2016-04-23 09:47:00

ቅ. አ. ፍራንቼስኮ በቅድስተ ማርታ የጸሎት ቤት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ "እግዚአብሔር በእኛ እና በዘመናት ውስጥ የፈጸማቸው ተግባራትን ማስታወስ ያስፈልጋፋል" ማለታቸው ተገለጸ።


ቅዱስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ፍራንቸስኮ ዘወትር ጥዋት በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤተ መስዋዕተ ቅዳሴ እንደ ምያሳርጉ የሚታወቅ ሲሆን በትላንታናውም ጥዋት ማለትም በሚያዝያ 14,2008 እንደ ተለመደው በርካታ ካህናት እና ምዕመናን በተገኙበት ባደረጉት ስብከተ ወንጌል “እግዚአብሔር በእኛ እና በዘማናት ውስጥ የፈጸመውን ታላቅ ተግባራት ማስታወስ ወደ አምላክ ይበልጥ እንድንቀርብ ያደርገናል” ማለታቸው ተገለጸ።

በዕለቱ በተነበበው ምንባብ ላይ ተንተርሰው ክርስቲያኖች ያለፈውን ሕይወታቸውን ዞር ብለው መመልከት እና ማስታወስ ይገባቸዋል በማለት ስብከታቸውን የጀመሩት ቅዱስነታቸው እግዚአብሔር በሕይወታችን የፈጸማችውን አንኳር ተግባራት እና ያሳየንን ምልክቶች ማስታወስ እግዚአብሔር በሕይወታችን ውስጥ የነበረበትን ጊዜያት እንድንገነዘብ ይረዳናል ገልጸዋል። 

በማህደረ ትውስታችን ውስጥ እግዚኣብሔር የፈጸማቸውን ወብ እና መልካም የሆኑ ነገሮችን እና እንዲሁም እንቅፋቶችን እና ተቀባይነትን ባጣንበት ጊዜ ሁሉ እግዚአብሔር ለእኛ ቅርብ የሆነባቸውን ጊዜያት እና በክፉ ሥራችን አፍረን እና ፈርተን እንዳንጠፋ የጠበቀንን እግዚአብሔርን ማስታወስ ይገባል በለዋል።

“እግዚአብሔር እንዴት እንዳዳነን ዞር ብለን መመልከት ይገባናል” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉ ቅዱስነታቸው “በልባችን እና በህሊናችን በምናስብበት ወቅት ሁሉ ወደ ኢየሱስ እንድንቀርብ ያደርገናል” ብለዋል። “ሁላችንም እንደ ምናስታውሰው ኢየሱስ እራሱ ነው በጸሎተ ሐሙስ ማታ እና በስቅለት አርብ  ስጋውን እና ደሙን ‘ይህንን ለእኔ መታሰብያ አድርጉ’ ብሎ እንደስጠን የምያሳየው እግዚአብሔር ያደረገልንን የማዳን ተግባር ማስታወስ አስፈላጊ መሆኑን ነው” ብልዋል።

“አንድ ክርስቲያን ያለፈበትን የሕይወት ጎዳና በማስታወስ፣ እግዚአብሔር እየረዳው እጁን ይዞ  እዝህ ድረስ እንዳደረሰው ማወቅ ይጠበቅበታል ብለው አንድ አንዴም ጌታን እኔ አልፈልግህም ከእኔ ወድያ ሂድ ብለን በምናመናጭቀው ወቅት ሁል እግዚአብሔር ፋላጎታችንን ያከብራል ይህንንም ማወቅ ያስፈልጋል” ብለዋል። “ምንም እንኳን” አሉ ቅዱስነታቸው “ምንም እንኳን እግዚአብሔር የእኛን ምርጫ የምያከብር ቢሆንም ያለፈው ሕይወታችንን ቆም ብለን ማሰብ እና መንገዳችንን እንዴት እየተጓዝን እንደ ሆነ ማወቅ አስፈላጊ ነው፣ ይህንንም ተግባር ሁሌ ማስታወስ አስፈላጊ መሆኑንም በአጽኖት ገልጸዋል።

“ይህንን በምናደርግበት ጊዜ ሁሉ እግዚአብሔር የሰጠንን ፀጋ በማስታወስ ይህንን ወይም ያንን ፈጽሜኋለው ነግር ግን በነግሮቼ ሁሉ እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ነበር ብለን ስናስብ፣ ያደረገልንን በማሰብ ወደ እርሱ እንድንመለስ የምያደርግ አጋጣሚን የፈጥርልናል ብለዋል።

በስብከታቸው ማጠቃለያ ላይ ቅዱስነታቸው የጌታ ጥበቃ ሁል ጊዜም ቢሆን ከእኛ ጋር መሆኑን አስታውሰው ነገር ግን በሕይወታችን ዘመን ስንት ጊዜ ለዝህ ለጌታ ጥበቃ በራችንን ዘግተናል? ስንት ጊዜስ እርሱን እንዳላየን ሆነን አልፈናል? ስንት ጊዜስ እርሱ ከእኛ ጋር እንደ ሆነ ሳናምን ቀርተናል? ስንት ጊዜስ ያሳየንን የማዳን ምስጢር ክደናል? እነዝህን እና እነዝህን የመሳሰሉ ተግባራትን በምንፈጽምበት ጊዜ ሁሉ እርሱ እግዚኣብሔር ከእኛ ጋር መሆኑን ይቀጥላል ብለውዋል ቅዱስነታቸው።

በትጨማሪም ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ግንኙነት ምን ይመስላል? እግዚአብሔር በእየ አንድ አንዳችን ሕይወት ውስጥ የፈጸማቸው ውብ እና ድንቅ ሊባሉ የሚችሉ ተግባሮችን ሁል ጊዜ ማስታወስ አስፈላጊ ነው” ብለው ስብከታቸውን አጠናቀዋል።   

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.