2016-04-06 16:11:00

ቅድስት መንበርን በማገልገል አብነት ለሆኑት የተሰጠው ልዩ የእውቅና ሽልማት


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮ በአገረ ቫቲካን ቅድስት ማርታ ሕንፃ የቫቲካን ረዲዮ መሥተዳድር ኃላፊና የር.ሊ.ጳ. ሐዋርያዊ ጉዞዎች አዘጋጅ በመሆን ላገለገሉት ለዶክተር አልበርቶ ጋስባሪና ቤተሰቦቻቸውን ተቀብለው ለዶክተር ጋዝባሪ ቅድስት መንበርን በማገልገል አብነት ለመሆናቸው እውቅና በመስጠት የፒያኖ ማኅበር የዓቢይ መስቀል ፍረሰኛ ሽልማት መስጠታቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።

በተካሄደው የሽልምናት አሰጣጥ ሥነ ሥርዓት የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን፡ ብፁዕ ካርዲናል ፊሎኒ፡ ብፁዕ ካርዲናል ረ፡ ብፁዕ ካርዲናል በርተሎና ብፁዕ ካርዲናል ስተላ እንዲሁም ብፁዕ አቡነ ፒየሮ ማሪኒ፡ ፕሮፈሰር ናቫሮ ቫልስ፡ ብፁዕ አቡነ ጋኤንስዋይን መሳተፋቸው የገለጠው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ የሽልማቱ ያሰጣጥ ስነ ሥርዓት እንዳበቃም ዶክተር ጋዝባሪ ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ስንበት በኋላ በተዘጋጀላቸው የእንኳን ደስ አለዎት ሰላምታ በመለዋወጥ ሥነ ሥርዓት የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ተኪ ብፁዕ አቡነ አንጀሎ በቺዩ ባሰሙት ንግግር ዶክተር ጋዝባሪ ተመድበው ያገለገሉበት ኃላፊነት አድካሚ ከመሆኑም ባሻገር እጅግ ጥናቃቄ የሚጠይቅ ነው፡ ር.ሊ.ጳ.ን በተለያዩ አህጉራት ባካሄዷቸው ጉብኝቶች በመሸኘት የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይንና ቅድስት መንበርን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ያገለገሉ ታታሪ አገልጋይ በማለት እንደገለጡዋቸው የተካሄደው ስነ ሥርዓት የተከታተሉት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ አስታወቁ።

ጋዝባሪ በሽልማቱ ያሰጣጥ ስነ ሥርዓት ቤተሰቦቻውና እንዲሁም የቅዱስ ጴጥሮስ ብሔራዊና ዓለም አቀፋዊ ሓዋርያዊ ጉብኝቶች በተለያዩ የኃላፊነት ሥር በመታቀፍ እያገለገሉ የሚገኙትን ሁሉ እንዲሳተፉ ማድረጋቸው ጂሶቲ ሲያመለክቱ በእውነቱ የሰጡት አገልግሎት አለ ተባባሪዎቸውና የሥራ ባልደረቦቻቸው የተዋጣለት ባልሆነ ነበር በማለት ጋዝባሪ ባሰሙት ንግግር እንዳሰመሩበት ይጠቁማሉ።

የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሐዋርያዊ ጉዞዎችን ማዘጋጀት የእምነት ጽናትን ይጠይቃል

የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሐዋርያዊ ጉዞ አዘጋጅ መሆን ጉዞው የማይደጋገም እያንዳንዱ ጉዞ የገዛ እራሱ መለያ ያለው ሁሌ አዲስ እና ጥንቋቄ የሚጠይቅ የጉዞው ዓላማና የሚጎበኘው አገር ባህልና ታሪክ ማወቅ እንደ ቅድመ ሁነት የሚያስቀምጥና የእምነት ጽናት የሚጠቅ አገልግሎት መሆኑ ብፁዕ አቡነ በቺዩ ባሰሙት ንግግር እንዳበከሩ የገለጡት ልኡክ ጋዜጠኛ ጂሶቲ አክለው፥

ለዶክተር ጋዝባሪ የተሰጠው ሽልማት ቅንነታቸውና ያላቸው ሙያዊ ብቃት ጭምር በአድናቆት እውቅና የሰጠ ነው ያሉት ብፁዕ አቡነ በቺዩ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ በሚያደርጉዋቸው ጉዞዎች የሚያካሂዱት ግኑኝነቶች የሚያስተላልፉት መልእክት በአጠቃላይ የጉዞው መርሐ ግብር እጅግ ሰፊና ጥልቅ በመሆኑ በዚህ ጉዞ ቅዱነታቸውን መሸኘት በእውነቱ ቅድስት መንበር በጠቅላላ ለኵላዊት ቤተ ክርስቲያን የሚሰጥ አገልግሎት መሆኑ በእምነት የታገዘ አስተውሎ ካልተሰጠው በስተቀረ ዘልማድ ሆኖ ነው የሚቀረው ብለው በቫቲካን ረዲዮ ውስጥም የመስተዳድር ኃላፊ ሆነው በማገልገልም የሥራ መደራረብ የነበራቸው ቢሆንም ያላቸው የሙያ ብቃት ተደራራቢው ኃላፊነት በሙላት ሊወጡ እንዳገዛቸው ገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.