2016-05-04 16:36:00

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. አዲስ የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡክ ሰየሙ


የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡክ አማካሪ በመሆን ቅዱስ አባታችንን በማገልገል ላይ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ኩሪያን ማቲው  ቫያሉንካል ወደ ሊቀ ጳጳሳነት ምዕርግ ከፍ በማድረግ በሙሉ ሕጋዊ መብት በፓፑዋ ኒው ጊኒ የቅድስ መንበር ሐዋርያዊ ልኡክ እንዲሆኑ እ.ኤ.አ. ግንቦት 3 ቀን 2016 ዓ.ም. በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ መሰየማቸው የቅድስት መንበር የዜናን ኅትመ ክፍል መግለጫ አስታወቀ።

ብፁዕ አቡነ ቫያሉንካል እ.ኤ.አ. ነሐሴ 4 ቀን 1966 ዓ.ም. በአገረ ህንድ በምትገኘው ቫዳቫቱር ከተማ የተወለዱ እ.ኤ.አ. ታህሳስ 26 ቀን 1991 ዓ.ም. በካታቫም ሰበካ ማዕርገ ክህነት ከቀበሉ በኋላ በሕገ ቀኖና ሊቅነት አስመስክረው ከሰነ 13 ቀን 1998 ዓም. በቅድስት መንበር ዲምሎማሲያዊ ጉዳይ ሥር በመታቀፍ ማገልገል ከጀመሩ በኋላ በጊኒ በኮርያ በረፓብሊካዊት ዶመኒካና በባንግላደሽ በሃንጋሪና በግብጽ በሚገኙት የቅስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡካን መዋቅር ሥር በመታቀፍ እንዳገለገሉ ያስታወሰው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አያይዞ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ቫያሉንካል ህንድኛ ታሚል ማላያላም ስፓንኛ እንግሊዝኛ ጣልያንኛ ፈረንሳይኛና ጀርመንኛ ቋንቋ ጠንቅቀው እንደሚያውቁ ያመለክታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.