2016-03-30 15:29:00

በበልጂም፣ በሙስሊም የአገሪቱ ማኅበረሰብ ፍርሃትና የውይይት ፍላጎት መፈራረቅ


በበልጂም አሸባሪያን አክራሪያን ሙስሊሞች ከጣሉት ግብረ ሽበራ ወዲህ በአገሪቱ ኅብረተሰብ መካከል እንዲሁም በአገሪቱ የምስልምና ሃይማኖት ተከታዮች መካከል ፍርሃት የሚያዛምት ቢሆንም ቅሉ በሕዝቡ መካከል የውይይት ፍላጎት እንዳይላጨለም የልብ ብርሃን የተሰየመው የሙስሊሞና ክርስቲያኖች የጋራ ዘማሪያም ቡድን መሪ የአፍቅሮተ ዘቤት ካቶሊካዊ ማኅበር በተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል በሚያነቃቃው የጋራ ውይይት የተሰኘውን መፈሳዊነት ሥር የሁሉም ሃማኖቶ ስለ ጋራ ውይይት አቢይ አስተዋጽኦ በመስጠት ላይ የሚገኙት ኑፊሳ ቡችሪፍ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃአ ምልልስ ገልጠው። አሸባሪያን የጣሉት ጥቃት ባጠቃላይ የምስልምና ሃይማኖት ጸንፈኞች የሚከተሉት ያክራሪነት መንገድና ግብረ ሽበራ በጠቅላላ በ 99,99 በመቶ የበልጂም ዜጋ አለ ምንም የሃይማኖት ልዩነት ተቀባይነት የሌለው ውጉዝ ተግባር በማለት ይገልጠዋል፡ ግብረ ሽበራ ከምስልምናው ሃይማኖት ጋር ምንም ዓይነት ትስስር የለውም፡ ስለዚህ የምስልምና ሃይማኖት ተገን በማድረግ የሚፈጸመው ግብረ ሽበራ በቅድሚያ ጸረ የምስልምና ሃይማኖት ተግባር ነው፡ ስለዚህ የተጣለው የሽበራ ጥቃት በሙስሊሞች ይደገፋል ብሎ መናገር ለገዛ እራሱ ግብረ ሽበራና አሸባሪያን የሚሹት ማኅበራዊና ሃይማኖታዊ ግጭት መደገፍ ይሆናል። ሙስሊሙ ለየት ባለ መልኩ ይኸንን ተግባር ማውገዝ ይኖርበታል የሚሉ አሉ። ሁሉም ሰላም ወዳጅ ዜጋ አለ ምንም የሃይማኖት ልዩነት ያወግዘዋል፡ ነገር ግን ሙስሊሙና የምስልምናው ሃይማኖት ሁሉ ተጠያቂ አድርጎ መናገር ለገዛ እራሱ ጸረ የሰላም ተግባር ማረማመድ ነው ብለዋል፡፡

የተጣለው የሽበራው ጥቃት ሁሉም የበልጂም ዜጋ የነካና በኅብረተሰብ ውስጥ የእርስ በእርስ አለ መተማመን በጎሪጥ የመተያየት አዝማሚያ እያስከተለም ነው። በርግጥ ማንኛውም ዓይነት ጦርነት ግጭትና ዓመጽ ለእርስ በእርስ አለ መተማመን ፈተና ሊገፋፋ ይችል ይሆናል ባህርያዊም ነው ነገር ግን አለ መተማመኑ በሌላው ላይ አመጽ ለማድረስ ምክንያት ሊሆን አይችልም። ግብረ ሽበራው በሁሉም ሙስሊምም ይሁን ክርስቲያን እና የሌላው ሃይማኖት ተከታዮች ጭምር ፍርሃት አሳድረዋል፡ ቢሆንም ቅሉ ፍርሃቱ ለመዘጋጋት ሳይሆን ለውይይት የሚገፋፋ ኃይል መሆን አለበት ካሉ በኋላ የሙስልም ሃይማኖት ተከታይ ወጣቶች የሚከተሉት ሃይማኖት ምክንያት ግብረ ሽበራውን ይደግፋሉ ብሎ መፍረዱ በእውነቱ አቢይ ስህተት ነው፡ ይኽ እንዳይሆንም በትምህርት ቤቶች የተለያዩ ቅስቀሳ ለማካሄድና ሰላማዊ ያብሮ ኑሮ የሚያናጋው ጸረ ሰላም ተግባር ሁሉ በመለየት ወጣቱ ትውልድ በአብሮ የሰላማዊ ኑሮ ግንባታ አስተዋጽኦ እንዲያበረክት የሚደገፍ እቅድ አስፈላጊ መሆኑ እየተስተጋባ ነው፡ የእግዚአብሔር ፍቅር በውስጣችን ነው፡ የተጣለው አመጽ ጸረ እግዚአብሔር በመሆኑም ጸረ ፍቅር ነው፡ ስለዚህ ይኽ በውስጣችን ያለው ፍቅር ማንኛምው ዓይነት ዓመጽ ሊያጠፋው እንደማይችል ታምነን ተስፋ በማነቃቃት በጋራ በመወያየት ወደ ፊት እንዲባልና የሁሉም የተለያዩ ሃይማኖቶች የጋራ ውይይት የሰላም መሣሪያ መሆናቸው በመመስከር ሁልን ለሰላም እንዲያነቃቁ ኃላፊነት አለባቸው በማለት ያካሂዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.