2016-04-13 16:23:00

የኬንያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት፥ ምግባር ብልሽትና ዘጋዊ መከፋፈል እንዲወገድ


በናይሮብ የኬንያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ባካሄደው ይፋዊ ምሉእ ጉባኤ ፍጻሜ ባወጣው መግለጫ በአገሪቱ የሚታየው ምግባረ ብልሽትና ሙስና እንዲሁም የተለያዩ የፖለቲካ ሰልፎች ዘጋዌ ላይ የተመሠረተ የሚፈጥሩ የፖለቲካ ሰልፍ ጥርናፌ የሚቃወም ባጠቃላይ የአገሪቱ ወቅታዊው ሁኔታ የሚዳስስ መልእክት ማስተላለፋቸው ፊደስ የዜና አገልግሎ ይጠቁማል።

የኬንያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ይላሉ ኬንያ፡ ማኅበራዊ እሴቶችና ተዋረድ መሠረታውያን ደንቦች በልቡ የሚያስቀድም ዜጋ ሁሉ አገሪቱን ላደጋ የሚያጋልጣት ጉዳይ ሁሉ በጋራ በመቃወም በጋራ መፍትሔ በማፈላለጉ አግልግሎት እንዲጠመድ በማሳሰብ፡ በአሁኑ ወቅት እየታየ ያለው ምግባረ ብልሽት ሙስናና በኤኮኖሚው በፖለቲካካው ዓለም የሚታየው ዘጋዌ ስብስብ ለአገር አንድነት አደጋ መሆኑ ለይቶ ሊመለከተው ይገባል እንዳሉ የገለጠው ፊደስ የዜና አገልግሎት አክሎ፥

ሙስናና ምግበረ ብልሽት አገር የሚያመነምን ነቀረሳ ነው

በፁዓን ጳጳሳቱ ምግባረ ብልሽት በአሁን ወቅት ኬንያን እያመነመነ ያለው ምግባረ ብልሽት ድኽነት የጤና ጥበቃ የማግኘት መብት መዛባት የትምህርት ቤቶችን መዋቅሮች ጥራት ጎደል እንዲሆኑ የሕንጸት ዘርፎች ሁሉ ገንቢ አስተዋጽኦ እዲሰጡ የማይደግፍ እንዲሆን የሚያደርግ፡ የሥራ አጡ ብዛት በተለይ ደግሞ ወጣቱ ትውልድ በሥራ አጥነት ችግር እንዲጠቃ የሚያደርግ ግብረ ሙስና በሁሉም ዘርፍ እንዲስፋፋ እያደረገ መሆኑ በማብራራት፡ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ህዳር 2015 ዓ.ም. በአገሪቱ ዓለም አቀፋዊ ሐዋርያዊ ጉብኝት በማካሄድ ሁሉም ምግባረ ብልሽት ካለ ምንም እጅ መስጠት ወይንም መሰላቸት እስኪ ያከትምለት ድረስ በጽናት ይኸንን ማኅበራዊ ነቀርሳ በጋራ እንዲዋጋ አደራ ያሉትን ቃል የኬንያ ብዓን ጳጳሳት ባስተላልፉት መልእክት ዋቢ በማድረግ ጥሪው ዳግም እንዳሰጋቡ ያመለክታል።

እየተስፋፋ ያለው የዘጋዌ (ጎሰኛነት) አደገኛነቱ

የኬንያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የአገሪቱ የሕግና ፍትሕ አገልጋይ ዜጎች የኬንያ ሕገ ደንብ እንዲከበር የሚያደርግ የአንድ አገር መንግሥታዊ መዋቅር ከሆኑት ውስጥ አንዱ ሆኖ እያለ ነገር ግን በምግባረ ብልሽት ታምሶ ማየቱ አሚያሳዝን ብቻ ሳይሆን የዜጎች በሕግ ላይ የነበራቸው እማኔ የሚያዳክም ብሎም ጨርሶ እንዲጠፋ የሚያደርግ መሆኑ በማሳሰብ፡ ከዚሁ ጋር በማያያዝም ሥር እየሰደደ ያለው ዘጋዊነት ማለትም ጎሳዊነት በተለይ ደግሞ ይኽ አይነቱ አደገኛው ክፍፍል ለተለያዩ የፖለቲካ ሰልፎች ስብስብ መሰረት ሆኖ ሲታይ የሚያስከትለው አደጋ ከወዲሁ ለመገመት አያዳግትም። በመሆኑ ይኸንን አይነቱ የፖለቲካዊ ሰልፎች የመጠራነፉ ጉዳይ የሕዝብና የአገር አንድነት ለአደጋ የሚያጋልጥ መሆኑ ከወዲሁ በማስገንዝብ የፖለቲክ ሰልፎች ጥርናፌ ፖለቲካዊ መራሐ ግብር እንጂ ዘግወ መሆን የለበትን እንዳሉ ፊደስ የዜና አገልግልት አመለከተ።

የጎሳ ልዩነት አደገኛነቱን እያወቁ ነገር ግን ይኽ ልዩነት የግል ጥቅማቸውን ለማረጋገጥ እንደ መሣሪያ የሚያውሉ ሁሉ ሕዝብንና አገርን ለአደጋ የሚያጋልጡ ናቸው። አለ ምንም ሃፍረት በተለያየ ሥፍራ ዘጋዊነት የሚተገብሩ በተለያየ ዘርፍ ሁሉ የዘመድ አዝማድ አሠራር በማስፋፋት የውሁድን ጎሳ እንደ ተገዥ የብዙሃኑ ደግሞ እንደ ገዥ የሚያስቀምጥ አመለካከትና ፖለቲካዊ አወቃቀር ገቢራዊ ሆኖ አገርንና ሕዝብን ለከፋ አደጋ ከማጋለጡ በፊት መወገድ ይኖርበታል እንዳሉ ፊደስ የዜና አገልግሎት ገለጠ።

ኬንያ ተስፋዋን እንዳታጨልም

በመጨረሻም እ.ኤ.አ. በ 2017 ዓ.ም. በኬንያ የሚካሄደው ሕዝባዊ ምርጫ የአገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳት ከወዲሁ በማስተዋል ነጻው የምርጫ ሂደት ተቆጣጣሪው ድርገት ሕዝባዊ ምርጫው ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትና አገር ልማት ለአደጋ በሚያጋልጥ ተግባር እንዳይበከል ማለትም በምግባረ ብልሽትና በሙስና እንዳይጠቃ በቅርብ እንዲከታተል አደራ በማለት የአገሪቱ ዜጎች በግልና በአገር ደረጃ በመተባበር ማንኛውም ዓይነት ምግባረ ብልሽት አገር ለአደጋ የሚያጋልጥ ተግባር ሁሉ እንዲታገል ማሳሰባቸው ፊደስ የዜና አገልግሎት ይጠቁማል። 








All the contents on this site are copyrighted ©.