2016-04-06 16:18:00

ነፓል፥ መንግሥት በዓለ ልደት በአገሪቱ ባሕረ ሃሳብ ብሔራውያን በዓላት ተብለው ከሚጠቀሱት ውጭ አደረገ


የአገረ ነፓል መንግስት ከአገሪቱ ባሕረ ሃሳብ ዘንድ ብሔራውያን በዓላት ተብለው ከሚመለከቱት ውስጥ አንዱ የነበረው እ.ኤ.አ. ታህሳስ 25 ቀን የሚከበረው የጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ልደት መሰረዙ ኤሺያን ኒውስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

የአገሪቱ የውስጥ ጉዳይ ሚኒ. ሻክቲ ባስነ መንግሥታቸው ከባሕረ ሐሳብ በዓለ ልደት እንዲነሳ ያደገገበት ምክንያት በአገሪቱ ባሕረ ሐሳብ ዘንድ ያለው የበዓላት ቀናት ብዛት ግምት በመስጠት በበዓላት ምክንያት የማይሠራባቸው ቀናት ዝቅ እንዲል ማድረግ ያለው አስፈላጊነት ያስተዋለ ነው በማለት እንደገለጡ ያመለከተው ኤሺያን ኒውስ የዜና አገልግልት፡ በዓለ ልደት ለሚያከብሩ የአገሪቱ ዜጎች በበዓለ ልደት ቀን የእረፍት ቀን ሆኖ ይታሰብላቸዋል እንዳሉ ሲገልጥ ሆኖም የአገሪቱ ማኅበረ ክርስቲያን አባላት የመንግሥት ሠራተኞች ብቻ አይደሉም ብዙዎችም በግል ድርጅቶች የሚሠሩ ናቸው እንዲህ በመሆኑም መንግሥት የወሰደው ውሳኔ ተቀባይነት የለውም ሲሉ የነፓል ክርስቲያን ፈደራላዊ ማኅበር ጠቅላይ ዋና ጸሓፊ ጋሃትራጅ በሰጡት መግለጫ በማብራራት በአገሪቱ ባሕረ ሐሳብ ውስጥ 83 የበዓላት ቀናት የተመለከቱ ሲሆን እነዚህ ብሔራዊ በዓላት ተብለው በባሕረ ሓሳብ እውቅና ያገኙት በጠቅላላ የሂንዱና የሌሎች ኃይማኖቶች በዓላት ሲሆኑ የክርስትና ሃማኖት በዓላት ውስጥ አንድም እንደሌለ በማስታወስ መንግሥት የወሰደው ውሳኔ የአድልዎ ተግባር ነው እንዳሉ አስታወቀ።

እስካሁን ድረስ በዓለ ልደት በአገሪቱ ባሕረ ሐሳብ ዘንድ ብሔራውያን በዓላት ተብለው ከሚጠቀሱት ውስጥ አንዱ ሆኖ መቆየቱ ሲታወቅ። ብዙ ክርስቲያን ያልሆነው የአገሪቱ ዜጋ ጭምር እንደ ቅቡል ብቻ ሳይሆን የዚህ በዓል ማራኪነቱንም ያስተዋለና እ.ኤ.አ. በ 2015 ዓ.ም. በዓለ ልደት ህንድ በአገሪቱ ላይ የወሰደችው የኤኮኖሚ ማእቀብ እንዲነሳ ጥያቄ እንደ ሃሳብ ያደረገ እንደነር ያስታወሱት መጋቤ ጋሃትራጅ መግሥት የወሰደው እርምጃ ማኅበረ ክርስቲያን  በሁለተኛ ደረጃ የሚቀመጥ ዜጋ ነው እንዳሉ ኤሺያን ኔውስ የዜና አገልግሎት ይፋ ሲያደርግ፡  ብዙ የተለያዩ በነፓል የሰብአዊ መብት ተሟጋችና የብሔር ማኅበራትና በጠቅላላ የተለያዩ ሀይማኖታውያን ማኅበራት የመንግሥት ውሳኔ በመቃወም ድምጻቸውን እያሰሙ መሆናቸው አስታውቀዋል።

የኔፓውል የተለያዩ ሃይማኖቶች የጋራው ምክር ቤት ተቃውሞው እያሰማ ሲሆን ማኅበረ ክርስቲያን ስለ እምነቱ ለመሰዋት ዝግጁ ነው ያሉት መጋቤ ጋሃትራጅ አክለው ውሳኔው በመንግሥትና በክርስትያን ማኅበረሰብ መካከል ከዚህ ቀደም የተደረጉት ስምምነቶች ለአደጋ የሚያጋልጥ መሆኑ በማብራራት በሕገ መንግሥት ውስጥ ባለው የመቅጫ ሕገ አንቀጽ 156 ሃይማኖትን መቀየር ወንጀል ነው በማለት የሚገልጠው ርእስ ለገዛ እራሱ ካህናትና የክርስቲያን ማኅበራትን ሌሎች አቢያተ ክርስቲያን መብትና ክብር የሚጻረር ነው እንዳሉ ኤሺያን ኒውስ አመለከተ።

በነፓል የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በማኅበራዊና በሕንጸት ዘርፍ የምትሰጠው አስተዋጽኦ አቢይ መሆኑ በአገሪቱ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን በመንግሥትም እውቅና ያለው እውነት ነው፡ ያ 1.5 በመቶ የሚገመተው ካቶሊክ በ 2006 ዓ.ም. ብዛቱ 0.5 በመቶ የነበረው በስድስት ዓመት ውስጥ ብቻ ከአራት ሺሕ ወደ10 ሺህ ከፍ እንዳለና 100  በካቶሊክ አቢያተ ክርስቲያን የሚመሩ የአገሪቱ አምራች ዜጋ በማሰናዳቱ ሂደት አቢይ አስተዋጽኦ የሚሰጡ 100 አቢያተ ትምህርት እንዳሉ ኤሺያን ኔውስ የዜና አገልግሎት ያመለክታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.