2016-04-05 10:57:00

"የእግዚአብሔር ምሕረት፣ ትዕግስት እና ፍቅር መግለጫ የሆነውን መጻሐፍ ቅዱስን አዘውትረን ልናነብ ይገባል"


በሚያዝያ 3,2016 በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለጠቅላላ አስተምሮ ለተገኙ ምዕመናን እና ሀገር ጎብኝዎች ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ “የእግዚአብሔር ምሕረት፣ ትዕግስት እና ፍቅር መግለጫ የሆነውን መጻሐፍ ቅዱስን ሁሉም ክርስቲያኖች አዘውትረው ማንበብ እንደ ሚገባቸው ማሳወቃቸው ተገለጸ።

እንደ አውሮፓዊያን የዘመን አቆጣጠር እና በላቲን ስርዓተ ሉጢርጊያ ደንብ መሰረት በመጋቢት 27,2016 ከተከበረው የፋሲካ በዓል ቡኋላ ቀጥሎ ያለው ሰንበት እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ያሳየውን መለኮታዊ ምሕረት የምታወስበት ሰንበት እንደ መሆኑ መጠን፣ ይህንን አጋጣሚ ተጠቅመው  እግዚአብሔር መሐሪ መሆኑን ያወሱት ቅዱስ አባታችን “ምሕረት ገደብ የለሽ ተግባር” መሆኑን ገልጸው “ባለንበት ወቅት የሰው ልጅ በህመም  እና ፍርሐት ውስጥ እያለፈ በሕይወቱ እርግጠኛ የማይሆንበት ደረጃ ላይ መደረሱን” አመልክተዋል።

“ማንኛውም ዓይነት ጠባሳ በእግዚአብሔር እርዳታ እና ምሕረት አጥጋቢ በሆነ መልኩ ልፈውስ ይችላል” በማለት አስተምሮኋቸውን የቀጠሉት ቅዱስ አባታችን ይህንን የእግዚኣብሔር ምሕረት በመላበስ የሚገኘውን በረከት ለዓለም ማዳረስ ይጠበቅብናል” ብለኋል።

“ይህንን ተግባር በሚገባ ለመፈጸም እንድንችል ግንዛቤን የሚሰጠን መጻሐፍ ቅዱስን አዘውትሮ ማንበብ አስፈላጊ መሆኑን አመልክተው የእግዚአብሔርን ምሕረት መረዳት የምያስችለን ግልጽ የሆነ መጽሐፍ” መሆኑንም ጨምረው ገልጸኋል።

በመቀጠልም “እግዚአብሔር የፈጸማቸው የምሕረት ተግባራት ሁሉ በመጻሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ተጽፈው  ይገኛሉ ማለት ባንችልም (ኢየሱስ ያደረጋቸው ሌሎች ብዙ ነገሮች አሉ፣ ሁሉም ነገር ቢጻፍ ለተጻፉት መጻሐፍት ሁሉ ዓለም በቂ ቦታ የሚኖረው አይመስለኝም። ዩሐ. 21.25) ነገር ግን እግዚአብሔር ቀን በቀን የሚያሳየንን ፍቅር፣ ፀጋ እንዲሁም ምሕረት እያከልንበት አብሮን እንዲጓዝ ማድረግ የምገባን ክፍት የሆነ ቅዱስ መጻሐፍ” መሆኑንም ጨምረው ገልጸኋል።

ቅዱስነታቸው “እግዚአብሔር በሕይወታችን የምፈጽማቸው ታላላቅ ወይም አናሳ ተግባራትን በማይታይ መልኩ ልያከናውናቸው እንደ ሚችል ገልጸው ኢየሱስ ከሙታን በተነሳ ወቅት በፍርሐት ተውጠው የነበሩ ሐዋሪያቱ ልብ ውስጥ የነበረውን ፍርሃት በምሕረቱ ማጥፋቱ በመጀመሪያ የምያሳየው በፍርሃት ተውጠው የምኖሩበትን ቤት በር መዝጋታቸው እና በሌላ በኩል ደግሞ ኢየሱስ ፍርሃታቸውን አስወግዶ ወደ ዓለም ሁሉ ልልካቸው ማሰቡን የምያሳይ ቋሚ ምልክት” መሆኑንም አስገንዝበኋል።

ቅዱስነታቸው በአስተምዕሮኋቸው ማመልከት የፈለጉት የሰው ልጆች ሁሉ በእንደ እዝህ ዓይነት አጣብቂኝ ውስጥ እንደ ምገቡ ለማመልከት እና የሰው ልጆች በአብዛኛው ልባቸውን ለእግዚአብሔር እንደ ሚዘጉ፣ ነገር ግን እግዚኣብሔር በምሕረቱ የተዘጋውን የሰው ልብ እንደ ሚከፍት የምያሳይ ጥሪ በመሆኑ ሳንዘገይ ላባችንን ለእግዚኣብሔር ምሕረት መከፈት እንዳለብን  ለማስገንዘብ  መሆኑም ጭምር ታውቁኋል።

“ወደ ሕያወት የምያመራ አንድ መንገድ ብቻ አለ” ያሉት ቅዱስ አባታችን “ይህም መንገድ ከእራስ ወዳጅነት በመላቀቅ በደሙ የገዛንን የክርስቶስን መንገድ መከተል ብቻ መሆኑን” ገልጸው “ይህም ማለት ደግሞ ለተቸገሩ ሰዎች ሁሉ የቻልነውን ያህል እጃችንን በመዘርጋት እና የአቅማችንን በመለገስ፣ በተለይም ደግሞ ቀርቦ የሰዎችን ችግር መስማት እና መረዳት በጣም አስፈላጊ ተግባር እና ወደ ሕይወት የሚመራን ጎዳን መሆኑን” አስረድተኋል።

ቅዱስ አባታችን፣ “ይህንን ዓይነት መንፈስዊ ተግባራትን በምንፈጽምበት ወቅት እግዚአብሔር በማያልቀው ምሕረቱ ሕይወታችንን ይጎበኛል፣  በችግራችን እና በድካማችን ጊዜ  ሁሉ ከእኛ ጋር እንደ ሚሆን እና እንደ ምያበረታን ልናምን ይገባል” በለኋል።

በመጨረሻም “ክርስቶስ የሰላም አባት በመሆኑ እና ኋጥያትን፣ ሞትን እና ፍራሃትን የማሰውገድ ሐይል ስላለው፣ በተጨማሪም እርሱ የምሰጠን ሰላም የምያለያየን ሳይሆን አንድ የምያደርገን ሰላም በመሆኑ ብቻችንን የማይተወንን፣ በመከራችን እና በሕመማችን ጊዜ ሁሉ የምያጽናናንን እና ተስፋችንን የምያለመልም ሰላም በመሆኑ የክርስቶስን ሰላም አጥብቀን ልንሻ ይገባል” በማለት አስተምዕሮኋቸውን አጠናቀኋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.