2016-05-04 16:41:00

ዓለም አቀፋዊ ዓውደ ጥናት፥ ተቀባይነት ያለው ልማትና የሥራ መጻኢ


ጳጳሳዊ የፍትህና ሰላም ምክር ቤት ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ልማትና የሥራ መጻኢ በሚል ርእስ ሥር ያዘጋጀው ግንቦት 5 ቀን 2016 ዓ.ም. የሚጠናቀቀው ዓውደ ጥናት እ.ኤ.አ. ግንቦት 2 ቀን 2016 ዓ.ም. ከቀትር በኋላ መጀመሩ ቀደም ተብሎ መገለጡ የሚታወስ ሲሆን፡ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ግንቦት አንድ ቀን 2016 ዓም. እኩለ ቀን በአጸደ ቅዱስ ጴጥሮስ ጸሎት ንግሥተ ሰማይ ከማሳረጋቸው አስቀድመው የለገሱት አስተንትኖ እንዳጠቃለሉ ይኸንን ጳጳሳዊ የፍትህና ሰላም ምክር ቤት ያዘጋጀው ዓለም አቀፋዊ  ዓውደ ጥናት አስታውሰው፥ ሥራ የሰው ልጅ ክብር መግለጫና በእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ የሰው ልጅ ያለው ሱታፌ በማረጋገጥ በዚሁ አማካኝነትም የእግዚአብሔር የፈጣሪነት ተግባር ቀጣይነቱ ለማረገጥ የሚቻለው ሥራ የሰው ልጅ ክብር መለጫ ሲሆንና ተቀባይነት ያለው የልማት እቅድ ሲተገብር መሆኑ እንዳሰመሩበትና በዚያኑ ዕለትም ትዊተር በተሰየመው ማኅበራዊ ድረ ገጽ አማካኝነትም ሥራ አጥነት ወጣት ትውልድ በከፋ ደረጃ ሲያጠቃና የሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ክብር የማያከብር የሥራ ዓይነት መስፋፋት የሚከስተው ችግር ምንኛ አደገኛ መሆኑ ያስገነዝበናል የሚል ሃሳብ የሚያስተጋባ መልእክት አስተላልፈው እንደነበም ሲገለጥ፡ የፍትኅና ሰላም ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካዲናል ፒተር ቱርክሶን ልጉባኤው ባስደመጡት ንግግር፥

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ምኅዳርና ድኽነት (ድኾች) የተሰኙት ሁለት አንገብጋቢ ጉዳዮች እንዳሉ ይናገራሉ። በአሁኑ ሰዓትም ሥራ ሌላ ተጨማሪ አንገብጋቢ ጉዳይ ከሚባሉት ውስጥ የሚጠቀስ ሆኗል። የዓለም ትኵረቱ ትርፍ የሚል ሲሆን። እንድ ግብ የሚያስቀምጠውም ትርፍ በመሆኑ ሰብአዊ ፍጡር አስተማማኝነ በሌለው ሁኔታ እንዲጠቃ አድርገዋል፡ የሥራ ክብር እንዴት ለሁሉም ለማስጠበቅ። ዋስትናና መረጋጋጥ ሥራ በኅብረተሰብ ዘንድ እንዴት በማድረግ ነው የሰላም ገጠመኝ እንዲሆን ለማድረግ የሚቻለን?  የሚለውን ጥያቄ ብፁዕነታቸው በማቅረብ ይኽ ደግሞ የዚህ ዓውደ ጥናት ዋነኛው ምክንያትም ለእነዚያ ጥያቄዎች መልስ ማፈላለግ የሚል ሃሳብ ለማስተግባት አልመው መሆናቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ሚከለ ራቪይርት ገለጡ።

በኢጣሊያና በሳን ማሪኖ ለዓለም አቀፍ የሥራ ድርጅት ተጠሪ ጃኒ ሮሳስ ባስደመጡት ንግግር ምንም’ኳ በ 21ኛው ክፍለ ዘመን የምንገኝ ብንሆንም አሁንም ሥራ የባርነት ባህርይ እየተላበሰ የሰብአዊ መብትና ክብር ማእከል የማይደርግ ሆኖ ይታያል፡ ይህ ችግር የነበረ ብቻ ሳሆን በዚህ በበለጸገው ዓለም መልኩና አካሄዱ ቀይሮ በተራቀቀ መንፈስ የሚከሰት አቢይ ችግር ሆኗል፡ በአሁኑ ሰዓት በዓለማችን 400 ሚሊዮን የሚገመቱ ሠራተኞች በሚያገኙት ክፍያ ይቅር ቤተሰቦቻቸው ገዛ እራሳቸውንም ለማስተዳደር የማይችሉ ሆነው ሥራ ያላቸው ቢሆኑም ቅሉ በድኽነት የሚኖሩ ሆነዋል እንዳሉ ዓውደ ጥናቱን በመከታተል ላይ የሚገኙት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ሚከለ ራቪያርት አስታወቁ።

ብፁዕ ካርዲናል ቱርክሶን ባስደመጡት ምዕዳንም ሄንርይ ፎርድ፥ የገንዘብ ኃብት ገቢና ወጪ የማሥተዳዳር ዘይቤ እያንዳንዱ ሰው የጋራ ጥቅም በማረጋገጡ ሂደት የሚደግፍ መሆን አለበት ሲል የተናገረውን ቃል ጠቅሰው ስለዚህ ልማት ዙሪያ ልዩ ራእይ ያላቸው፡ ሃሳብ ያላቸው ዜጎች መዋዕለ ንዋይ የማኘት እድል ሊኖራቸው ይገባል። የዚህ አይነቱ አሠራር የሥራ እድል ይፈጥራል። ባለ ሀብቶች ባለ ተላልቅና ተናንሽ ኢንዳስትሪዎ ባለ ንብረት የሆኑት አዳዲስ የሥራ ዕድል ለመፍጠር እንዲችሉ መደገፍ ይኖርባቸዋል፡ እነርሱም በተራቸው ትርፍ ብቻ ከሚለው ኤኮኖሚያዊ እሳቤ ተላቀው ሰብአዊነት ማእክል ሊያደርጉ ይገባል እንዳሉ ራቪያርት አስታወቁ።

ጀነቭ ለሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ለዚያ የተለያዩ የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን የተራድኦ ማኅበራትና የተለያዩ ካቶሊካውያን የተራድኦ ማኅበራት ለሚያቅፈው ካሪታስ ኢንተርናዚዮናሊስ ማኅበር ልኡክ ብፁዕ አቡነ ሮበርቶ ቪቲሎ በአሁኑ ወቅት በዓለማችን በሚገባ የተሰናዱ ምሁራን በተለያየ ዘርፍ የሰለጠኑ ጭምትና ልባም ወጣቶች ሥፍር ቁጥር የላቸውም ሆኖም በሥራ አጥነት የተጠቁ ናቸው። በመሆኑም በዓለም የሚታየው የሥራ አጥነት ችግር ለመቅረፍ  እግርብ ላይ እየዋለ ያለው የሥራ ፖለቲካና የሥራ ኤኮኖሚ ሰብአዊነት ማእከል ባደረገ በሥነ ምግባር የተካነ አመለካከት ሊታደስ ይገባዋል የሚል ሃሳብ በአጽንዖት ያሳሰበ ንግግር ለጉባኤው ማስደመጣቸው ራቪይርት ገለጡ።

ይኽ በእንዲህ እንዳለም በዚህ እ.ኤ.አ. ግንቦት 2 ቀን 2016 ዓ.ም. ከቀትር በኋላ በተጀመረው ዓውደ ጥናት ከተለያዩ አገሮች የተወጣጡ የሥነ ሥራ ሊቃውንትና የሥራና ሠራተኛ ጉዳይ አጥኚዎች በጠቅላላ 100 ተጋባእያን እየተሳተፉ  ሲሆን የሥራ ዓለም ወጣቶች የሥራ መብት የሥራ ሥነ ምግባርና ክብር ማኅበራዊ ሰላምና ፍትህ እንዲሁም እድገት በተሰኙት ንኡሳን እርእስቶች ዙሪያ በቡድን በመከፋፈል ሰፊ የክብ ጠረጴዛ ውይይት እየተካሄደ ሲሆን፡  ዓውደ ጥናቱ ስለ ሥራ ዓለምና የሥራ ጉዳይ በተመለክተ የሚፈጠረው ችግር እንዲሁም የሥራውን ዓለም ለማሻሻል ይደግፋሉ  መፍትሔ ይሆናሉ የሚባሉት ጽንሰ ሐሳቦች ዙሪያ ሰፊ ውይይት እየአካሄደ መሆኑ ራቪያርት ያመለክታሉ።








All the contents on this site are copyrighted ©.