2016-05-02 15:53:00

ዓለም አቀፋዊ ዓውደ ጥናት፥ ተቀባይነት ያለው ልማትና የሥራ መጻኢ


ጳጳሳዊ የፍትህና ሰላም ምክር ቤት ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ልማትና የሥራ መጻኢ በሚል ርእስ ሥር ያዘጋጀው ግንቦት 5 ቀን 2016 ዓ.ም. የሚጠናቀቀው ዓውደ ጥናት እ.ኤ.አ. ግንቦት 2 ቀን 2016 ዓ.ም. ከቀትር በኋላ መጀመሩ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዚጠኛ አሊና ቱፋኒ ገለጡ።

ቅዱስ አባታን ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ግንቦት አንድ ቀን 2016 ዓም. እኩለ ቀን በአጸደ ቅዱስ ጴጥሮስ ጸሎት ንግሥተ ሰማይ ከማሳረጋቸው አስቀድመው የለገሱት አስተንትኖ እንዳጠቃለሉ ይኸንን ጳጳሳዊ የፍትህና ሰላም ምክር ቤት ያዘጋጀው ዓለም አቀፉ ዓውደ ጥናት አስታውሰው፥ ሥራ የሰው ልጅ ክብር መግለጫና በእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ የሰው ልጅ ያለው ሱታፌ በማረጋገጥ በዚሁ አማካኝነትም የእግዚአብሔር የፈጣሪነት ተግባር ቀጣይነቱ ለማረገጥ የሚቻለው ሥራ የሰው ልጅ ክብር መለጫ ሲሆንና ተቀባይነት ያለው የልማት እቅድ ሲተገብር መሆኑ እንዳመለከቱ ያስታወሱት ልእክት ጋዜጠኛ ቱፋኒ አያይዘው፥ ይኽ ጳጳሳው የፍትሕና ሰላም ምክር ቤት ከዓለም አቀፍ የሥራ ድርጅት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ዓውደ ጥናት ዓላማው የቤተ ክርስቲያን ማኅበራዊ ትምህርት የተከበረ ሥራና የሥራ ክቡርነት ሥር የሚሰጠው ትንተናና ጽንሰ ሓሳብ በጥልቀት ለመመልከትና ብሎም የተከበረ ሥራ ትርጉምና የክቡር ሥራ ቅዋሜ የሚያረጋግጡት ባህርያትና  መሠረታውያን ነገሮች ለይቶ የሚተነትን መሆኑ ጳጳሳዊ የፍትና ሰላም ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ፒተር ቱርክሶን ዓውደ ጥናቱን በማስመለክት በሰጡት ጋዜጣዊ መለጫ እንዳብራሩ ገልጠዋል።

ብፁዕ ካርዲናል ቱርክሶን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፥ ዓውደ ጥናቱ የተዘጋጀው እ.ኤ.አ. ግንቦት አንድ ቀን ታስቦ የሚውለው ዓለም አቀፍ የሠራተኞ ቀንና ኵላዊት ቤተ ክርስቲያን በተመሳሳይ ቀን የምታከብረው የቅዱስ ዮሴፍ ሠራተኛ ዓመታዊ በዓል ምክንያት በማድረግ መሆኑ በመግለጥ፡ ብፁዕነታቸው ግንቦት አንድ ቀን ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ ባስደመጡት ስብከት፥ ሥራ እግዚአብሔር ለሰው ልጅ የሰጠው ኃላፊነት ሲሆን። በእግዚአብሔር የማዳን እቅድ ዙሪያ ሲጤን ያለው እውነተኛው ትርጉሙንና ያለው ክብር ሊስተዋል እንደሚቻልም በስፋት ማብራራታቸው ቱፋኒ ያመለክታሉ።

በዚህ እ.ኤ.አ. ግንቦት 2 ቀን 2016 ዓ.ም. ከቀትር በኋላ በተጀመረው ዓውደ ጥናት ከተለያዩ አገሮች የተወጣጡ የሥነ ሥራ ሊቃውንትና የሥራና ሠራተኛ ጉዳይ አጥኚዎች በጠቅላላ 100 ተጋባእያን እየተሳተፉ ሲሆን፡ ግንቦት 3 እና 4 ቀን 2016 ዓ.ም. የሥራ ዓለም ወጣቶች የሥራ መብት የሥራ ሥነ ምግባርና ክብር ማኅበራዊ ሰላምና ፍትህ እንዲሁም እድገት በተሰኙት ንኡሳን እርእስቶች ዙሪያ በቡድን በመከፋፈል ሰፊ የክብ ጠረጴዛ ውይይት እንደሚካሄዱና በመቀጠልም ውይይትና ዓውደ ጥናቱ ስለ ሥራ ዓለምና የሥራ ጉዳይ በተመለክተ የሚፈጠረው ችግር እንዲሁም የሥራውን ዓለም ለማሻሻል የሚቀርቡት አዳዲስ መፍትሔ የሚባሉት ጽንሰ ሐሳቦች ዙሪያ ሰፊ ውይይት እንደሚያካሂድ ልእክት ጋዜጠኛ ቱፋኒ አስታውቀዋል። 








All the contents on this site are copyrighted ©.