2016-04-21 11:45:00

ቅዱስ አባታች ፍራንቸስኮ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን "ኢየሱስ በኋጥያት እና በኋጥያተኛ መኋከል ያለውን ልዩነት ጠንቅቆ ያውቃል" ማለታቸው ተገለጸ።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ ዘወትር ረዕቡ ዕለት በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለጠቅላላ አስተምሮ ለተሰብሰቡ  ምዕመናን እና ሀገር ጎብኚዎች የዕለቱን ወንጌል ተንተርሰው “ኢየሱስ በፈሪሳዊው ስምሆን ቤት እራት መጋበዙን አውስተው “ሁላችንም ኋጥያተኞች ነን ምክንያቱም በጣም ብዙ ጊዜ እኛ ከሌሎች  የተሻለን ሁነን እንዲሰማን በምያደርገን የግብዝነት ፈታና ስለምንወድቅ ነው” ብለው “ሁላችንም ኋጥያታችንን እና ወደቀታችንን ተመልከተን ወደ ጌታ መቅረብ እንደ ሚገባ አውስተው  ይህም የምያሳየው የእምነታችን ምሰሶ የሆነውን በጌታ እና በኋጥያተኛ መኋከል ያለውን ግንኙነትን ማጠናከር ነው” ማለተቸው ተገለጸ።

 ቅዱስነታቸው ከሉቃስ ወንጌል በመጥቀስ በኋጥያተኛነቷ የምትታወቅ አንዲት ሴት ወደ ኢየሱስ መጥታ በእግሩ ሥር ተንበርክካ እያለቀሰች እና እግሮቹን ወድ በሆነ ሽቶ እየቀባች በጸጉርዋ እግሩን ታብስ እንደ ነበር ጠቅሰው ፈሪሳዊያን ግን ወጭያዊ ገጽታውን ብቻ ተመልክተው እንደፈረዱባት ገልጸኋል። ነገር ግን አሉ ቅዱስነታቸው “ነግር ግን ኢየሱስ በኋጥያት እና በኋጥያተኛ መኋከል ያለውን ልዩነት ጠንቅቆ ያውቅ ስለነበር እንደ ፈሪሳዊያን በችኮላ ሊፈርድባት አልፈለገም” ብለኋል።

“ጌታ ግን” አሉ ቅዱስነታቸው “ጌታ ግን ለስምሆን ሴቲቷ በእግዚአብሔር ምሕረት ላይ ያላትን እምነት እና የመታመን መግለጫ የሆነውን ተግባር በመጸሟ የኃጥያቱዋ ሁሉ ይቅርታ ማባሉን” ለስምሆን በግልጽ አስረድቶታል ብለኋል።

ቅዱስነታቸው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰብሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኚዎች “የእግዚአብሔር ምሕረት ለሁሉም ቅርብ ነው” ብለው “ጭፍን ጥላቻን እና መሰናክሎችን ሁሉ የመገርሰስ እና የማስወገድ ኋይል” እንዳለውም ገልጸኋል።

በመጨረሻም “በክርስቶስ ባለን እምነት ምክንያት እኛም ለኋጥያታችን ስርሄት አግኝተናል በዝህም አዲስ የሕይወት ጸጋ ተቀብለናል” ብለው የሰማይ ንግሥት ሆይ የሚለውን ጸሎት ከምዕመናን ጋር ከደገሙ ቡኋላ ለሕዝቡ ቡራኬን ሰጥተው እና ሰላምታን አቅርበው የዕለቱን አስተምሮ አጠናቀኋል።

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.