2016-03-30 15:35:00

በደቡብ ሱዳን ለተጨባጭ ሰላም ከአቢያተ ክርስቲያን ሃሳብ ቀረበ


በደቡብ ሱዳን የሁሉም አቢያተ ክርስቲያን ምክር ቤት አባላት የሃማኖት መሪዎች በአገራቸው ያለው የብዙ ሰው ሕይወት ለሞት የዳረገው የእርስ በእርስ ግጭት እልባት እንዲያገኝና ሰላምና መረጋጋት እውን እንዲሆን ሰላማዊ የጋራ ኑሮ ለማሳካት በሚደረገው ጥረት በቁርጠኝነት የሚጠበቅባቸው አስተዋጽኦ ከማበርከት ወደ ኋላ እንደማይሉ ገልጠዋል ሲል ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

በዚያች በሉኣላዊነት ቅዋሜ እጅግ ወጣት በሆነቸው አገረ ደቡብ ሱዳን ባለፉት 27 ወራት ለ 12 ሚሊዮን የሚገመተው የአገሪቱ ዜጋ ለተለያየ ችግር ያጋለጠው አስከፊው ደማዊ የእርስ በእርስ ግጭት የተከሰተባት ስትሆን። የአገሪቱ የአቢያተ ክርስቲያን የሃይማኖት የበላይ መንፈሳዊ መሪዎች በበዓለ ፋሲካ ምክንያት ባስተላለፉት መልእክት፥ ይህች በእርስ የእርስ ጦርነት እጅግ የደማችን አገራችው ሰላም እንደሚያፈልጋት ገልጠው፡ ሙሉ አቅማቸውንና ብቃታቸውንም ሁሉ በማሰባሰብ የግጭቱና የዓመጹ ታሪክ ወደ የሰላም ታሪክ እንዲለወጥ የሚጠበቅባቸው አስተዋጽኦ ዛሬም እንደ ጥንቱ ለማቅረብ ዝግጁነታቸውን በማደስ፡ አቢያተ ክርስቲያናቱ በሚያነቃቁት የሰላም ዓውደ ጉባኤዎችና ውይይቶች ሁሉ የዓመጽ ምክንያት በመለየት መጪው የደቡብ ሱዳን አገር ግንባታ ለማፋጠንና የመጻኢው አገራዊ መርሃ ግብር ይተገበርም ዘንድ በቁርጠኝነት እንዲሚያገለግሉ ማረጋግጣቸው የገለጠው ፊደስ የዜና አገልግሎት አያይዞ፥ የአቢያተ ክርስቲያን መሪዎች ዝግጁነታቸው ላረጋገጡበት ዓላማ የጁባ ለካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ኣቡነ ፓውሊኖ ሉኩዲ ሎሮ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ድጋፍና ሱታፌ በማረጋገጥ፥ ሕጻናት አዛውንት ንጹሓን ዜጎች ለሞትና ለመፈናቀል አደጋ ሲጋለጡ ዝም ብሎ ለማየት የሚቻለን አይደለም። ኢፍትሓዊነት ሊከሰትብን የተፈጠርን ሳይሆን ለድህነት የተፈጠርን ነን እንዳሉ ገልጠዋል።    








All the contents on this site are copyrighted ©.