2016-04-01 16:05:00

ሐዋርያዊ ቤተ ኑዛዜ የጠራው መልክአ ምኅረት ዙሪያ የሚወያዩ ዓውደ ጉባኤ


ሐዋርያዊ ቤተ ኑዛዜ ቅዱስ አባታን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የምኅረት ዓመት ያወጁበት መልክአ ምህረት ርእስ ሥር የደረሱት ሰነድ ዙሪያ እንዲወያይ የተጠራው የሁለት ቀናት ዓውደ ጉባኤ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 1 ቀን 2016 ዓ.ም. መጠናቀቁ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዚጠኛ ፋቢዮ ኮላግራንደ አስታወቁ።

ስለዚሁ እ.ኤ.አ. መጋቢት 31 ቀን 2016 ዓ.ም. በሐዋሪያዊ ቤተ ኑዛዜ አቢይ አናዣዥ ብፁዕ ካርዲናል ማውሮ ፒያቸንዛ ባስደመጡት ንግግር የተጀመረው ዓውደ ጉባኤ በማስመልከት ለሐዋራዊ ቤተ ኑዛኤ ጉባኤ እንደራሴ ብፁዕ አቡነ ክርይስዝቶፍ ንይካይል ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፥ የጉባኤው ዋና ተሳታፍያን ካህናት ገዳማውያንና ደናግሎች እንዲሁም የቲዮሎጊያ ተማሪዎችና በተለያየ ሐዋያዊ ግብረ ኖልዎ መስክ በተለያዩ ቁምስናዎች የሚያገለግሉ ዓለማያን ምእመናን ናቸው። የተለያዩ የቲዮሎጊያ ዘርፎች ሊቃውንት ቅዱስ አባታን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የምኅረት ዓመት ያወጁበት መልክአ ምህረት ርእስ ሥር የደረሱት ሰነድ ዙሪያ በተለያዩ የቲዮሎጊያ ጥናት ዘርፎች አማካኝነት በማንበብ የሚያብራራ ጥልቅ አስተምህሮ ይሰጣሉ ብለው፥ የቤተ ክርስቲያን መሠረት ምኅረት ነው ብለዋል።

ምኅረት የወንጌል ማእከል ነው። ይኽ ደግሞ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ቅዱስ ጴጥሮሳዊ ሥልጣናዊ ትምህርታቸው የሚያጎላውና የትምህርታቸው መሠረት መሆኑ ገና የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታዮ ሆነው ከተመረጡ በኋላ እ.ኤ.አ. መጋቢት 19 ቀን 2013 ዓ.ም. የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ጴጥሮትስ ተከታይ ሥልጣናቸው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ በይፋ ጀምረው እ.ኤ.አ. የካቲት 7 ቀን 2013 ዓ.ም. የሮማ ጳጳስ ሐዋርይዊ ሥልጣናቸውን በይፋ ለማስጀመር በሮማ ጳጳሳዊ ባዚሊካ ቅዱስ ዮሐንስ ዘላተራኖ ባዚሊካ መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገው ባስደመጡት ስብከት ዘንድ ተመልክቶ እናገኘዋለን፡ በእግዚአብሔር መኃሪነት ላይ ያለን እምነት እንዴት የተዋበ ነው። ያወደር የማይገኝለት እግዚአብሔር ለእኛ ያለው ፍቅር መለኰታዊ ምኅረት መሆኑ ቅዱስነታቸው በጥልቀት ገልጠዉታል። የምኅረት ቅዱስ ዓመት እንኳርም እርሱ ነው ብለዋል።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ቤተ ክርስቲያን በጦርነት ሜዳ መሀል የምትገኝ የሕክምና ቤት በማለት ይገልጧታል። ይኽ ደግሞ በቤተ ክርስቲያንና በጌታችን እየሱስ ክርስቶስ መካከል ያለው ግኑኝነት ምን ተመስሎው ይገልጥልናል። የቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ምጢራዊነት የሚግልጥና ቤተ ክርስቲያን ወደ የከተሞቻችንና የህልውና ጥጋ ጥግ ክልል እንድትል መጠራቷ የሚያረጋግጥልን ጥልቅ ሃሳብም ነው። ቤተ ክርስቲያን የዚያ የእግዚአብሔር እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ከእኛ ጋር መሆኑን እውን ለሚያደርገው ክርስቶስ  ህልው የሆነባት ህያው ምስክር ነች ብለዋል።

በምኅረት ቅዱስ ዓመት የአዋጅ ሰነድ ቁጥር 17 ላይ እንደምናነበው የንስሐና የዕርቅ ሚሥጢር ፍሬዎችና ምንመት መካከል ያለው ግኑኝነትና የእግዚአብሔር ምኅረት ጥልቅ ትርጉሙ እናገኛለን። ተርቱሊያኖ በጻፈው የአጶሎጊያ እርሱም የትክክለኛ ትምህርት ለመከላከል አልሞ በደረሰው ሰንድ ዘንድ አናዣዝ ባጋጣሚ የሚኮን ሳይሆን ተኵኖ ነው እርሱም እናዛዥ ለመሆን መጠራትና በጥሪው በመታነጽ ማደግን እንደሚጠይቅ ያብራራል። ስለዚህ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮም ለዚሁ ነው አንድ አናዛዥ አናዛዥ ከመሆኑ በፊት ዕለት በዕለት የምኅረት ጣዕም የሚያጣጥምና የሚኖር መሆን አለበት የሚሉት። አናዛዦች ለምእመናን ልክ የዚያ ጠፍቶ የተገኘ ልጅ ታሪክ የሚኖሩ ሆኖ መገኘት አለበት፡ ጠፍቶ የተገኘው ልጅ በአባቱ ዘንድ የተሰጠው ክብር የሚገልጡና ይኸንን ሁነት የሚኖሩ መሆን እንደሚጠበቅባቸው ያሳስባሉ። ምኅረትና የምኅረት ቦታ ትክክለኛው ሥፍራ የቅዱስ መንፈስ ሥፍራ   ነው ሲሉ ቅዱስነታቸው የገለጡት ሃሳብ አስታውሰው ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.