2016-05-02 15:44:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፥ ሌላው መደገፍ የሰላም መልእክት ነው


የምኅረት ዓመት ምክንያት በማድረግ እ.ኤ.አ. ሚያዚያ 30 ቀን 2016 ዓ.ም. ከተለያዩ አገሮች የተወጣጡ የመከላከያ ኃይል አባላትና ጡረተኞች አባላት በቤተሰቦቻቸው ተሸኝተው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ጋር ተገናኝተው መሪ ቃል መቀበላቸው የቫቲካ ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ዳኒኤለ ካርጋሊያኖ ገለጡ።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በለገሱት ምዕዳን የመከላከያ ኃይል አባላት ሥራ የሰላም አገልጋይ ነው የሚለውን ሃሳብ እንዳሰመሩበት የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ካርጋሊያኖ አያይዘው፥ ያንን እኔ እንዳቀርኳችሁ እናንተም እርስ በእርሳችሁ ተፋቀሩ የሚለው ወንጌላዊ ቃል ላይ በማተኵር፡ ሁሉም ሰላም ፍትሕና ፍቅር በመገንባቱ ረገድ ኃላፊነት እንዳለበትም አሳስበው፡ የመከላከያ ኃይል አባላት በዓለም እርቅ እንዲሰፍን የሚያገለግሉ የሰላም መሣሪያ እንዲሆኑ የተጠሩ መሆናቸው ቅዱስታቸው በአጽንኦት የገለጡ የመከላከያ ኃይል ትርጉመ ሃሳቡን ያንን ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ከመላ አለም የተወጣጡ የመከላከያ ኃይል አባላት በሁለት ሺሕኛው ቅዱስ ዓመት ምክንያት ተቀብለው በለገሱት ምዕዳን የመከላከያ ኃይል አባላት የሕዝቦች ጸጥታና ደኅንነት እንዲሁም የሕዝቦች ነጻነት የሚያስጠብቁ ሰላም ገንቢዎች ሲሉ የገለጡት ሃሳብ የሚያስታውስ ሲሆን። ለያይ የግንብ አጠር ሳይሆን አገናኝ ድልድይ ገንቢዎች እንሁን በማለት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በመደጋገም በተለያየ ወቅት የሚብራሩት ሃሳብ ሁሉም እንደ ጥሪው አማካኝነት ይኸንን ዓይንቱን ግኑኝነት እግብር ላይ ሊያውለው እንደሚገባም በሰጡት ምዕዳን ደግመው ያሳሰቡት ሃሳብ ሲሆን፡ የመከላከያ ኃይል አባላት ተልእኮ ሰላም መገንባት ነው፡ ትምህርት ቤቶች ማከሚያ ቤቶች የመጓጓዣ መንገዶች የመሳሰሉት የሕዝቦች አገልግሎት መስጫ መዋቅሮች በማስፋፋት በተለያዩ ድኾች አግሮች የሚገኙትን ታማሚዎች ለከፍተኛ ህክምና ወደ ምዕራቡ ዓለም እንዲላኩ በማድረጉ ሂደት ባጠቃላይ በሰብአዊነት ግንባታ ዘርፍ አቢይ አገልግሎ የሚሰጡ መሆናቸው እዛው የቅዱስ አባታችን ምዕዳን ለመቀበል ከተገኙት ውስጥ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር በካሄዱት ቃለ ምልልስ ያስተጋቡት ሃሳብ መሆኑ  የቫቲካ ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ዳኒኤለ ካርጋሊያኖ ገልጠው፡ በአሁኑ ሰዓት የሚታየው የስደኛው ጸአት በተለይ ደግሞ በባህር ጉዞ በኩል የሚሰደዱት በጉዞ እያሉ ከሚያጋጥማቸው የሞት አደጋ ለማትረፍ በሚሰጡት የፈጥኖ ደራሽ አገልግሎት  የባህር ድንበር አስከባሪ የባህር ኃይል አባላት የሚሰጡት አገልግሎት የሚደነቅ መሆኑ በተለያየ ወቅት በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በተለያዩ የሃይማኖት መሪዎችና የመንግሥታት መሪዎች ጭምር እንደሚገለጥም ቃለ  ምልልስ ያካሄዱት በማስታወስ የመከላከያ ኃይል አባላት ተልእኮ የምንኖርበት ዓለም ሰብአዊ ልክነተ እንዲኖረው ለማድረግ የሚል መሆኑ ያመለክታሉ።








All the contents on this site are copyrighted ©.