2016-04-19 11:22:00

ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለጠቅላላ አስተምሮ ለተገኙ ሰዎች ያስተላለፉት መልዕክት


ባለፈው ቅዳሜ ማለትም እንደ አውሮፓዊያን የቀን አቆጣጠር በሚያዝያ 16.2016 የግሪክ ደሴት የሆነችውን እና ጦርነትን እና መከራን በመሸሽ ወደ አውሮፓ እየትሰደዱ ያሉትን ስደተኞች እያስተናገደች ባለችሁ የሌስቮስ ደሴትን በጎበኙት ወቅት ቅዱስ አባታች “ብዙ ስቃይን አይቻለው” ማለታቸው ተገለጸ።

በትላንትነው ዕለት ማለትም እንደ አውሮፓዊያን የቀን አቆጣጠር በሚያዚያ 17,2016 በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ሳምንታዊ የጠቅላላ አስተምሮኋቸውን ለመከታተል ለተሰበሰቡ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኚዎች ስሜትን በሚነካ መልኩ ቅዱስነታቸው  ስደተኞች በጣም አስከፊ ሊባል በምችል ሁኔታ ላይ እንደ ሚገኙም ደሴቲቱን ከግሪክ የኦርቶዶክስ ፓትሪያርክ በርቴለሜውስ እና የአቴንስ ሊቀ ጳጳስ ከሆኑት ኤሮንየሙስ ጋር በጎበኙበት ወቅት መታዘባቸውን አስታውቀኋል።

በተመሳሳይ ወቅት በትላንትናው ዕለት በኤኳዶር በደረሰው የመሬት መንቀጥቀት ሕይወታቸውን ላጡ እስካሁን ባለው መረጃ መሰረት 272 ሰዎች እና በተጨማሪም በጃፓን በደርሰው ተማሳስይ አደጋ ነብሳቸውን ላጡ ሰዎችም በዕለቱ ጸሎት ማድረሳቸውም ተዘግቡኋል።

የሰማይ ንግሥት የምለውን ፀሎት ካሳረጉ ቡኋላ ቅዱስነታቸው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለትሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኚዎች እንደ ገለጹት የግሪክ ደሴት የሆነችሁን ለስቮስ በጎበኙበት ወቅት በሁሉም የእድሜ ክልል የሚገኙ ስደተኞችን መመልከታቸውን ገልጸው ዓለም ልያገላቸው እና ልያርቃቸው ብፈልግም፣ እነርሱን የምያቀርብ እና መከራቸውን መጋራት የምችል ለሌላ ሀይል መኖሩንም ጨምረው ገልጸኋል።

ከኢራቅ፣ ከፍጋንስታን፣ ከሶሪያ እና ከአፍሪካ እንዲሁም ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች የተውጣጡ ስደተኞች የምኖሩበትን የስደትኛ ጣብያ ገቦኝተናል በማለት ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስ አባታችን 300 የሚሆኑ ስደተኞችን አንድ በአንድ ሰላም ብለናቸው ነበር ብለኋል። ከእነዝህም ስደተኞች መካከል ብዙ ሕጻናት እንደ ሚገኙ የገለጹት ቅዱስነታቸው፣ ከእንዝህም ሕጻናት አንድ አንዶች ወላጆቻቸውን እና  ቤተ ዘመዶቻቸውን አስታመው የቀበሩ፣ አንዳንዶቹም ከባሕር አደጋ የተረፉ መሆናቸውን እና በአጠቃላይ ከፍተኛ የሆነ ሐዘን የሰፈረበት ቦታ መሆኑን ለመረዳት ችያለሁ ብለዋል ቅዱስነታቸው።

በጉብኝቱ ወቅት ያጋጠመኝን አንድ ሰው ታሪክ ባካፍላችሁ ደስ ይለኛል በማለት ንግግራቸውን የቀጠሉ ቅዱስነታቸው “ይህ ሰው የእስልምና እምነት ተከታይ ሲሆን የምወዳት እና የምትወደው፣ የምያከብራት እና የምታከብረው ክርስቲያን ሚስት እንደነበረው ገልጾ ነገር ግን ይቺ የምወዳት ሚስቱ እምነቷን እንድትክድ በአሸባሪዎች በተጠየቀች ጊዜ እንቢ እንዳለች እና ክርስቶስን መካድ እና እምነቷን መለወጥ እንደ ማትፈልግ በመግለጿ ብቻ መታረዷን እያለቀሰ ነግሮኝ ነበር” ብለው ይህ ድርጊቱዋ እንደ ሰማዕት ልያስቆጥራት እንደ ምችልም ጨምረው ገልጸኋል ቅዱስነታቸው።

በኤኳዶር እና በጃፓን በደርሰው የመሬት መንቀጥቀጥ ሕይወታቸውን ያጡትን ሰዎች ማስታውስ ይገባል በማለት ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በዝህ አስከፊ እና ቅጽበታዊ አደጋ ነብሳቸውን ያጡት ሰዎች ቤተሰቦችን መጽናናትን ተመኝተው መልካም እረኛ የሆነው ኢየሱስ ጥበቃው ከእነርሱ ይሆን ጸንድም የዘወትር ጸሎታቸው መሆኑንም ጨምረው ገልጸኋል።

“እኔ መልካም እረኛ ነኝ። መልካም እሬኛ ነብሱን ለበጎቹ አሳልፎ ይሰጣል። ማንም ሰው በጎቼን ከእጄ ልነጥቃቸው አይችልም” የምለውን እና ከዩሐንስ ወንጌል ከምዕራፍ 10 የተውሰደውን የዕለቱን ምንባብ መሰረት በማድረግ ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት “ከእነዝህ ቃላት መረዳት የምንችለው የኢየሱስን ቃል የማንሰማ ከሆነ ማንም ሰው የእርሱ ተከታዮች ናችሁ ልለን እንደ ማይችል በመሆኑ ይህ “ማዳመጥ” የምለው ቃል መታየት ያለብን ጠለቅ ብለን መሆን እንዳለበት ገልጸው የጋራ መግባባት ላይ የምያደርስን “ማዳመጥ” በምንተገብርበት ወቅት የእርሱ ተከታዮች መሆናችንን ማሳየት ስንችል ብቻ መሆኑንም አክለው አሳስበዋል።

ይህ “ማዳመጥ” የምለው ቃል ልወክል የምገባው በጆሮኋችን  መስማት የምለውን ብቻ ሳይሆን በልባችንም ማዳመጥ አስፈላጊ መሆኑንም ጭምር ገልጽኋል።

እነዝህ የኢየሱስ ቃላት “ሕይወታችን በኢየሱስ እጅ ላይ በምሆንበት ወቅት ሁሉ የእርሱ ጥበቃ ሁል ጊዜም ከእኛ ጋር እንደ ምሆን ነው” ያሉት ቅዱስነታቸው ስለ ዝህም ምንም አይነት ፍርሀት ልገባን አይገባም ምክንያቱ ማንም ሰው ከኢየሱስ እጅ ልነጥቀን ስለ ማይችል ነው ካሉ ቡኋላ ሁል ጊዜ የምያሸንፈው ፍቅር ብቻ መሆኑን ገልጸው ይህ የማይረታውን የኢየሱስ ፍቅር ሁል ጊዜ መፈለግ እንደ ምገባ በመጥቀስ እና ቡራኬን ሰጥተው የእለቱን ንግግራቸውን እና አስተምሮኋቸውን አጠናቀኋል።

                                                     

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.