቶ ያለው ፖለቲካዊ ቀውስ በሰላማዊ መንገድ መፍትሔ እንዲያገኝ ጥሪ በማቅረብ ብቻ ሳይሆን የሕዝብ ህሊን በማንቃቃትና በማነጽ ስለ ብራዚል እንደትጸልይም አረጋግጠው ህዝብ መቼም ቢሆን ተስፋውን እንዳያጨልም አደራ በማለት አብራ በመጓዝ የሚያስፈራው መውደቅ ሳይሆን ወድቆ መቅረት መሆኑ ታስገነዝባለች ሲሉ ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.