2016-05-04 16:46:00

የቅዱስ ዓመት አዋጅ ሰነዶች ለትርኢት


እ.ኤ.አ. እስከ ሐምሌ ወር የሚዘልቅ ቅዱስ ንግደት በሚል ርእስ ሥር የሮማ የመንፈሳዊ ንግደት ተንከባካቢ ማኅበር ከአገረ ቫቲካን ዝግ ቤተ መዝገብ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ከር.ሊ.ጳ. ቦኒፋዚዮ ስምንተኛ ጀምሮ እስከ ቅዱስ አባታችን ር.ሊጳ. ፍራንቸስኮ የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ዓመት የአዋጅ ሰነዶች ትርኢት እ.ኤ.አ. ግንቦት 3 ቀን 2016 ዓ.ም. በይፋ መከፈቱ የቫቲካ ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ዳኔለ ጋራሊያኖ ገለጡ።

የተለያዩ ቅዱሳን ዓመታት አዋጅ በብራና በአርእስተ ሊቃነ ጳጳሳት እጅ ጽሑፍ የተደነገጉ ከቦኒፋዚዮ ስምንተኛ ወዲህ የታወጁት ኵላዊት ቤተ ክርስቲያን የኖረቻቸው ቅዱሳን አመታትና ዋና መርሆአቸው ያካተተ ትርኢት እንደሚሆንም ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ቃለ ምልልስ ያካሄዱት የሮማ መንፈሳዊ ንግደት ጉዳይ የሚከታተለው ማኅበር አስተዳዳሪ ብፁዕ አቡነ ሊበኢሪዮ አንድረአታ ገልጠው፥ ይኽ ትርኢት ለሁሉም በቤተ ክርስቲያን የተኖሩት የቅዱሳን አመታት ታሪክ ለመረዳት እንዲችል የሚደግፍ እያንዳንዱ የቅዱስ አመት አዋጅ በተለያየ ወቅት የተኖረ ንዲታወጅ ያደረገው መሠረተ ምክንያቱ የሚያመለክትና ቤተ ክርስቲያን የድህነት እቅድ በተለያየ ወቅት በቅዱስ አመት አዋጅ አማካኝንት እንዴት እንደገለጠችውና እንዳበሰረቸውም የሚመሰክር ትርኢት ነው ብለዋል።

የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ አንድ ቅዱስ አመት ሲያውጁ የማዳን እቅድ በጊዜ በማንበብ በሰው ልጅና በእግዚአብሔር መካከል ግኑኝነት እንዲታደስና ሰው በዚህ ምድር ተጓዥና እንግዳ መሆኑ እንዲያስተውል የሚደግፍ የንግደት መንፈስ የሚያነቃቃ ተጓዥ ወይን ነጋዲ መሆን ያለው ትርጉም ልብ እንዲል የኃጢአት ሥርየት የሚጸግው ዳግም ለኅዳሴና ወደ እግዚአብሔ መመለስ የሚያነቃቃ ነው ብለው ከዚህ የትርኢቱ  ዓላማ ጋር በማያያዝም ወጣት ትውልድ በሕይወት መኖር በእድሜ ገደብ አጥሮ ነዋሪ ነኝ ብሎ ገዛ እራሱን እንዳያታልል ቅዱስ ዓመት የሚያቀርበው ጥሪ ለየት ባለ መልኩ ያመለከተዋል። ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ሲያቋቁሙ አለ ምክንያታ አልነበረም፡ በዚህ መርሐ ግብር መሠረትም ወጣቱ ትውልድ ዓለም አቀፋዊ የወጣቶች ቀን በሚካሄድባቸው አገሮች በየሁለት ዓመት አንዴ ወደ ተለያዩ አገሮች ነጋዲ በመሆን በመጓዝ ቅዱሳት ሥፍራዎች በመጎብኘት የቤተ ክርስቲያን ኵላዊነት በዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን በሚገኙት በቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሥር በመሰባሰብ እይኖረ በእምነት እንዲነቃቃ አድርጎታል።

እምነት ተጓዥ ነው፡ ተቁሞ የሚኖር አይደለም። ይኽ ደግሞ ሐዋርያዊነትን ያመለክታል፡ ሁሉም እንደሚያውቀውም በቅዱሳት ዓመት ምክንያት ቤተ ክርስቲያን እያንዳንዱ በጥሪው አማካኝነት በማሰባሰብ ቅዱስ ዓመትና ጥሪው መካከል ያለው ግኑኝነት በማብራራት ሁሉም ከኣግዚአብሔር ምህረት የተቀበለው ጥሪ አማካኝነት ከእግዚአብሔር ጋር ያለው ግኑኝነት በተግባር መግለጫ ከሚሆነው ከገዛ እራሱ ከጎረቤቱ ጋር በመገናኘትእምነቱን ለመመስከር የሚደገፍ አዋጅ ነው በማለት ያካሄዱት ቃል ምልልስ አዚህ ላይ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.